Get Mystery Box with random crypto!

Muktarovich Ousmanova

የቴሌግራም ቻናል አርማ muktarovichousmanova — Muktarovich Ousmanova
ርዕሶች ከሰርጥ:
Fastmereja
የሰርጥ አድራሻ: @muktarovichousmanova
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 63.74K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopia forever

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2024-04-11 11:07:36
ፖለቲከኛው በቴ ኡርጌሳ “በጸጥታ አካላት” ከተያዘ በኋላ ነው የተገደለው- የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት

ግድያው “ባልታወቁ ሰዎች” የተፈጸመ ነው- የኦሮሚያ ክልል መንግስት

ሚያዝያ 03 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) ብሎ የሚጠራው ቡድን ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ በኩል ባወጣው መግለጫ በቴ ኡርጌሳ በመቂ ከተማ ካረፉበት ሆቴል እኩለ ሌሊት ላይ “በጸጥታ አካላት” ከተወሰዱ በኋላ ተገድለዋል ሲል ገልጿል።

ኢሰመኮን ጨምሮ ሌሎችም የኦነግ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ግድያ ነጻ ምርመራ እንዲድረግበት እየጠየቁ ሲሆን... ዝርዝሩን ከድረ ገጻችን https://addismaleda.com/archives/36451 ይመልከቱ
———
12.9K views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 12:11:42
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የህዝብ ግኑኝነት ከፍተኛ ሀላፊ አቶ በቴ ኡርጌሳ መገደላቸውን ኦሜን ዘገበ።
በተወለዱበት መቂ ከተማ ከሆቴል  አውጥተው እንገደሏቸው መረጃ ደርሶኛል ብሏል።
17.5K views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 11:50:11
የአማራ ህዝብ ዛሬ ከጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ጎን መሆኑ ለማስመስከር ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እያካሄደ ነው ተብሎ ይህ ፎቶ እየተዘዋወረ ነው። የአማራ ህዝብ የአብይ ዋነኛ ደጋፊ ነበረ። በሚልዮኖች ወጥቶ ደግፎአል። ዛሬ ይህችን የምታክል የመንደር ስብስብ ሰልፍ እንደ ድጋፍ መቁጠር በጣም የሚያስተዛዝብ ነው። መንግስት የአማራ ህዝብን ችግር እና ግጭት በስክነት በመመልከት ወደ ቀልቡ መመለስ አለበት።
15.1K views08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 19:33:14
ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች በፖሊስ ድብደባ እና እስራት ተፈፀመባቸው

ተማሪዎቹ የተራዘመ የመመረቂያ ግዜን በመቃወም ሰልፍ የወጡ ሲሆን የትግራይ የፀጥታ ሐይሎች ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እንደፈፀሙባቸው ለዶቼቬለ ተናግረዋል፣ 10 ተማሪዎች ደግሞ መታሰራቸው ተገልጿል።

እንደ ተማሪዎቹ ገለፃ በፖሊስ የሐይል እርምጃ አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸው ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ አሪድ ግቢ ተነስተው ያሏቸውን ቅሬታዎች ለማሰማት ወደ መቐለ ከተማ ጎዳናዎች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት ነው።

ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተገደዱት በተለያዩ ችግሮች ለዓመታት ትምህርታቸው ሲስተጓገል ቆይቶ ዘንድሮ ለመመረቅ እየተጠባበቁ የነበረ ቢሆንም፤ ዩኒቨርሲቲው ሌላ ተጨማሪ ዓመት መማር እንደሚጠበቅባቸው ከተገለፀላቸው በኃላ ነው።

ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት ግን ለዩኒቨርሲቲው በተደጋጋሚ ቅሬታ ማቅረባቸውን እና ከዩኒቨርሲቲው ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልፀዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ በነበሩበት ወቅትም ጥይት በመተኮስ፣ በድብደባ እና በአፈሳ ፖሊስ ሰልፉን በሐይል መበተኑ ተማሪዎቹ አስረድተዋል።

Source: Deutsche Welle Amharic
14.0K views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 14:48:18
ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር ከሀገሯ ማባረሯን ገለጸች።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ ከአራት ወራት በፊት በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል።

ይህ ስምምነት ሶማሊላንድን የራሷ ሉአላዊ ግዛት አድርጋ በምታያት ሶማሊያ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣንና እና ተቃውሞን ማስከተሉም አይዘነጋም።

