Get Mystery Box with random crypto!

ISLAMIC SCHOOL

የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL
የሰርጥ አድራሻ: @islam_and_science
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 18.51K
የሰርጥ መግለጫ

✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 22

2021-01-26 06:24:09 መራራ እዉነት
ክፍል

........ ሰሚራ ሽኩር

.......ሁሉንም አቅጀ አስቤበት ነዉ የመጣሁት ኢንሻአላህ ይሳካል አዎ ይሳካል ደጋግሜ ለራሴ ነገርኩት ባይሳካስ ብየ ስፈራ ይሳካል ብየ ለራሴ እነግረዋለሁ

....በሄድኩኝ በማግስቱ አክብረዉ አረዱልኝ በላሁ ጠጣሁ በጣም ጥሩዎች ናቸዉ። ሱመያም ከአማኔ ከተለየች ቡኋላ ጤናዋ ትክክል እንዳልሆነ ብዙ አጫወተችኝ በታሪኳ አዝና ስትነግረኝ እያለቀሰች ነዉ የምትናገር እኔም ለማፅናናት እየሞከርኩ ግን ሱመያ ባለቤትሽን ማታም አሁንም አላየሁትም የት ሂዶ ነዉ ስል ጠየቋት ሱሚም "የትኛዉ ባለቤቴን ነዉ ሙቷል እያልኩሽ" ስትል መለሰችልኝ ግራ ገባኝ እህ እና አሚር የማን ልጂ ነዉ የአማን እንዳልሆነ አቃለሁ አማኔ እኛ ቤት ከመጣ ሶስት አመት ከምናምን አራት አመት ይሆነዋል አማር አራት አመት ሀያት ስድስት አመት ይሆናታል ሱመያ ሁለት አመት እንደሆናት አይደል አማን የተለያት!..... ሳላቅ በሀሳብ
እድሜ ማሰብ ጀመርኩ

ሱመያም ቆጣ ኮስተር ብላ ስታዳምጠኝ ነበር "እንዴት አወቅሽ እንዴት ማን ነሽ አንች !...." አፋጠጠችብኝ ልሸዉዳት ሞከርኩ አልቻልኩም ደጋግማ በጥርጣሬ መመልከት ጀመረች የሆነ የደበቋት ነገር አንዳለ ግልፅ ነዉ እሷም አሚርን ባል የለኝም እያለችኝ ከማን ወለደችዉ ማወቅ እፈልጋለሁ ምን አልባት ከሙሀመድ ይሆን ስል አሰብኩ ኧረ የማይታሰብ ነዉ እንዴት የባሏን ወንድም አግብታ አይ አይሆንም ከራሴ ጋር መከራከር ጀመርኩ ሱመያም እንዴት ላቅ እንደቻልኩ ንገሪኝ ብላ አፈጠጠችብኝ ምን ልበላት አማኔ ነዉ የነገረኝ ከዛስ የማይሆን ነገር ነዉ


....የሷን መልስ ለመመለስ የግድ አሚርን ከማን እንደወለደችዉ ማወቅ አለብኝ አሚርን ከማን ወለድሽዉ ብየ ጠየኳት ከዛ እኔ ደግሞ እንዴት ላቅ እንደቻልኩ እረግርሻለሁ አልኳት

ሱሚም "አሚሬን የወለድኩት ከአማን ነዉ" ብላ ግግም አለች ባላቅ ጥሩ እሱ በአንደበቱ አንድ ሴት ልጂ ብቻ እንዳለዉ ነግሮኝ እሷ ትዋሸኛለች እንዴ!
ሱሚ አትዋሽኝ ከአማን አንድ ልጂ ብቻ ነዉ ያላቹህ ስል አፈጠጥኩባት
ረጋ ብላ "አላህ በተአምሩ ሁለት አረገልኝ አንድ ከወንድ አንድ ደግሞ ከሴት አሚር ያልኩትም ስሙን ስጠራ ሁሌም አማኔን እንዳስታዉስ አጠገቤ እንዳለ እንዲሰማኝ ብየ ነዉ"

