Get Mystery Box with random crypto!

Muktarovich Ousmanova

የቴሌግራም ቻናል አርማ muktarovichousmanova — Muktarovich Ousmanova
ርዕሶች ከሰርጥ:
Fastmereja
የሰርጥ አድራሻ: @muktarovichousmanova
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 63.74K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopia forever

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2024-04-18 14:32:31
በብራዚል በሞተ ሰው ስም ብድር ለመውሰድ አስክሬኑን በዊልቸር ላይ አድርጋ ወደ ባንክ የመጣችዉ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች

የ42 ዓመቷ ብራዚላዊት ሴት ህይወቱ ያለፈ ባለቤቷን ወደ ባንክ አምጥታ በስሙ ከባንክ ብድር ለማዉጣት ስትሞክር በቅርቡ በቁጥጥር ስር ውላለች።

ማክሰኞ ሚያዚያ 9 ቀን ኤሪካ ዴ ሱዛ ቪየራ ኑነስ የተባለችዉ ግለሰብ ህይወቱ ካለፈዉ የ68 ዓመቱ ፓውሎ ሮቤርቶ ብራጋ ስም 3,200 ዶላር የባንክ ብድር ለማዉጣት ወደ ባንጉ፣ ሪዮ ዴጄኔሮ ወደሚገኘው የኢታው ዩኒ ባንኮ ቅርንጫፍ መጥታለች። የአዛውንቱን በዊልቸር ላይ የነበሩ ሲሆን አጎቷ እንደሆኑ እና የመጀመሪያ ተንከባካቢ መሆኗን ተናግራለች። የባንኩ ሰራተኞች ብዙም ሳይቆይ በብራጋ ላይ ከባድ ችግር እንዳለ አስተውለዋል፡፡ምክንያቱም ይህችዉ ሴት የሟችን ጭንቅላት በእጇ ስትደግፍ ጥርጣሬ ፈጥሮባቸዋል። እናም ምንም አይነት በህይወት እንዳለ የሚያሳይ ምልክት አልታየበትም፣ ነገር ግን ቪየራ ኑነስ በተፈጥሮው ዝምተኛ እንደሆነ ለባንኩ ሰራተኞቹ እየነገራቻቸዉ ነበር ተብሏል።

ምንም እንኳን ለምትጠይቀዉ ጥያቄ መልስ የመስጠት አቅም እንደሌለው ግልጽ ቢሆንም አስክሬኑን ልታናግረው ስትሞክር ትታያለች፡፡“አጎቴ እየሰማህ ነው? መፈረም አለብህ። ካልፈረምክ ምንም መንገድ የለም ” እያለች ስትናገር እንደነበር ምስክሮች ኤሪካ ዴ ሱዛ ቪዬራ ኑነስ በዊልቸር ላይ ለተቀመጠዉ አስከሬን ስትናገር ሰምተዋል፡ "ላንተ መፈረም አልችልም፤ማድረግ የምችለውን አደርጋለሁ፤ ተጨማሪ ራስ ምታት እንዳትሰጠኝ ስምህን መዝግብ ስትል ትደመጣለች፡፡

ከባንኩ ሰራተኞች አንዱ "ደህና ነው ብዬ አላምንም" ሲል ይደመጣል፤ቪዬራ ኑኔስ ግን "አጎቷ" ደህና እንደሆነ ትናገራለች ፣ ትንሽ ዝምታ ስለሚያበዛ ነዉ በማለት ለማስተባበል ሞክራለች፡፡

ዳጉ ጆርናል
18.6K views11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-18 13:10:29
ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀሲስ በላይ መኮንን በተጠረጠሩበት በሀሰተኛ ሰነድ የዶላር ዝውውር ወንጀል ለምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ፡፡

የፌደራል ፖሊስ መርማሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ከትናንት በስቲያ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ በአካል ቀርበው ሀሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን በመያዝ ለ3 ግለሰቦች እና ለአንድ የግል ድርጅት ሒሳብ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሊያዘዋውሩ ሲሉ በአፍሪካ ህብረት ሴኪዩሪቲዎች ተይዘው ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ተላልፈው መሰጠታቸውን ጠቅሶ የጥርጣሬ መነሻውን ለችሎቱ አቅርቧል።

በዚህ መነሻ መሰረትም መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ሥራ ለማከናወን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ተጠርጣሪ ቀሲስ በላይ መኮንን ድርጊቱ መፈጸሙን አምነው፤ ይሁን እንጂ ወንጀል አለመፈጸማቸውን አስረድተዋል፡፡

ስለሆነም የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ በማለፍ ለፖሊስ የ7 ቀናት የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል።
#FBC
19.1K views10:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 13:19:04
" "የአማራ ታጣቂዎች" ያቋቋሟቸውን አስተዳደሮች ለማፍረስ ከፌደራል መንግስት ጋር ተስማምተናል ሲል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ

