Get Mystery Box with random crypto!

በብራዚል በሞተ ሰው ስም ብድር ለመውሰድ አስክሬኑን በዊልቸር ላይ አድርጋ ወደ ባንክ የመጣችዉ ግለ | Muktarovich Ousmanova

በብራዚል በሞተ ሰው ስም ብድር ለመውሰድ አስክሬኑን በዊልቸር ላይ አድርጋ ወደ ባንክ የመጣችዉ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች

የ42 ዓመቷ ብራዚላዊት ሴት ህይወቱ ያለፈ ባለቤቷን ወደ ባንክ አምጥታ በስሙ ከባንክ ብድር ለማዉጣት ስትሞክር በቅርቡ በቁጥጥር ስር ውላለች።

ማክሰኞ ሚያዚያ 9 ቀን ኤሪካ ዴ ሱዛ ቪየራ ኑነስ የተባለችዉ ግለሰብ ህይወቱ ካለፈዉ የ68 ዓመቱ ፓውሎ ሮቤርቶ ብራጋ ስም 3,200 ዶላር የባንክ ብድር ለማዉጣት ወደ ባንጉ፣ ሪዮ ዴጄኔሮ ወደሚገኘው የኢታው ዩኒ ባንኮ ቅርንጫፍ መጥታለች። የአዛውንቱን በዊልቸር ላይ የነበሩ ሲሆን አጎቷ እንደሆኑ እና የመጀመሪያ ተንከባካቢ መሆኗን ተናግራለች። የባንኩ ሰራተኞች ብዙም ሳይቆይ በብራጋ ላይ ከባድ ችግር እንዳለ አስተውለዋል፡፡ምክንያቱም ይህችዉ ሴት የሟችን ጭንቅላት በእጇ ስትደግፍ ጥርጣሬ ፈጥሮባቸዋል። እናም ምንም አይነት በህይወት እንዳለ የሚያሳይ ምልክት አልታየበትም፣ ነገር ግን ቪየራ ኑነስ በተፈጥሮው ዝምተኛ እንደሆነ ለባንኩ ሰራተኞቹ እየነገራቻቸዉ ነበር ተብሏል።

ምንም እንኳን ለምትጠይቀዉ ጥያቄ መልስ የመስጠት አቅም እንደሌለው ግልጽ ቢሆንም አስክሬኑን ልታናግረው ስትሞክር ትታያለች፡፡“አጎቴ እየሰማህ ነው? መፈረም አለብህ። ካልፈረምክ ምንም መንገድ የለም ” እያለች ስትናገር እንደነበር ምስክሮች ኤሪካ ዴ ሱዛ ቪዬራ ኑነስ በዊልቸር ላይ ለተቀመጠዉ አስከሬን ስትናገር ሰምተዋል፡ "ላንተ መፈረም አልችልም፤ማድረግ የምችለውን አደርጋለሁ፤ ተጨማሪ ራስ ምታት እንዳትሰጠኝ ስምህን መዝግብ ስትል ትደመጣለች፡፡

ከባንኩ ሰራተኞች አንዱ "ደህና ነው ብዬ አላምንም" ሲል ይደመጣል፤ቪዬራ ኑኔስ ግን "አጎቷ" ደህና እንደሆነ ትናገራለች ፣ ትንሽ ዝምታ ስለሚያበዛ ነዉ በማለት ለማስተባበል ሞክራለች፡፡

ዳጉ ጆርናል