.... መልኩን እስኪ አይዉ ብላ ወደኔ ጠጋ አደረገችዉ አማኔን ይመስላል ግን እንዴት አሰብኩ ምን አልባት እርጉዝ እኔደሆነች ይሆናል አማኔ እንደወጣ የቀረ ግን አማኔ ለምን አልነገረኝም ስል አሰብኩ ሱመያም ንግግሯን ቀጠል አድርጋ እንደገመትኩት "የሁለት ወር እርጉዝ እንደነበርኩ ነዉ እኔም እሱም እርጉዝ እንደሆንኩ ሳያቅ ሳላቅ እንደወጣ የቀረ ብዙ ሰዎች በመኪና አደጋ እንደሞተ እንደቀበሩት ነግረዉኛል"

አቤት ይሄ ህዝብ ግን ዉሸቱ መቸ ይሆን የሚለቀዉ ስል አሰብኩ ያላየዉን አየሁ ፤ያልሰማዉን ሰማሁ ፤ያልበላዉን በላሁ፤ የሌለዉን አለኝ፤የማያቀዉን አቃለሁ፣ ያልሆነዉን ሆንኩ፤ያልቀበረዉን ቀበርኩ....
አቤት አረ ሸም ነዉ!!!!
....ለነገሩ እኔስ የምር የአክስት ልጂ ሁኜ ነዉ እንዴ የአክስት ልጂ ነኝ ያልኩ!

.....እሽ ከዛስ ሱመያ ንግግሯን ቀጠለች "እርጉዝ መሆኔ የተነገረኝ ቀን አማኔ ሆስፒታል ሊያስመርቅ የሄደ ቀን ነበር ደስ አለኝ ሰርፕራይዝ ለማድረግ ሽር ጉድ ብየ ኬክ ሰርቸ፤ቡናየን አፍሎቸ፥ምግብ አብስየ፤ቤቴን አፅድቸ...ዉብ ሁኘ ብጠብቀዉ ብጠብቀዉ ቀረ በስልክ እንዳልነግረዉ አልፈለኩም የመጨረሻ ቀን ያናገረኝ ራት በላሽ ብሎ የደወለልኝ ምሽት ነበር የእሁድን ምሽት በሂወቴ መቸም አረሳትም የአማኔን የመጨረሻ ድምፅ ሰምቸባታለሁ ከሱ ቡሀላ ብዙ ባል ጠየቀኝ ማግባት አልፈለኩም ቤተሰቦቸ እንኳን ልጆችን እኛ እናሳድግ አንች አግቢ ብለዉ በተደጋጋሚ ይጨቀጭቁኛል እኔ ግን ቃል አለኝ ሁሌም ላንለያይ ከአማኔ ጋር ቃል ተግባብተናል!በዱንያ ሞት ቢለያየን በአሂራ በጀነት እንገናኛለን ኢንሻአላህ!" እንባዋን መቋቋም አልቻለችም

....አዛዘነችኝ ምን ልበላት ደሞ ደስ አለኝ የአማኔ አንድ ሴት አንድ ወንድ ልጂ አለዉ እንዴት ይደሰት እነዚህን የመሳሰሉ ቆንጆ ልጆች ሲያይ ብየ አሰብኩ

"እሽ አንችስ እንዴት ልታቂ ቻልሽ በአላህ ምንም እንዳትዋሽኝ ንገሪን" አለችኝ
.....የመጠዉ ይምጣ በፍቅር አራት አመት ሙሉ ተሰቃይታለች እሱም ተሰቃይቷል ከዚህ ቡሀኋ ግን ማልቀስ በናፍቆት መሰቃየት....ይበቃል ብየ ለመናገር ወሰንኩ ደሞ አሜኔ እንዳትናገሪ ብሎ ደጋግሞ አስጠንቅቆኛል በዚህ አሷ በአላህ እንዳትዋሽኝ ሁሉንም ንገሪኝ ትለኛለች ምን ይሻለኛል? ልናገር ወይስ አልናገር