ይህንን ተከትሎም ሶማሊያ የተለያዩ ዲፕሎማያው እርምጃዎችን ስትወስድ የቆየች ሲሆን፤ ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያን አምባሳደር ከሀገሯ ማባረሯን ሮይተርስ ዘግቧል።

እንደ ዘገባው ከሆነ ሶማሊያ በሞቃዲሾ የኢትዮጵያን አምባሳደር ያባረረች ሲሆን ለውሳኔው መነሻ የሆነው ደግሞ ከሶማሊላንድ ጋር ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ ባደረገችው የወደብ ስምምነት ምክንያት ነው።

ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በፑንትላንድ እና ሶማሊላንድ ያሉ የኢትዮጵያን ቆንስላ ጽህፈት ቤቶችንም ዘግቻለሁ ብላለች።

አል ዐይን አማርኛ በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነቢዩ ተድላ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

በተያያዘ ዜና የፑንትላንድ ገንዘብ ሚንስትር መሀመድ ፋራህ የመሩት ልዑክ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ ፑንትላንድ በገንዘብ ሚንስትሯ መሀመድ ፋራህ የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጉን ተናግረው ይህ የአዲስ አበባ ጉብኝት ከሰሞኑ ወቅታዊ ጉዳይ ጋር የማይገናኝ እንደሆነ እና የጉብኝት ፕሮግራሙም የቆየ ቀጠሮ ነው ሲሉ በዛሬው ሳምንታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች መግለጫቸው ላይ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ባሳለፍነው ጥር ወር ላይ ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ባደረጉት የወደብ መግባቢያ ስምምነት ምክንያት የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት እንዲሻክር ምክንያት ሆኗል።
17.9K views11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 17:19:55
ትዝታ ገረመው ስራ አገኘች፣ ተቀጥራለች።
#FastMereja
ትዝታ ገረመው አዲሱን ስራዋን በኢትዬጲያን ቢዝነስ ሪቪዊ (Ethiopian Business Review) የመረጃ ጥንቅር እና ምርምር ኦፊሰር (Data Researcher) ሆና ሚያዝያ 1 ሥራ ለመጀመር የቅጥር ደብዳቤ ዛሬ ተቀብላለች።
15.5K views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 12:02:20
መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

28ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 28ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የመካከለኛ ዘመን 2017-2021 የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማዕቀፍ ላይ ነው፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚና ፊሲካል ማዕቀፉ የመንግስት በጀት ከማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታው እና የፊሲካል አቅም ጋር ተጣጥሞ እንዲዘጋጅ ለማድረግ፤ ከመንግስት ገቢ አሰባሰብ እና ሀብት አመዳደብ አኳያ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በማመላከት ለቀጣይ በጀት አመት የበጀት ዝግጅት ለማድረግ፤ የመካከለኛ ዘመን የመንግስት ገቢና ወጪ እንዲሁም የፊሲካል ሚዛን የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለመለየት እና ለማመላከት የሚያገለግል ማዕቀፍ በመሆኑ ምክር ቤቱ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የተጨማሪ እሴት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በሀገሪቱ የእኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የተደረጉ ለውጦችን በህግ ማእቀፉ ውስጥ ማስገባት በማስፈለጉ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ጫና እንዳያርፍባቸው ለማድረግ የሚያስችል ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብዓቶችን በማከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

//

#PMOEthiopia
16.7K views09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 20:15:23
አዲሱ አዋጅ “ስለ መኖሪያ ቤት ኪራይ ውል” ዘመን ምን ዝርዝር ይዟል?

ዛሬ በፓርላማ በጸደቀው “የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ” ከተዘረዘሩ ድንጋጌዎች ውስጥ፤ “የመኖሪያ ቤት የኪራይ ውል ዘመንን” የሚመለከቱት የሚጠቀሱ ናቸው። “የመኖሪያ ቤት ኪራይ የውል ዘመን ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም” ሲል የደነገገው አዋጁ፤ ይህ የተደረገበትን ዋነኛ ምክንያት በማብራሪያው ላይ አስፍሯል።

