Get Mystery Box with random crypto!

Muktarovich Ousmanova

የሰርጥ አድራሻ: @muktarovichousmanova
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 63.04K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopia forever

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-06-14 20:21:48
ዛሬ ለፓርላማ የተመራው፤ የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የሚፈቅደው የአዋጅ ማሻሻያ ምን ይዟል? 

የውጭ ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እንዲገቡ የሚፈቅደው የባንክ ስራ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራ። የአዋጅ ማሻሻያው፤ የባንክ አገልግሎት ዘርፍን “ለመምራት፣ የፈቃድ አሰጣጥን ለመወሰን እና ለማስተዳደር” የሚያስችል ሆኖ እንደተዘጋጀ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ሰኔ 7፤ 2016 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው፤ የባንክ ስራ አዋጅ ማሻሻያን ጨምሮ አምስት የአዋጅ ረቂቆች ለፓርላማ እንዲቀርቡ ውሳኔ አሳልፏል።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው አዲሱ የአዋጅ ማሻሻያ፤ የባንክ ዘርፉን “በጥንቃቄ በተዘጋጀ የሕግ እና የቁጥጥር ማዕቀፍ ለውጭ ኢንቨስትመንት መክፈት የዘርፉን ተወዳዳሪነት እና ቅልጥፍና” ያሻሽላል ተብሎ እንደሚታመን ያስረዳል። 

በአዋጅ ማሻሻያ ረቂቁ መሰረት፤ የውጭ ባንኮች “በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በባለቤትነት የሚያስተዳድሩት” ተቀጥላ ባንክ ወይም የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ ወይም የውክልና ጽህፈት ቤት በኢትዮጵያ እንዲከፍቱ ይፈቀድላቸዋል። 

የአዋጅ ማሻሻያው፤ የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ባንኮች ውስጥ የድርሻ ባለቤት እንዲሆኑ ጭምር ይፈቅዳል። የውጭ ሀገር ዜጎች እና የውጭ ንብረት የሆኑ የኢትዮጵያ ድርጅቶች፤ በአንድ ባንክ የሚኖራቸው የአክሲዮኖች ድርሻ 40 በመቶ ብቻ ሆኖ በአዋጅ ማሻሻያ ረቂቁ ተገድቧል። 

ለዝርዝሩ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/13326/

@EthiopiaInsiderNews
14.8K views17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-13 20:04:49
የአያትን አክሲዮን የገዛ ሁሌም ትርፋማ

በ 2015 ዓ.ም 51% ትርፍ /Dividend/ ለባለክሲዮኖች አከፋፍለናል

በቀላል አማርኛ የ 1 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የነበራቸው ባለአክሲዮኖች 510 ሺ ብር ትርፍ /Dividend/ አግኝተዋል

የ 5 ሚሊዮን ብር የገዙ 2.5 ሚሊዮን ብር አትርፈዋል

የአንድ አክሲዮን ዋጋ 100 ብር ነው

ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የአክሲዮን መጠን 2500 ነው

ዝቅተኛ የአክሲዮን ዋጋ 262,500 ብር ፣ 5% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ

ከፍተኛ የአክሲዮን መጠን ገደብ የለውም

40% ከፍለው ቀሪውን በሶስት ዓመት መጨረስ ይችላሉ

አክሲዮኑን ከገዙ ከአንደኛው ወር ጀምሮ የትርፍ ተካፋይ መሆን ይጀምራሉ

ለበለጠ መረጃ:
በ 0912287354 / 0904444670 ይደውሉ

http://t.me/Tsion_won
https://t.me/nvhfjnfdhnojbfedgjn

Whatsapp - https://wa.me/251912287354?text
16.6K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-13 18:31:56
የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በዚህ ፖስት ስር ያስቀመጡት ኮሜንት እያነጋገረ ነው።
17.0K views15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-13 17:57:53
በላይ በቀለ ወያ ተፈቷል። እንኳን ለቤትህ አበቃህ ወንድማለም
16.8K views14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-13 12:04:54
ብሔራዊ ውርደት ነው። የትውልድ ምክነት ነው። ያሳዝናል
7.1K views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-12 18:51:51
“ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ” በእስር ላይ የሚገኙ ሶስት ጋዜጠኞች “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቀረቡ

የተፈጻሚነት የጊዜ ወሰኑ ባለፈው ሳምንት ካበቃው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ ሶስት ጋዜጠኞች፤ “አካልን ነጻ የማውጣት” (habeas corpus) አቤቱታ ለፍርድ ቤት አቀረቡ። አቤቱታውን በጠበቆቻቸው በኩል ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ጋዜጠኞች በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ ናቸው።

ጋዜጠኞቹ አቤቱታውን ያቀረቡት፤ የፌደራል ፖሊስ “ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጣስ በእስር እንዲቆዩ” በማድረጉ መሆኑን ከጠበቆቻቸው አንዱ የሆኑት አቶ አዲሱ ጌታነህ “ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ሶስቱ ጋዜጠኞች “ካለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መያዛቸው”፣ ከተያዙም በኋላ “በ48 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ ሲኖርባቸው” ይህንን መብታቸውን መነፈጋቸውን ጠበቃው ገልጸዋል።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ፤ ጋዜጠኞቹ “ከፍርድ ውጭ ተገድደው የተያዙ” መሆናቸውን ይገልጻል።