.........ብዙ ሳስብ ቆይቸ መናገርን መረጥኩ እዉነታዉ ቢያስደነግጥ ቢመርም እዉነትና ዉሸት እያደረ ይገለፃል አይደል የሚባለዉ ቢመርም አማን በሂወት እንዳለ አብዶ በቅርብ ጊዜ እንደተሻለዉ እዚህም እንድመጣ ያረገ እሱ እንደሆነ በዝርዝር አንድም ሳላስቀር ነገርኳት አላመነችኝም "የኔ የኔ አአአአአማን በበሂወት አለ" አለችኝ አወ በሂወት አለ አልኳት
"የት እንዴት ማለቴ እሽ እርግጠኛ ነሽ የኔ አማን በሂወት አለ"አናዘዘችኝ
አወ አለ ደጋግሜ አማን በሂወት አለ ስል ነገርኳት የዚህን ጊዜ በጩኸት አማኔ የኔ አማን በሂወት አለ በሂወት አለ አማን አልሞተም"እያለች ቀወጠችዉ
"እሽ የት ነዉ ነይ ነይ አማኔ ላይ እንሂድ የኔን አማን አሳይን" ከተቀመጥኩበት ጎትታ አስነሳችን ቆይ ተረጋጊ እኔን በሂወት እንዳለሁ እንዳታቅ ብሎኛል ብየ ነገርኳት "ለምን እኔን አይወደኝም እኔ እስከዛሬ በፍቅሩ መቃጠሌን አያቅም ዉሸታም አይልሽም አማኔን አቀዋለሁ አይልሽም ነይ አሳይኝ ነይ"
..... እንደብድ የምታደርገዉን አታቅም ፀጉሯን ለራሱ በሂጃብ አልሸፈነችዉም ምን ልበላት እንዴትስ ብየ ላረጋጋት ግራ ገባኝ ታለቅሳለች ትስቃለች ድብልቅልቅ ያለ ስሜት እኔ እሷን ወስዶ ማገናኘት አላቃተኝም ነገር ግን አማኔ የHiv በሽተኛ ነዉ መገናየት አይችሉም ቢገናኙ የባሰ ጉዳት ነዉ ጨነቀኝ አማኔ የHiv በሽተኛ ነዉ ብየ እንዳልነግራት እንዴት ብየ ግን ደግሞ እንድትረጋጋ የግድ መናገር አለብኝ ተናግሬ አማኔን ማየት አለብኝ ካለች ትየዉ አላይም ካለችም ግልግል ነዉ ልጆቹ አባታቸዉን አሳይቸ እመልሳለሁ በቃ ልንገራት ብየ

ሱመያ አንድ መራራ አዉነት አለ ልብ ብለሽ ስሚኝ የምነግርሽን ሰምተሽ አማኔን ለማየት ዝግጁ ከሆንሽ ነገ በጠዋት ልጆችሽን ይዘሽ አማኔን አሳይሻለሁ የምነግርሽን እዉነት ሰምተሽ ለመሄድ ፍቃደኛ ካልሆንሽ ልጆችን ወስጀ ለአማኔ አሳይቸዉ እመልስልሻለሁ ተስማምተሽ ቃል ጊቢና ልንገርሽ አልኳት እሷም ደንግጣ አይኖን አፍጥጣ "ምን መራራ እዉነት ነዉ አማኔ ምን ሆነ ደህና አይደለም እንዴ አማኔ ምን ሁኖ ነዉ!?" ብላ ጠየቀችኝ አብሽሪ ከስንት የመከራና የስቃይ ጊዜን አልፎ ለጤናዉ በቅቷል አልሀምዱሊላህ አልኳት "ደህና ከሆነ ምን መራራ እዉነት ነዉ እሽ ንገሪኝ ቃል እገባልሻለሁ "


.....ንግግሬን ቀጠልኩ ያኔ አማኔ ከአንች ቤት ወደሚመረቀዉ ሆስፒታል የሄደ ምሽት ....ምን ብየ ልተንፍስ አይን አይኖን ማየት ጀመርኩ "እ የሄደ ምሽት ምን" ለማወቅ ጓጉታለች
የሄደ ምሽት አንችጋ ራት እንደበላሽ ሊጠይቅ ሲደዉልልሽ ምግብና መጠጡን ሲስተር ሀዋ ነበረች ያቀረበችለት ከዛ...