“የአዋጁ ዓላማ የመኖሪያ ቤት ኪራይ የተረጋጋ እንዲሆን ለማድረግ በመሆኑ፤ [ውሉ] ከሁለት ዓመት ያነሰ ቢሆን አከራዩ ውሉን ለማደስ ፍቃደኛ ላይሆን ስለሚችል፤ ተከራይ በየጊዜው በቀጣይ ስለሚከራየው ቤት በመጨነቅ የተረጋጋ ህይወት እንዳይመራ ያደርገዋል” ሲል የአዋጁ ማብራሪያ አትቷል። “ከሁለት ዓመት ያለፈ ዘመን ይኑረው ቢባል ደግሞ የአከራይን መብት እንዳይጫን፤ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የውል ዘመኑ ከሁለት ዓመት ያላነሰ ጊዜ እንዲሆን” መደረጉን የአዋጁ ማብራሪያ አስገንዝቧል።

“አዋጁ ከመውጣቱ በፊት ከሁለት ዓመት በታች የተደረጉ የቤት ኪራይ ውሎች ላይ ይህንን አዋጅ ተግባራዊ ማድረግ ፍትሐዊ ስለማይሆን፤ በውላቸው ላይ ያጸደቁት ቤት ኪራይ የውል ዘመን ተቀባይነት እንዲያገኝ ተደርጓል” ሲል ማብራሪያው አክሏል። ከዚህ በተጨማሪ የውል ዘመን ሳይጠናቀቅ፤ የአንድ ቤት ባለቤትነት “በውርስ፣ በሽያጭ፣ በዕዳ ወይም በሌላ ማናቸውም ህጋዊ ምክንያት” ለሌላ ወገን ከተላለፈ፤ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውሉ ሊቋረጥ የሚችለው “ቤቱ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ የሚቆጠር የ6 ወር ማስጠንቀቂያ ለተከራይ በመስጠት ቤቱን እንዲለቅ ማድረግ እንደሚቻል ማብራሪያው” ደንግጓል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

* * ዝርዝሩን ከታች ከተያያዘው ምስላዊ መረጃ ይመልከቱ
17.5K views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 18:15:27
በመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ፤ በተቆጣጣሪ አካል እንዲወሰን የሚያደርግ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ

በመኖሪያ ቤቶች የሚደረገው የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ላይ፤ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እንዲሁም በክልሎች በሚቋቋም ተቆጣጣሪ አካል በሚወስነው መሰረት እንዲከናወን የሚያደርግ አዋጅ ዛሬ በፓርላማ ጸደቀ። የተቆጣጣሪ አካሉ “የሀገሪቱን ነባራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች” ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ በየዓመቱ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ ዓመት የሚጸና የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርግ በአዲሱ አዋጅ ተደንግጓል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከጸደቀበት ዕለት ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆነው ይህ አዋጅ፤ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደርን ለመደንገግ የተዘጋጀ ነው። በስድስት ክፍሎች እና በሰላሳ ሁለት አንቀጾች የተዋቀረው አዋጁ፤ ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ እና ዋጋ፣ ውል የሚቋረጥባቸውን አካሄዶች፣ የተቆጣጣሪ አካል ስልጣን እና ተግባር እንዲሁም የጥቆማ እና ቅሬታ አቀራረብ ስነ ስርዓትን የተመለከቱ ድንጋጌዎችን በውስጡ አካትቷል።

“የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር” የሚመለከተው ይህ አዋጅ ከያዛቸው ድንጋጌዎች መካከል፤ “ነባር የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን” የተመለከተው ይገኝበታል። “አዋጁ ከመውጣቱ በፊት በጹሁፍ የተደረገ ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል፤ በአከራይ እና ተከራይ ስምምነት እንዲቋረጥ ካልተደረገ በስተቀር፤ በአግባቡ መረጋገጥ እና መመዝገብ እንዳለበት” በአዲሱ አዋጅ ላይ ሰፍሯል።

ውሉ መመዝገብ እና መረጋገጥ ያለበት፤ በዛሬው ዕለት በጸደቀው አዋጅ መሰረት የሚቋቋመው “ተቆጣጣሪ አካል” በተሰየመ በ30 ቀናት ውስጥ እንደሆነ በአዋጁ ተቀምጧል። ክልሎች የሚመሰረተው አካል፤ የውል ማረ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
17.1K views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 12:21:46
የአስራ አንድ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት (ሲኦፒ) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ለመወያየት የቀረበለትን ጥሪ ውድቅ ያደረገው መንግሥት በአገሪቱ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ የመነጋገር ፍላጎት ስለሌለው መሆኑን ገለጸ።
ኦፌኮ ከጠቅላዩ ጋ የተደረገውን ውይይት እንዲሳተፍ ቢጠየቅም ጥያቄውን አለመቀበሉን ተናግረዋል።
17.8K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