Get Mystery Box with random crypto!

የሕወሃት ኃይሎች በራያ አላማጣ አንዳንድ ቦታዎችን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ፤ የፕሪቶሪያዉ ስምምነት | Muktarovich Ousmanova

የሕወሃት ኃይሎች በራያ አላማጣ አንዳንድ ቦታዎችን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ፤ የፕሪቶሪያዉ ስምምነት ጠላቶች ያደረጉት እንጂ በሕወሃት አልያም ጊዜያዊ መስተዳድሩ የተፈጸመ አለመሆኑን አቶ ጌታቸዉ ረዳ ተናገሩ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ፣ በደቡብ ትግራይና በሌሎች በኃይል የተያዙ የትግራይ ግዛቶች ባኹኑ ወቅት የተፈጠረው ክስተት በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ወይም በሕወሃት ወይንም በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል የተፈጠረ ግጭት አይደለም ሲሉ ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ በኤክስ ትስስር ገጻቸው ላይ መለጠፋቸውን ተመልክተናል።

ጌታቸው፣ ክስተቱ ኹለቱ ወገኖች የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እያደረጉት ያለውን አወንታዊ ግንኙነት ለማደናቀፍ የፈለጉ የስምምነቱ ጠላት የኾኑ ኃይሎች የፈጠሩት ነው በማለት ከሰዋል።

ኹለቱ ወገኖች ችግሮችን ለመፍታትና የሚስማሙባቸውን ጉዳዮች ለማጎልበት አዲስ አበባ ውስጥ ስብሰባ ላይ እንደኾኑም ጌታቸው ጠቁመዋል።

ሕወሃት ጥቃት ከፍቶ ተቆጣጥሯቸዋል የተባሉት አካባቢዎችን በተመለከተም አብን ማምሻውን ጠንከር ያለ መግለጫ አሰራጭቷል።

አብን የሕወሃት ኃይሎች በድጋሚ በአማራ ሕዝብ ላይ "አራተኛ ዙር" ጥቃት ከፍተዋል ሲል ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከሷል። የፌዴራሉ መንግሥትና የአማራ ክልላዊ መንግሥት ሕወሃት በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተውን ሌላ ዙር ጥቃት ባስቸኳይ እንዲያስቆሙ የጠየቀው አብን፣ የአማራ ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት የሕወሃትን ጥቃት እንዲመክትም ጥሪ አድርጓል።

አብን ይህን መግለጫ ያወጣው፣ የሕወሃት ኃይሎች በራያ አላማጣ አካባቢ አንዳንድ ቦታዎችን እየተቆጣጠሩ ስለመኾኑ በተሰማ ማግስት ነው።