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot

በአላህ ፍቃድ የመጨረሻዉ ክፍል






Join
https://telegram.me/Islam_and_Science
7.9K views03:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-25 06:12:43 መራራ እዉነት
ክፍል

........... ሰሚራ ሽኩር

......ምን አልባት ናፍቆቱ ይሆናል እንዲህ ያጠቆራት እያልኩ ሳስብ ማን ነሽ?ማንን ፈልገሽ ነዉ የመጣሽ ? ስትል ጠየቀችኝ ማን ልበላት ምን ልመልስ ግራ ገባኝ
.....እእእእእ ያማን ያማን ምንልበል በቃ ያማን ዘመድ ነኝ ብየ ብገላገልስ አልኩና እዉነት ለመናገር ልክ እንደህቴ እንደሪሁየ የለለ አስመሳይ ነኝ እንድታምነኝ የአማን ዘመድ ነኝ
ዉይ አታቂኝም እንዴ የአክስቱ ልጂ ነኝ አማኔ ካየኝ ያቀኛል አማኔን ጥሪልኝ እሱን ለአንድ ጉዳይ ፈልጌዉ ነዉ አልኳት

.... ልብ አለማለቷ ነዉ እንጂ ዉሸቴን እንደሆነ ትንሽ ይለይ ነበር ያዉ መንተባተብ ፊቴን ማላብ እየዋሸሁ መሆኑን ያስታዉቃል።
እሷም "አማኔ አማኔ...." ምን ትበለኝ አይ የታመመዉን ማገገም የተሳነዉን ቁስሏን ነከሁኝ መሰል ከአይኖቿ እንባ እየወረዱ እዝን ብላ "ለመሆኑ አንች ማን ነሽ" ስትል ጠየቀችኝ ስሜ ሀናን ይባላል አልኩና ዘመድ መሆኔን እንድታምን አማን ስለዘመዶቹ የነገረኝን ታሪክ አጣፍጨ ነገርኳት እሷም እዉነት ዘመድ ብትሆንነዉጂ ይሄን ሁሉ ታሪክ ከየት ታቃለች እያለች የምታስብ ትመስላለች ዘመድ መሆኔን እርግጠኛ ስትሆን ነይ ግቢ ወደቤት ብላ ካስገባችኝ ቡኋላ ምግብ አቀረበችልኝ አይ ሱሚ በልተሽ መሞቱን ብታቂ ይሻላል በበዶ ሄድሽ ሀዘኑን አትችይዉም ብላ ይሆን ስል አሰብኩ መቸም በሂወት እንዳለ አታቅም ማን ይነግራታል! አይ እዱንያ ፈተናሽ መብዛቱ ኑሮሽ መምረሩ አታላይ የዉሸት ኑሮ ደስታሽ ትንሽ ሀዘንሽ ብዙ ዉስብስብ መራራ ኢጭ!!!


....ለማንኛዉም የመጠሁበት አላማ ሊሳካ ነዉ መሰል አላቅም ወደ ሱሚ ጠጋ አልኩና አማኔ አይመጣም እንዴ እስኪ ደዉይለት እኔ ለመሄድ እቸኩላለሁ ጉዳይ አለብኝ አልኳት ሱሚም "እእእእእእ እማኔ አማኔ.." እንባዋ እንደጎርፍ መዉረድ ጀመረ ምን ብላ ትንገረኝ ሆስፒታል ሊያስመርቅ እንደወጣ አልመጣም ወይስ ሞተ ብላ ግራ በተጋባ በናፍቆት በተቆራረጠ ድምፅ "ሀናን አማኔ ሀናን አማኔ በሂወት የለም! ከዚህ የተሻለ ቦታ ሂዷል በቃ ሙቷል አማን ሞተ አማን ጥሎን ሄደ" ....እሪ ብላ ማልቀስ ጀመረች

