Get Mystery Box with random crypto!

የአንድ አመት ልጁን ከእነ ህይወቷ ለመቅበር የሞከረው ወላጅ አባት በቁጥጥር ስር ዋለ። #FastMe | Muktarovich Ousmanova

የአንድ አመት ልጁን ከእነ ህይወቷ ለመቅበር የሞከረው ወላጅ አባት በቁጥጥር ስር ዋለ።
#FastMereja
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፒክተር አለማየሁ አማረ ለክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን እንደገለፁት በወረዳው ኮሶል ቀጭን መንደር ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረው ፀብ ምክንያት የወንጀል ድርጊቱን ለመፈፀም ሙከራ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡

አዛዡ አክለውም በባልና ሚስት መካከል በተፈጠረ ጊዜያዊ ፀብ እናት የአንድ ዓመት ሴት ህፃን ልጅ ጥላ በመጥፋቷ ወላጅ አባት ቲቲዮስ ኪያግላስ የተባለው ተጠርጣሪ የአንድ ዓመት ህፃን ልጁ እያለቀሰች ስታስቸግረዉ በሁኔታው ተበሳጭቶ የአንድ አመት ልጁን በህይወት ለመቅበር ጉድጓድ ሲያዘጋጅ የተመለከቱ የአከባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ ጥቆማ ይሰጣሉ፡፡

ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተጠርጣሪውን ጉድጓድ እየቆፈረ እያለ በቁጥጥር ስር እንዲውል በማድረግ ህፃኗን ጉዳት ሳይደርስባት መታደግ መቻሉንና በተጠርጣሪው ላይ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡

ፖሊስ የህፃኗን ወላጅ እናቷን እያፈላለገ ሲሆን ህፃኗ በአሁን ሰዓት ሰሜን ቤንች ወረዳ ፖሊስ እንክብካቤ እያደረገላት እንደሚገኝ የገለፀት ፖሊስ አዛዡ በቤተሰብ መካካል አለመግባባቶች በሚፈጠሩበት ወቅት ችግሩን በመነጋገር መፍታት ይገባል ሲሉ ፖሊስ አዛዡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ሲል ፋስት መረጃ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን መረጃ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።