Get Mystery Box with random crypto!

ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች በፖሊስ ድብደባ እና እስራት ተፈፀመባቸው ተማሪ | Muktarovich Ousmanova

ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች በፖሊስ ድብደባ እና እስራት ተፈፀመባቸው

ተማሪዎቹ የተራዘመ የመመረቂያ ግዜን በመቃወም ሰልፍ የወጡ ሲሆን የትግራይ የፀጥታ ሐይሎች ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እንደፈፀሙባቸው ለዶቼቬለ ተናግረዋል፣ 10 ተማሪዎች ደግሞ መታሰራቸው ተገልጿል።

እንደ ተማሪዎቹ ገለፃ በፖሊስ የሐይል እርምጃ አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸው ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ አሪድ ግቢ ተነስተው ያሏቸውን ቅሬታዎች ለማሰማት ወደ መቐለ ከተማ ጎዳናዎች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት ነው።

ተማሪዎቹ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተገደዱት በተለያዩ ችግሮች ለዓመታት ትምህርታቸው ሲስተጓገል ቆይቶ ዘንድሮ ለመመረቅ እየተጠባበቁ የነበረ ቢሆንም፤ ዩኒቨርሲቲው ሌላ ተጨማሪ ዓመት መማር እንደሚጠበቅባቸው ከተገለፀላቸው በኃላ ነው።

ከሰላማዊ ሰልፉ በፊት ግን ለዩኒቨርሲቲው በተደጋጋሚ ቅሬታ ማቅረባቸውን እና ከዩኒቨርሲቲው ምላሽ አለማግኘታቸውን ገልፀዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ በነበሩበት ወቅትም ጥይት በመተኮስ፣ በድብደባ እና በአፈሳ ፖሊስ ሰልፉን በሐይል መበተኑ ተማሪዎቹ አስረድተዋል።

Source: Deutsche Welle Amharic