ይህን ዜና በሰማን በማግስቱ ዛሬ የአማራ ክልል መንግስት ተወረርኩኝ መግለጫ አውጥቷል። የሚገርመው የፌዴራል መንግስት ይህን ወረራ ይከላከልልኝ ማለቱ ነው። ለአለማቀፍ ማህበረሰብም አቤቱታ አሰምቷል። ለአማራ ህዝብና ፋኖም እንደቀድሞው ሁሉ "ሀገርን ከመፍረስ" አብረን በመታገል፣ ከ"ሀዲውን ህወሓት አብረን እንታገል ብሏል
18.7K viewsedited  10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 13:56:48
በከፋ ዞን በገጠመ የትራፊክ አደጋ አምስት ሰው ወዲያው ሲሞት፣ በርካቶች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ገጥማቸዋል
20.6K views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 13:14:06
የትህነግ ወታደሮች በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ትጥቅ መፍታት፣ Disarm ወታደሩ ወደየቤቱና ሞያው መበታተን Dimobilize እና መልሶ ወደ መደበኛ ህይወት መመለስ ነበረበት።
ይህ አልሆነም። እንደምታዩት ራያን ወረዋል። ምስሉ፣ አላማጣ ሲገቡ ነው። ወደ ሌላ ዙር ጦርነት የትግራይ ህዝብ ገብቷል።
በርግጥ የሚያሳምም ነው።
ነገም በወልቃይት የሚነሳ ነው ይህ ነገር። ያሳዝናል
20.6K views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 13:01:31
አለምነ ያስደነገጠው የኦርቶዶስ ቄስ የግድያ ሙከራ

ታዋቂው  የኤሲሪያን  (አሶራውያን) ኦርቶዶክስ ቄስ ብጹዕ አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል (ቢሾፕ ማር ማሪ) ሲድኒ ውስጥ በዘውትራዊውና የተመለደው ቀጥታ የሚሰራጭ  የስብከት መርሃ ግብራቸው ላይ ሳሉ ማንም ባልገመተው ሁኔታ አንድ ሰው በፍጥነት ተጠግቶ በጩቤ ፊትና አንገታቸው አካባቢ ሲወጋጋቸው የሚያሳይ ምስል ተለቋል። እጅግ ይዘገንናል። የሰው ልጅ ጭካኔ ብሷል። ዓለሙ እያበደ ነው።   መስቀል የያዘ የሃይማኖት አባት በጩቤ እንዴት ይወጋል?...  ምዕመን መስሎ ገብቶ በአደባባይ ይህንን መፈጸም ግን እብደት እንጂ ምን ይባላል?
ተወግተው ተርፈዋል።
ጨርሶ ይማራቸው።
የአለም ጭካኔ ከብዷል።
19.4K views10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 10:49:47
የሕወሃት ኃይሎች በራያ አላማጣ አንዳንድ ቦታዎችን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ፤ የፕሪቶሪያዉ ስምምነት ጠላቶች ያደረጉት እንጂ በሕወሃት አልያም ጊዜያዊ መስተዳድሩ የተፈጸመ አለመሆኑን አቶ ጌታቸዉ ረዳ ተናገሩ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ፣ በደቡብ ትግራይና በሌሎች በኃይል የተያዙ የትግራይ ግዛቶች ባኹኑ ወቅት የተፈጠረው ክስተት በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ወይም በሕወሃት ወይንም በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል የተፈጠረ ግጭት አይደለም ሲሉ ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ በኤክስ ትስስር ገጻቸው ላይ መለጠፋቸውን ተመልክተናል።

ጌታቸው፣ ክስተቱ ኹለቱ ወገኖች የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እያደረጉት ያለውን አወንታዊ ግንኙነት ለማደናቀፍ የፈለጉ የስምምነቱ ጠላት የኾኑ ኃይሎች የፈጠሩት ነው በማለት ከሰዋል።

ኹለቱ ወገኖች ችግሮችን ለመፍታትና የሚስማሙባቸውን ጉዳዮች ለማጎልበት አዲስ አበባ ውስጥ ስብሰባ ላይ እንደኾኑም ጌታቸው ጠቁመዋል።

ሕወሃት ጥቃት ከፍቶ ተቆጣጥሯቸዋል የተባሉት አካባቢዎችን በተመለከተም አብን ማምሻውን ጠንከር ያለ መግለጫ አሰራጭቷል።

አብን የሕወሃት ኃይሎች በድጋሚ በአማራ ሕዝብ ላይ "አራተኛ ዙር" ጥቃት ከፍተዋል ሲል ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከሷል። የፌዴራሉ መንግሥትና የአማራ ክልላዊ መንግሥት ሕወሃት በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተውን ሌላ ዙር ጥቃት ባስቸኳይ እንዲያስቆሙ የጠየቀው አብን፣ የአማራ ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት የሕወሃትን ጥቃት እንዲመክትም ጥሪ አድርጓል።