....ወይኔ ጉዴ ምን ልበል እኔዉ እንድትነግረኝ ጠይቄ እኔዉ ደነገጥኩ ሙቷል ብላ ነዉ ያሰበች ለነገሩ እንደዚህ እየተዋወዱ በሂወት ቢኖር ጨክኖ ሳያየኝ ከኔ እርቆ መኖር አይችልም ብላ ስለምታስብ ነዉ ሙቷል የምትል
እይ መኖሩን ባወቅሽ ስል በዝነት አየኋት በፍቅር እንደተጎዳች ማንም አይቶ ይመሰክራል።

እኔም ወደድኩት እላለሁ አይ ሀናኔ ሱመያን ሳያት ፍቅር ምን አንደሆነ ገባኝ ጠቁራለች በሱ አሳብ በአማኔ ናፍቆት ይሆናል ሚስኪን እያልኩ ሳስብ በአንዴ ፊቴ ተቀያየረ በጣም ተናደድኩ ደነገጥኩ ግራ ገባኝ

.......አንድ በግምት ስድስት አመት የሚሆናት የምታምር ህፃን "ኡሚ ኡሚየ" እያለች የተቀመጥንበት ክፍል መጣች አማኔን ነዉ የምትመስል ሱሚም እንባዎቿን ጠራርጋ "መጣሽልኝ ሀያቴ" አለችና መጣሁ ብላ ወደ ዉስጥ ገባች ትንሽ ቆይታ "አይዞሽ ተጫወች ሙሀመድ ላይ ደዉየለታለሁ አሁን ይመጣል" ..... ለወሬዋ ቦታ አልሰጠሁትም ያችን ህፃን እየተመለከትኩ የአማኔ ልጂ ናት ወይስ ብየ አሰብኩ አወ የአማኔ ልጂ ናት እሱን ነዉ የምትመስል አልሀምዱሊላህ

አይ አሁን የአማኔ ወንድም ከመጣ ጉዴ ፈላ በቃ ዘመዳችን አይደለችም ይል ይሆን ቢል በማስመሰል ተክኛለሁ ማሳመን አይከብደኝም ስል ራሴን አረጋጋሁ ከቆይታ ቡሀላ አንድ የአራት አመት ልጂ እየወደቀ እየተነሳ እኛ ወዳለንበት ሳሎን ቤት መጣ አሚሬ ተነሳህ የኔ ልጂ አለችና አቅፋ ምግብ መስጠት ጀመረች

....ያረቢ ምን እየሆነ እንዳለ ግራ ገባኝ ቆይ አግብታ ነዉ ስል አሰብኩ ለነገሩ አራት አመት ሙሉ ሳታገባ እሱን መጠበቅ ከባድ ነዉ እንኳን አገባች አማን በሂወት እንዳለ ብነግራት ትዳሯን ማበላሸት ነዉ ለነገሩ አማን በሂወት እንዳለ ብታቅ የHiv በሽተኛ ስለሆና የመገናኘት እድላቸዉ 0% ነዉ........ ብዙ አሰብኩ

.... እንዲሁ ሳስብ የቤት መኪና ይዞ የአማን ወንድም ሙሀመድ መጣና ተተዋወቅን ነጋዴ ነዉ አማን እንዳለዉም ሙሀመድ ትንሽ ጠቆር ማለቱ ነዉ ከአማን የሚለየዉ እንጂ መንታ ነዉ የሚመስሉት።
.....ዘመዳቸዉ እንደሆንኩ ሱመያ ነገረችዉ
ዘመዳችን አይደለችም ይላል ብየ በፍራት አይን አይኑን ሳይ "እይ የኔ ነገር ሁሌም ስራ ስለምዉሉ ዘመድ ይኑረን አይኑረን የማቀዉ ነገር የለም በይ ተንግዲህ እንደዋወላለን አትጥፊ" ብሎ ስልኩን ሰጠኝ ።

.... አልሀምዱሊላህ በጣም ጨንቆኝ ነበር
በቃ ልሂድ እየመጣሁ እዘይራቹሀለሁ ብየ ተነሳሁ ምን አደርጋለሁ የሱመያን ባለቤት ለማወቅ ለማየት ጓጉቸ ነበር ብጠብቅ ብጠብቅ አልመጣም ጊዜዉም እየመሸ መጣ ልሂድ ብየ ተነሳሁ አይቻልም አሉኝ ለነገሩ እኔም የአማኔን ልጂ ሳልይዝ ከዚህ ቤት አልወጣም እንደዉ ላስመስል ብየ እንጂ

