Get Mystery Box with random crypto!

Muktarovich Ousmanova

የቴሌግራም ቻናል አርማ muktarovichousmanova — Muktarovich Ousmanova
ርዕሶች ከሰርጥ:
Fastmereja
የሰርጥ አድራሻ: @muktarovichousmanova
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 63.74K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopia forever

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-04-24 12:07:18
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሁሉንም ሃይማኖቶች በእኩልነት ያከብራል

ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ ፖሊስ ከየትኛውም ሃይማኖት፣ ብሄር እና ፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዳ እና ብዛህነትን እሴቱ ያደረገ ሕዝባዊ ተቋም መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሃይማኖቶች ብዛህነትን የሚያከብርና የሚያስከብር በእኩልነት ለሁሉም ሙያዊ አገልግሎት የእየሰጠ ያለ ተቋም ሆኖ ሳለ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አዲስ የፖሊስ አባላትን ለመመልመል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ የተላከ የፖሊስ አባል ምክትል ሳጂን ታመነ ዱባለ ጥር 5 ቀን 2016 ኬቾ ወዜ ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያን በመገኘት የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ሃይማኖታዊ መዝሙር በመዘመር እና በሕዝብ ፊት ጥይት እየተኮሰ በማህበራዊ ሚዲያ ሰሞኑን የሚሰራጨው ቪዲዮ ከተቋሙ መተዳደሪያ ህግና አሠራር ውጭ እንደሆነ መግለጫው አረጋግጧል።

አባሉም ይህንን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎት የፈፀመው ድርጊት በተቋሙ ሕገ ደንብ መሠረት በሕግ አግባብ እያጣራ እንደሚገኝ መግለጫው አመላክቷል።

ፖሊስ የሁሉም አገልጋይ ሆኖ ሳላ አባሉ እምነቱን በግል መከተል እየቻለ ነገር ግን መንግስት ፀጥታ እንዲያስከብር ያስታጠቀውን የጦር መሣሪያ ከፍተኛ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ፍፁም የፖሊስን ዲሲፕሊን በጣሰ መልኩ የፈፀመው ተግባር በሕግ የሚያስጠይቅ ስለሆነ ተቋሙ ሕግ ፊት እንደሚያቀርበው በመግለጫው ገልጿል።

አባሉ የፈፀመው ተግባር እውነታው ይሄ ሆኖ ሳለ ከዚህ ውጭ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚራገቡ የተሳሰቱ መረጃዎችን ኅብረተሰቡ እንዳይከተል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ አሳስቧል
ሚያዚያ 16 2016
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
21.3K views09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 21:43:04
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አሜሪካን ይጎበኙ ዘንድ በፕሬዚዳንት ባይደን ግብዣ እንደቀረበላቸው የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ዘግቧል።
22.3K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 15:33:28
ምንድነው የሚባለው?

የደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል የቆዳ ስፔሻሊስት እና የመንታ ልጆች እናት የሆነችው ዶክተር ኤልሳቤጥ በጥይት ተደብድባ ተገድላለች ተብሏል። ገዳይዋ ማንም ይሁን ማን እጅግ አስፀያፊ ድርጊት ነው

እህታችን በሰላም እረፊ
24.0K views12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-23 07:43:20
ኢትዮጵያዊቷ የርቀት ሯጭ እና የኦሎምፒክ የፍጻሜ ተወዳዳሪ ዘርፌ ወንድምአገኝ በአበረታች መድሃኒት ክስ የ5 አመት እገዳ ተጣለባት።

ያለፈው አመት በቶኪዮ ኦሊምፒክ የ3000 ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ውድድር ላይ የደረሰችው እና የአለም ሻምፒዮና መድረክን በጠባብ ልዩነት ያጣችው የኢትዮጵያ ሯጭ ሁለት የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች በሰውነቷ ዉስጥ መገኘቱ በመረጋገጡ ለአምስት አመታት እገዳ ተጥሎበታል።