የፌደራል ፖሊስ የጋዜጠኞቹን “ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጣስ በእስር ላይ ማቆየቱ ሕገ ወጥ ተግባር ነው” ሲሉም የጋዜጠኞቹ ጠበቆች በአቤቱታው ላይ አመልክተዋል።

ዝርዝሩን ለማንበብ https://ethiopiainsider.com/2024/13301/

@EthiopiaInsiderNews
13.9K views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-12 12:06:56
የጌታቸው ረዳ ጠባቂዎች ተቀየሩ
የፌዴራል መንግሥቱ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ አዳዲስ ጠባቂዎችን እንደመደበላቸው ዘ-ጆርናሊስት ከታማኝ ምንጮች ሰምቷል።

የጌታቸው ረዳ አጃቢዎች መቀየር በሕወሓት እና ጊዚያዊ አስተዳደሩ መካከል ያለውን የሰፋ ልዩነት ያሳያል ተብሏል።

ምንጮች እንደገለጹት፣ "ነባሩ ሕወሓት" በሚባለው እና እርሳቸው በሚመሩት ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል ያለው ልዩነት በፕሬዝዳንቱ ላይ የደህንነት ሥጋት ሳይፈጥር አልቀረም።

የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በቅርቡ በመቀሌ ከተማ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ በህወሓት እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ መካከል ያለው ልዩነት የፖለቲካ ብቻ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሳምንታት በፊት ከትግራይ ክልል ከመጡ ሰዎች ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ባደረጉት ውይይት ደጋግመው "ጌታቸውን አግዙት፤" ሲሉ ተደምጠዋል።
ያልተሰሙ አዳዲስ አለማቀፍና ሀገርአቀፍ ዜናዎችን ለማግኘት ቻናላችንን join አድርጉ
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
16.9K views09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-11 18:58:24
ግንቦት 20 ከካላንደር ላይ ተሰረዘ
#FastMereja
ዛሬ በፓርላማ የፀደቀው የህዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበርን ለመወሰን የወጣው አዋጅ በልማድ ሲከበር የቆየውን ግንቦት 20 ብሔራዊ በአልነቱ አስቀርቷል፡፡

የሰማዕታትን ቀን (የካቲት 12) እና የብሔር ብሔረሰቦች ቀን (ህዳር 29 ) መስሪያ ቤቶች ክፍት ሆነው፤ ታስበው ይውላሉ ተብሏል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሰንደቀ ዓላማ ቀን፣ የመከላከያ ቀን፣ የሴቶች ቀንና ሌሎችም በዓላት ታስበው የሚውሉ ናቸው ተብሏል፡፡

አዋጁ ተከብረው በሚሉ ብሔራዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት ለሕዝብ አገልግሎት ክፍት መደረግ አለባቸው ያላቸውን ተቋማትን ዝርዝር አስቀምጧል፡፡

በዚህም የእለት ከእለት ኑሮ አስፈላጊ የሆኑ የውሃ፣ የመብራት፣ የስልክ እና መሰረታዊ አገልግሎቶች የጤና ተቋማትና መድሃኒት ቤቶች ለሕዝብ ደህንነት አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት ተቋማት የእሳት አደጋ፣ መከላከል አገልግሎትና የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች እንዲሁም ነዳጅ ማደያዎች ክፍት ሆነው እንዲውሉ በአዋጁ ተቀምጠዋል፡፡

ምክር ቤቱ የህዝብ በዓላትና የበዓላትን አከባበር መወሰን የወጣውን ረቂቅ አዋጅ በአንድ ድምፅ ተአቅቦና በአብላጫ ድምፅ አፅድቆታል ሲል ሸገር ሬዲዮ ዘግበዋል።
17.9K views15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-11 15:10:07
የማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ 9 ሰዎችን ያሳፈረ አውሮፕላን መከስከሱ ተረጋገጠ

የማላዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ሳውሎስ ቺሊማን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎችን አሳፍሮ ትናንት ተሰውሯል የተባለው አውሮፕላን መከስከሱ ተረጋገጠ፡፡

በደረሰው የመከስከስ አደጋ ሁሉም ተሳፋሪዎች ሕይወታቸው ማለፉን የማላዊ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ ማሳወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ንብረትነቱ የሀገሪቱ መከላከያ ሃይል የሆነ አውሮፕላን የማላዊ መዲና የሆነችውን ሊሎንግዌን እንደለቀቀ ከራዳር ውጭ መሆኑ ትናንት መገለጹ ይታወሳል።

የአቪዬሽን ባለስልጣናት ከራዳር ውጭ ከሆነችው አውሮፕላን ጋር መገናኘት አለመቻላቸውን ማሳወቃቸውን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ የአውሮፕላኗ ፍለጋና የነፍስ አድን ተግባር እንዲከናወን ትዕዛዝ አስተላልፈው ነበር።

በዚህም መሰረት ትናንት ምሽቱን እና ዛሬ ረፋድ ድረስ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በቺንካንጋዋ ደን ውስጥ ፍለጋ ሲያደርጉ መቆየታቸው ተገልጿል።

በዚህም አውሮፕላኗ ተከስክሳ መገኘቷን ፕሬዚዳንቱ በሰጡት መግለጫ ጠቅሰው፤ በደረሰው አሰቃቂ አደጋ እጅግ ሀዘን ተሰምቶናል ብለዋል።
17.9K views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-06-07 13:56:57
  አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

https://t.me/sellphone2777

  0929008292

inbox @bina27

አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ
11.5K views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