ግን እሽ ብለዉ ቢሸኙኝ ወዴት አድር ነበር ቢሸኙኝ አባቢ ወንድም ቤት አድር ነበር ሁሉንም አቅጀ አስቤበት ነዉ የመጣሁ ኢንሻአላህ የመጠሁበት አላማ ይሳካል

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot


በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
8.1K views03:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-24 06:52:12 መራራ እዉነት
ክፍል

..... ሰሚራ ሽኩር

...አማኔ ማልቀስ ጀመረ በዚህ ጊዜ ሱሚ አግብታ ወልዳ ጥሩ ሂወት እየኖረች ይሆናል።
ወይም ቃሌን ብላ እኔን በተስፋ እየጠበቀችኝ ይሆናል ብቻ አላህየ የሱሚን ነገር አደራ አንተዉ ከክፉ ነገር ጠብቅልኝ ያረብ እያለ እጁን ወደ ላይ ወደ ጌታዉ አነሳ...

....... ለማመን የሚከብድ መራራ እዉነት ሆነብኝ ታሪኩ ከልቤ አዘንኩ አሁን ይሄ ሚስኪን ምን አደረገኝ ብላ ነዉ አጠጥታ እንዲያብድና የ Hiv በሽተኛ እንዲሆን ያደረገችዉ እንደዛ ሰዉ ሁሉ ሲርቃት አማኔ ስለቀረባት ወይስ ስላገባና ስለወለደ ቅናት...ነዉ እንዲህ እንድትጨክን ያደረጋት ብታቀዉ ነሮስ አማኔ ለሷ ከወንድም ከሁሉም በላይ ነበር ምን አይነት ጭንቅላት ቢኖራት ነዉ ይሄን ያሳሰባት ያረብ አሁንም የስራወን እንዳታጠዉ አምርሬ ረገምኳት በዚህ ስሜቴ አጠገቤ ብትሆን ብየ አሰብኩ የምገላት መሰለኝ

...እና የአማኔ ማበድ ስበቦ እሷ ነበረች ማለት ነዉ እሷን ብሎ ዶክተር ገደል በገባች ምናለ በሂወቴ አንዴ አግኝቻት በሰደብኳት...ከራሴ ጋር አወራ ጀመር

አማኔ ግን መጨረሻዉ ምን ይሆን ቤተሰብን አይፈልጋቸዉም እንደዉም በሂወት እንደሌለ ሰዉ በፍቅራቸዉ መጎዳትን ይመርጣል እነሱ እሱን ካዩ ቡሀላ የሚጎዱ ይመስለዋል ብቻ ዉስብስብ ነዉ በዛ ላይ አማኔ የHiv....በሽተኛ ነዉ አሁን አላህ ብሎትስ ቢገናኙ ብየ አሰብኩ አይ ባይገናኙ ይሻላል ከተገናኙ ሁለቱም ይጎዳሉ አልኩ።
... ግን ምኑ ይታወቃል የሚፈጠረዉ ነገር አይታወቅም!
ቢያንስ የአማኔን ልጂና ሚስቱን እኔ ባቃቸዉና ለአማኔ ልጁን ባሳየሁትና በተደሰተ ስል አሰብኩ ግን እንዴት ከአማኔ አድራሻቸዉን ልቀበል ብዙ መፍትሄዎችን አሰብኩ ነገር ግን ምንም መፍትሄ አላገኘሁም ምን ዝም ብየ ብጠይቀዉ አልናገርም ሊለኝ ነዉ እንኳን ያሉበትን ሀገር ታሪኩንስ ነገረኝ አይደል ስል አሰብኩ.....