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ: https://abcnews.go.com/Sports/wireStory/ethiopian-distance-runner-olympic-finalist-zerfe-wondemagegn-banned-109487297
23.6K views04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 13:33:04
➷አስገራሚው መንደር በፍጹም እንዳያመልጣችሁ!!!
ጊዮን ሆምስ የጊዮን ቢዝነስ ግሩፕ አካል
+251921388158
በመሃል ከተማ ሌላ ከተማ እየገነባ ይገኛል።
➷ወሎ ሰፈር መስቀል ፍላወር አጠገብ
50%የባንክ ብድር የተመቻቸለት
90% የተገነባ መንደር አፓርትመንቶች
በ10 % ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት
ይሁኑ
ባለ 1,መኝታ ➷96.5ካሬ
ባለ 2 መኝታ ➷168.9ካሬ
➷144ካሬ
ባለ 3 መኝታ 205ካሬ
ባለ 4 መኝታ 215ካሬ
➷50 አመት በቢዝነሱ ዘርፍ ልምድ ያካበተው
በውስጡ ስምንት እህት ኩባንያዎችን የያዘ
ጊዮን ቢዝነስ ግሩፕ
https://youtube.com/@Modernhouseinethiopia?si=O1OgP4AI7Re2Yv5w
15.7K views10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-21 12:49:50
ቀሲስ በላይ ዶላር ለማጭበርበር የሞከሩት ከአፍሪካ ህብረት አካውንት ነው

" ቀሲስ በላይ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ዉስጥ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመገኘት ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከህብረቱ የሂሳብ ቁጥር ለግንባታ እና ሌሎች ስራዎች ክፍያ በሚል 6 ሚሊዮን 50 ሺህ ዶላር ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ዉስጥ ያለዉ ቅርንጫፉ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት የተከፈተ ሲሆን በዋነኛነት የአፍሪካ ሒሳቦችን በተለይ ለማስተዳደር ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከልን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሪ ክምችት ያላቸዉ አካውንቶችን በማካተት ቁጥጥር ያደርጋል።

ቀሲስ በላይ በወቅቱ ሀሰተኛ የህብረቱ ማህተም ያረፈባቸዉን ወረቀቶች በመያዝ ለግንባታ እና የማሽነሪዎች አቅርቦት በሚል ክፍያዉን መጠየቃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።

ክፍያዉ ከመፈጸሙ በፊት ወደ ህብረቱ የስልክ ጥሪ ያደረጉት የባንኩ ሰራኞች የክፍያዉን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ሲሞክሩ የህብረቱ የፋይናንስ ክፍል የማያዉቀዉ መሆኑን እና ክፍያዉ እንዲታገድ ህብረቱ መጠየቁ መረጃዉ ይደርሳቸዋል።

ህብረቱ ይህንን ተከትሎም ግለሰቡ እንዲያዙለት ጠይቆ ቀሲስ በላይ በህብረቱ ጠባቂዎች በቁጥጥር ስር ዉለዉ በፌዴራል ፖሊስ ተላልፈው መሰጠታቸዉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ እንደተናገሩት "በመሠረቱ ጥሬ ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ ብቻ ሊሰጥ አይችልም ። ለማጭበርበር የሞከረዉም ግለሰብ መጥቶ መጠኑን በጥሬ ገንዘብ ሲጠይቅ ይህን እንኳን አያውቅም ነበር ማለታቸዉን ነዉ።


