Get Mystery Box with random crypto!

'የትም ተወለድ Competent ሁን' ነው መርሁ 'ለሕልም ተርጓሚዎችም ሕልሜን ነገርሁ የሚተረጕ | ናዝራዊ Tube

'የትም ተወለድ Competent ሁን' ነው መርሁ

'ለሕልም ተርጓሚዎችም ሕልሜን ነገርሁ የሚተረጕምልኝም አጣሁ።' ይላል የግብጽ ንጉስ ፈርዖን። ዮሴፍ በባርነት ተሽጦ የሚኖር የግብጽ ዜግነትም መብትም ያልነበረው እስረኛ ነበር። የንጉሱን ሕልም ፈታ ፈታ አድርጎ በዚያ ብቻ ሳያበቃ በግዞት ለሚኖርባት አገር የ14 አመታት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ቁጭ ቁጭ አድርጎ ዞር ሊል ሲል ፈርዖን ይመሰጥበትና 'ወዴት ወዴት. . . ?! አንተው ካመጣኸው አንተው አሩጠው እኔ ፈታ ልበልበት' ብሎ ስልጣኑን በሙሉ ለጆሲ delegate አድርጎ relax ማድረግ ቀጠለ! ግብጽ በግዜው በነበረው geo-political reality DV የሚሞላባት አገር ሆነች። ሰው ሁሉ ለsurvival የሚሸሽባት። Bible ነው ይህንን የሚነግርህ።

ዛሬ ታሪኩን አንብቤው ገርሞኝ ነው። ባቢሎንን፣ ፋርስና ሜዶንን፣ ሮምን. . . ብትጠቅስ መሪዎቻቸው ከዘር ይልቅ competence ላይ አተኩረው ገራሚ skill የነበራቸውን ግለሰቦች ከየትኛውም ጎሳ እየሰበሰቡ በመንግስታቸው ስርዓት አጥምቀው በአሪፉ reward እያደረጉ ተጠቅመው ይጠቅሙ ነበር። They recognized talent. ዳንኤል፣ ሲድራቅ፣ ሚሳቅ . . . talented ምርኮኞች ነበሩ። Somebody recognized their merit. (ያው ለግዜው theologyን ትተን historyው ላይ እናተኩር) That somebody was a great leader who know what to value and whom to reward. ዝም ብሎ ዘሬ፣ ብሔሬ. . . ገለመሌ የሚል ዝባዝንኬ ሳያበዛ problem solverን ከየትም የዓለም ጥግ ፈልጎ አግኝቶ reward ያደርጋል።

አማሪካን ተመልከት። የፈለገ ዘረኞች ቢሆኑ አሪፍ ብቃት ካለህ ከየትኛውም የዓለም ጉራንጉር ውስጥ ጭቃህን እያራገፍክ ብትመጣም ግድ ሳይላቸው እየተነጫነጩም ቢሆን ዶላር ይበጥሱልሃል። ለዚያ እኮ ነው ከእኛው ጨለማ ገጠር ወጥተው ወደ ምዕራባውያኑ የፈለሱ አንዳንድ የተሳካለቸው talented አበሾች autobiography ሲጽፉ፣

ከመዳ ወላቡ እስከ Malibu፣
ከአርማጭሆ እስከ Idaho፣
ከዋልድባ ገዳም እስከ Amesterdam
ከዋድላ-ደላንታ እስከ Atlanta
ከሸገር እስከ Manchester
ከገላን እስከ Milan

የሚል ቅጥያ ርዕስ ጨምረው ተዓምር የመሰላቸውን destiny እያሰቡ የሚነግሩን። ‘እዚህ ግባ ከማይባል ሰፈር ብወለድም እዚህ ግባ ብለውኝ ይኸው እያኖሩኝ ነው’ የሚል መልዕክት ያደርሱናል።

እናማ በአጭሩ ምን ለማለት ነው. . . በገራሚ ክህሎት ሰልጥነን እስካልተዘጋጀን ድረስ ዘሬ፣ ብሔሬ፣ አያቴ. . . ስንል ዛሬም መዘበቻ እና እጅግ ከሚገባው በላይ የተናቅን ህዝቦች ሆነናል። ምንም ነው የእኛ ብሔር። ችግር ፈቺዎች ናቸው ድርሻ ያላቸው በዚህች ዓለም።

ምን ያምረኛል. . . ይህንን ሁሉ ሚሊየን በብሔሩ ብቻ ተመክቶ ውጥርጥር ብሎ አገር ጠበበኝ የሚልን ወጠምሻ ሰብስቤ ትልልቅ የምዕራባውያን ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የጉልበት ስራ እንዲሰራ አራግፌ መምጣት! አለ አይደል incompetencyውን እና ስንፍናውን በብሔሩ ውስጥ ተሰውሮ የሚሸሸውንና የሌሎችን ስኬት ለመቀማት አገር የሚያምሰውን ወስጄ ጥልቅ እና ሰፊ coal mine ውስጥ ከሰል በአካፋ እየዛቀ ሰርቶ በላብ ማደርን እንዲማር መተው።

ይቆጫል ኢትዮጵያ መወለድ።
Yared Donis
@nazrawi_tube