አማኔ ግን በፊት የት ሆስፒታል ነበር የምትሰራ ልጂህና ሚስትህስ የት ነቸዉ ያሉት ስል ጠየቁት አማኔም ቆጫ ብሎ "ምን ያድርግልሻል እኔ በሂወት እንዳለሁ አንድም ሰዉ እንዲያቅ አልፈልግም በቃ ተይኝ ሳልፈልግ ታሪኬን ነግሬሻለሁ ከዚህ በላይ ግን አልችልም በቃ አልችልም"
... እያለቀሰ በእዝነትና በልቅሶ ብዛት በደከሙ አይኖቹ አስተዛዝኖ ነገረኝ
እኔም ኧረ አማኔ አብሽር እኔም እንድትገናኙና አንድ ላይ ላትሆኑ ተያይታቹህ እንድትጎዱ አልፈልግም! ደሞኮ አማኔ እስከዛሬ ሱሚም አግብታ ወልዳ ይሆናል እንደዉ ልጂህን ማግኘት ብችልና ይዠልህ ብመጣ....ብየ ነበር በቃ ተወዉ ብየ አዝኘ ተነሳሁ


.....አማኔም በልጁ ናፍቆት ስለተጎዳ ሂጀ ይዠለት የምመጣ መሰለዉ አቅማማና "እንግዲያዉስ ማግኘት ከቻልሽ በአካል ማምጣት ሞክሪ ግን ሱሚ ልጆን ስጣጠዉ እንዳትጎዳብኝ ደሞ አንድም ነገር ስለኔ ሳትተነፍሽ በሆነ ነገር አታለሽ/ምክንያት ፈጥረሽ ለአንድ ቀን ብቻ የልጀን አይን ልየዉ በአካል ካልቻልሽ ደግሞ ፎቶቸዉን ልለምንሽ ምን ያህል እንደናፈቁኝ ብታቂ"....

አንተ ብቻ ያሉበትን ቤታቹህን ንገረኝ ብየ አድራሻ ተቀበልኩት አባቢን በሶስት ቀናት ዉስጥ እንደምመለስ ነግሬዉ ፈቅዶልኝ እማየ መርቃ ሁሉም በደስታ ሸኙኝ

....ሱሚንና ልጇን ላግኛቸዉ አላግኛቸዉ የማቀዉ ነገር የለም በዛ ላይ ሱሚ አግብታ ይሆን ....ጨነቀኝ እሽ ባገኛቸዉስ ምናቹህ ነኝ እላቸዋለሁ ምን ብየስ የአማንን ልጁን ይዠለት እሄዳለሁ ተወሳሰበብኝ ያረብ!አንተዉ አቅልልልኝ ብየ ዱአየን አደረኩ።

....ያለኝ ሀገር ያለኝ ቦታና ቤት በነገረኝ መሰረት ሄድኩኝ ቤቱ ተደራራቢ ሶስት ፎቅ ነዉ አይ ቤቱን ተሳሳትኩ መሰል ብየ ተመለስኩ በድጋሚ የሰጠኝን አድራሻ ሳይ አልተሳሳትኩም ቤቱ የራሱ ነዉ ተገረምኩ አማኔ በጣም ሀብታም ነበር ማለት ነዉ ስል አሰብኩ

....ቁሜ ብዙ ካሰብኩ ቡሀላ በሩ ላይ የተገጠመዉን ደዉል ነካሁት ወድያዉ ቆንጂየ ልጂ በሩን ከፈተችልኝ ሱሚ ያላት መሆኖን ለማወቅ ጊዜ አልፈጀብኝም እንዳላትም አፍንጫዋ ቀጥ ያለ ቀጠን ያለች የምታምር እንስት ናት ግን ቀይ አይደለችም ትንሽ ጠቆር ያለች ነበረች...ምናልባት ናፍቆቱ ይሆናል እንዲህ ያጠቆራት እያልኩ ሳስብ "ማን ነሽ ማንን ፈልገሽ ነዉ የመጣሽዉ!" ስትል ጠየቀችኝ ማን ልበላት ምን ልመልስ....

