Get Mystery Box with random crypto!

በመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ፤ በተቆጣጣሪ አካል እንዲወሰን የሚያደርግ አዋጅ | Muktarovich Ousmanova

በመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ፤ በተቆጣጣሪ አካል እንዲወሰን የሚያደርግ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ

በመኖሪያ ቤቶች የሚደረገው የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ላይ፤ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እንዲሁም በክልሎች በሚቋቋም ተቆጣጣሪ አካል በሚወስነው መሰረት እንዲከናወን የሚያደርግ አዋጅ ዛሬ በፓርላማ ጸደቀ። የተቆጣጣሪ አካሉ “የሀገሪቱን ነባራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች” ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ በየዓመቱ ከሰኔ 30 ጀምሮ ለአንድ ዓመት የሚጸና የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርግ በአዲሱ አዋጅ ተደንግጓል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከጸደቀበት ዕለት ጀምሮ ተፈጻሚ የሚሆነው ይህ አዋጅ፤ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደርን ለመደንገግ የተዘጋጀ ነው። በስድስት ክፍሎች እና በሰላሳ ሁለት አንቀጾች የተዋቀረው አዋጁ፤ ስለመኖሪያ ቤት ኪራይ እና ዋጋ፣ ውል የሚቋረጥባቸውን አካሄዶች፣ የተቆጣጣሪ አካል ስልጣን እና ተግባር እንዲሁም የጥቆማ እና ቅሬታ አቀራረብ ስነ ስርዓትን የተመለከቱ ድንጋጌዎችን በውስጡ አካትቷል።

“የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር” የሚመለከተው ይህ አዋጅ ከያዛቸው ድንጋጌዎች መካከል፤ “ነባር የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውልን” የተመለከተው ይገኝበታል። “አዋጁ ከመውጣቱ በፊት በጹሁፍ የተደረገ ማንኛውም የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል፤ በአከራይ እና ተከራይ ስምምነት እንዲቋረጥ ካልተደረገ በስተቀር፤ በአግባቡ መረጋገጥ እና መመዝገብ እንዳለበት” በአዲሱ አዋጅ ላይ ሰፍሯል።

ውሉ መመዝገብ እና መረጋገጥ ያለበት፤ በዛሬው ዕለት በጸደቀው አዋጅ መሰረት የሚቋቋመው “ተቆጣጣሪ አካል” በተሰየመ በ30 ቀናት ውስጥ እንደሆነ በአዋጁ ተቀምጧል። ክልሎች የሚመሰረተው አካል፤ የውል ማረ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር