Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሁሉንም ሃይማኖቶች በእኩልነት ያከብራል ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፌደ | Muktarovich Ousmanova

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሁሉንም ሃይማኖቶች በእኩልነት ያከብራል

ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ ፖሊስ ከየትኛውም ሃይማኖት፣ ብሄር እና ፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዳ እና ብዛህነትን እሴቱ ያደረገ ሕዝባዊ ተቋም መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሃይማኖቶች ብዛህነትን የሚያከብርና የሚያስከብር በእኩልነት ለሁሉም ሙያዊ አገልግሎት የእየሰጠ ያለ ተቋም ሆኖ ሳለ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አዲስ የፖሊስ አባላትን ለመመልመል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ የተላከ የፖሊስ አባል ምክትል ሳጂን ታመነ ዱባለ ጥር 5 ቀን 2016 ኬቾ ወዜ ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያን በመገኘት የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ሃይማኖታዊ መዝሙር በመዘመር እና በሕዝብ ፊት ጥይት እየተኮሰ በማህበራዊ ሚዲያ ሰሞኑን የሚሰራጨው ቪዲዮ ከተቋሙ መተዳደሪያ ህግና አሠራር ውጭ እንደሆነ መግለጫው አረጋግጧል።

አባሉም ይህንን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎት የፈፀመው ድርጊት በተቋሙ ሕገ ደንብ መሠረት በሕግ አግባብ እያጣራ እንደሚገኝ መግለጫው አመላክቷል።

ፖሊስ የሁሉም አገልጋይ ሆኖ ሳላ አባሉ እምነቱን በግል መከተል እየቻለ ነገር ግን መንግስት ፀጥታ እንዲያስከብር ያስታጠቀውን የጦር መሣሪያ ከፍተኛ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ፍፁም የፖሊስን ዲሲፕሊን በጣሰ መልኩ የፈፀመው ተግባር በሕግ የሚያስጠይቅ ስለሆነ ተቋሙ ሕግ ፊት እንደሚያቀርበው በመግለጫው ገልጿል።

አባሉ የፈፀመው ተግባር እውነታው ይሄ ሆኖ ሳለ ከዚህ ውጭ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚራገቡ የተሳሰቱ መረጃዎችን ኅብረተሰቡ እንዳይከተል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ አሳስቧል
ሚያዚያ 16 2016
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