ሪፖርተር
16.0K views09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 19:56:05
የቡድን ሰባት ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች ይታያሉ ያሏቸው፤ “የማያቋርጡ እና ኃይለኛ ውጥረቶች” እንደሚያሳስቧቸው ገለጹ። በኢንዱስትሪ የበለጸጉት ሰባት አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ ይፈጸማሉ የሚባሉ “የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እና በደሎች ሪፖርቶች”፣ “ብርቱ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ” እና “የምግብ ዋስትና እጦት መስፋፋት” እንዳሰጋቸውም አስታውቀዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በኢትዮጵያ ጉዳይ ስጋታቸውን ያንጸባረቁት፤ በጣልያኗ ካፕሪ ደሴት ያካሄዱትን ስብሰባ ሲያጠናቅቁ ዛሬ አርብ ምሽት ባወጡት መግለጫ ነው። ሚኒስትሮቹ በዚሁ መግለጫቸው፤ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በተፈረመው ግጭት የማቆም ስምምነት አተገባበር ረገድ የተወሰዱ እርምጃዎችን በበጎ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል።

በሰብዓዊ መብቶች እና በሲቪል ሰዎች ጥበቃ፣ ውጥረቶችን ለመፍታት በሚደረግ ፖለቲካዊ ውይይት፣ በዕርቅ፣ በብሔራዊ ውይይት፣ የሽግግር ፍትህ እና በግጭት ወቅት ወንጀል የፈጸሙ ተጠያቂ ለማድረግ ተጨማሪ እና ዘላቂ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ አበረታተዋል። በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በመካሄድ ላይ በሚገኙ ግጭቶች የሚሳተፉ ወገኖች፤ በንግግር ሰላም ለማውረድ ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዲኖራቸው ጥሪ አቅርበዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
14.1K views16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 14:19:03
የአንድ አመት ልጁን ከእነ ህይወቷ ለመቅበር የሞከረው ወላጅ አባት በቁጥጥር ስር ዋለ።
#FastMereja
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፒክተር አለማየሁ አማረ ለክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን እንደገለፁት በወረዳው ኮሶል ቀጭን መንደር ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረው ፀብ ምክንያት የወንጀል ድርጊቱን ለመፈፀም ሙከራ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡

አዛዡ አክለውም በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረ ጊዜያዊ ፀብ እናት የአንድ ዓመት ሴት ህፃን ልጅ ጥላ በመጥፋቷ ወላጅ አባት ቲቲዮስ ኪያግላስ የተባለው ተጠርጣሪ የአንድ ዓመት ህፃን ልጁ እያለቀሰች ስታስቸግረዉ በሁኔታው ተበሳጭቶ የአንድ አመት ልጁን በህይወት ለመቅበር ጉድጓድ ሲያዘጋጅ የተመለከቱ የአከባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ ጥቆማ ይሰጣሉ፡፡

ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተጠርጣሪውን ጉድጓድ እየቆፈረ እያለ በቁጥጥር ስር እንዲውል በማድረግ ህፃኗን ጉዳት ሳይደርስባት መታደግ መቻሉንና በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

ፖሊስ የህፃኗን ወላጅ እናቷን እያፈላለገ ሲሆን ህፃኗ በአሁን ሰዓት ሰሜን ቤንች ወረዳ ፖሊስ እንክብካቤ እያደረገላት እንደሚገኝ የገለፀት ፖሊስ አዛዡ በቤተሰብ መካካል አለመግባባቶች በሚፈጠሩበት ወቅት ችግሩን በመነጋገር መፍታት ይገባል ሲሉ ፖሊስ አዛዡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል ፋስት መረጃ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን መረጃ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
16.5K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 07:29:24
ስልክዎትን ለመቀየር ወይም አዲስ ለመግዛት አስበዋል ?

አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

https://t.me/sellphone2777

0929008292

inbox @bina27

አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ

ክፍለ ሀገር ላላቸሁ ደንበኞችቻችንም በ DHL መላክ ጀምረናል
17.0K views04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-19 07:02:45
ትናንት ማታ በኬንያ መርሳቤት አከባቢ በደረሰ የጄሎኮፍተር አደጋ የኬንያ የመከላከያ አዛዥ ፍራንሲስ ኦጎላን ጨምሮ በርካታ የወታደራዊ አዛዦች መሞታቸው ተገለፀ
16.6K views04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