አብን ይህን መግለጫ ያወጣው፣ የሕወሃት ኃይሎች በራያ አላማጣ አካባቢ አንዳንድ ቦታዎችን እየተቆጣጠሩ ስለመኾኑ በተሰማ ማግስት ነው።
19.5K views07:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 11:05:18 ሀገሪቱ የጥቂቶች ሳይሆን በጣት ለሚቆጠሩት እንደሆነች ማሳያውን እዩት

"ብሔራዊ ባንክ ሐሙስ ሚያዝያ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የፋይናንስ ስታቢሊቲ ሪፖርት (Financial Stability Report) የባንክ ብድሮች በጥቂት ተበዳሪዎች እጅ ተከማችተው እንደሚገኙ ይጠቅሳል።

በአገሪቱ ያሉት ሁሉም ባንኮች እስካለፈው ዓመት ሰኔ መጨረሻ ድረስ በሥራ ላይ ካዋሉት አጠቃላይ 1.9 ትሪሊዮን ብር ብድር ውስጥ 23.5 በመቶውን ያበደሩት ለአሥር ተበዳሪዎች እንደሆነ በሪፖርቱ ተካቷል።

ከፍተኞቹ አሥር ተበዳሪዎች ከአጠቃላይ የባንክ ብድር መጠን ውስጥ በ2014 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ከነበረው 18.7 በመቶ ነው በ2015 ዓ.ም. መገባደጃ ላይ ወደ 23.5 ያደገ ነው ተብሏል።"

ደሀው ኑሮ እየከፋበት፣ ሀብታሙ እንዲህ በሚሆንበት ሀገር ሰላም ይኖራል ማለት ዘበት ነው
17.0K views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 10:53:55
እስራኤል በኢራን ላይ ልትወስድ ባሰበችው የአጸፋ እርምጃ አሜሪካ እንደማትተባበር ገለጸች

ኢራን ሶሪያ በሚገኘው የቆንስላ ፅህፈት ቤቷ ላይ ለተቃጣባት ጥቃት ቅዳሜ ሌሊት እስራኤል ላይ 300 ሚሳኤሎችና ድሮን ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ እስራኤል ለምትወስደው የአጸፋ እርምጃ አሜሪካ እንደማትተባበር ገልጻለች።

አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን እሁድ ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጠው ማብራሪያ ፕሬዝዳንት ጆው ባይደን እስራኤል ልትወስደው ያሰበችው የአጸፋ እርምጃን በጥንቃቄ እንድታጤነው ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ማሳሰባቸው ነው የተገለጸው።

ፕሬዝዳንት ባይደን እስራኤል ከኢራን የተቃጣባትን ጥቃት በአሸናፊነት መወጣቷን የጠቀሱ ሲሆን በዋናነት በአሜሪካና አጋሮቿ እገዛ 99 በመቶ የሚሆኑት ጥቃቶች በሚሳኤል መከላከያ መክሸፋቸውን በማሳያነት አቅርበዋል።

የአሜሪካ የብሔራዊ ጸጥታ ቃል አቀባዩ ጆን ኪርቢ በበኩላቸው አገራቸው በቀጣናው ግጭቱ እንዳይስፋፋ ለእስራኤል አቋሟን ግልፅ ስለማድረጓን ገልጸዋል።

አሜሪካ ለኢራንም በተዘዋዋሪ የዲፕሎማሲያዊ መረጀ ልውውጥ ተመሳሳይ መልዕክት እንዳስተላለፈች ነው የተነገረው።

የእስራኤል የጦር ካቢኔ በኢራን ላይ ሊወሰድ ስለሚገባው የአጸፋ እርምጃ ዙሪያ ተወያይቶ ከስምምነት ላይ ሳይደርስ መበተኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
ይህ ውሳኔ አሜሪካ በቀጥታ ከገባች ራሺያና ቻይና ሊገቡ ስለሚችሉ ነው ተብሏል። ያኔ ሶስተኛው የአለም ጦርነት በይፋ ይጀመራል።
17.0K views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 23:20:08
0921388158
ጊዮን ሆምስ የጊዮን ቢዝነስ ግሩፕ አካል በመሃል ከተማ ሌላ ከተማ እየገነባ ይገኛል።
➷ወሎ ሰፈር መስቀል ፍላወር አጠገብ
50%የባንክ ብድር የተመቻቸለት
90% የተገነባ መንደር አፓርትመንቶች
በ10 % ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት
ይሁኑ
ባለ 1,መኝታ 96.5ካሬ
ባለ 2 መኝታ 168.9ካሬ
ባለ 3 መኝታ 205ካሬ
➷50 አመት በቢዝነሱ ዘርፍ ልምድ ያካበተው
በውስጡ ስምንት እህት ኩባንያዎችን የያዘ
ጊዮን ቢዝነስ ግሩፕ
https://youtube.com/@Modernhouseinethiopia?si=O1OgP4AI7Re2Yv5w
17.7K views20:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