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
7.0K views03:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-23 05:46:05 መራራ እዉነት
ክፍል

....... ሰሚራ ሽኩር


.... ከሱሚ ጋር በፍቅር አብረን መኖር ጀመርን ያየን ሁሉ ይቀናብን ነበር በጣም እወዳታለሁ እሷም ትወደኛለች አምናታለሁ ታምነኛለች ሁሌም በምንም ተአምር ላንለያይ ዘመን በማይሽረዉ በጌታችን ቃል ምለናል
....ከህመሟ ልታደጋት ብጠጋት በፍቅሯ ሳበችኝ የአላህ ነገር ይገርመኛል ሂወቴን ፤ህልሜን አጠለሹት ብላ ስታማርር አላህ ሰበብ አድርጎ አገናኘን በርግጥም የኛ ጌታ የተሻለ ነገር ሊሰጠን እንጂ እኛን በምንም ነገር አይጎዳንም !
.....ከሱሚ ጋር ከተጋባን በሁለተኛ አመታችን እኔ የሴት ልጂ አባት ሱሚ የሴት ልጂ እናት ለመሆን በቃን ቤታችን ይበልጥ ሞቀ በደስታ ደመቀ ሴት ልጂ በመሆኖ በጣም ደስ አለኝ የናቴ ምትክ !

.....አሁን እየጨነቀኝ የመጣ የሲስተር ሀዋ ነገር ነዉ ምኗንም ማወቅ አልቻልኩም በቃ ስታየኝ እንደደመኛዋ ነዉ
ሱሚን ለማየት እንኳን ፍቃደኛ አይደለችም ለምን?አላቅም
ያች የማቃት የዋህ ለሰዉ አዛኟ ሲስተር ሀዋ አልመስልህ አለችኝ

በዚህ መሀል ግራ ገብቶኝ ሱሚ በወለደች በሁለት አመቷ ሲስተር ሀዋ ከድሮዉ ይበልጥ ትቀርበኝ ጀመር አይዞህ ሚስትህ ስለወለደች ብቻዋን እንዳትሆን ሂድላት ያንተን ተራ እኔ እሸፍንልሀለሁ" ትለኝ ጀመር እኔም የዋህነቷ እየገረመኝ ይበልጥ እየቀረብኳት ሄድኩ ከለታት በአንዱ ቀን የኛ ሆስፒታል ሌላ ሀገር ቁጥር ሁለት ሆስፒታል አስገንብቶ ለሁላችንም ጥሪ ተገደረልን እኔ ደግሞ የሆስፒታሉ ዋና አስተባባሪ ስለነበርኩ መቅረት አልችልም ለመሄድ ወስኘ በማግስቱ እንደምመጣ ለሱሚ ቃል ገብቸላት እሷም በስስት አይኖቿ እየተመለከተች ስማ ሸኘችኝ እኔ ከሲስተር ሀዋና ከሌሎች ጓደኞቸ ጋር ስንጓዝ ዉለን ቀን ወደ ሰባት ሰአት አካባቢ ድክም ብሎን አዲሱ ሆስፒታል ደርሰን ወደ ዉስጥ ገባን ሻዉር ወስደን አዲሱን ሆስፒታል ስንጎበኝ ቆይተን በስብሰባዉ ታድመን ፕሮግራሙ ስናከብር ካመሸን ቡሀላ የራት ግቤዣ ነበረን ብዙ መጠጦችና ብዙ ምግቦች በየአይነት ቀርበዋል ሲስተር ሀዋ ከሁል ጊዜዉ በተለየ ዘንጣ ተዉባ የራት ግቢዣዉ ላይ መጣችና አጠገቤ ተቀመጠች ከዛ መጣሁ ብየ ሱሚ ላይ ደዉየ ራት እንደበላች ካረጋገጥኩ ቡኋላ እኔም ልበላ ወደ ተዘጋጀዉ ማአድ አቀናሁ ሲስተር ሀዋ ምግቡንም መጠጡንም ከምን ጊዜዉ በሰሀኔ አድርጋ እንደጠበቀችኝ አላቅም እኔ የተቀመጥኩበት የነበረዉ ወንበር ላይ ተቀምጧል ከዛ ብላ እያለች ሰሀኑን ወደ ጠረፒዛየ አስጠጋችልኝ መጠጡንም/የተከፈተ እስፕራይት ጠጣ አያለች ሰጠችኝ እኔም ስበላ ስጠጣ ስስቅ ስጫወት አምሽቸ ነበር"

እማየ እኛ ወደተቀመጥንበት ክፍል መጣችና" በፈገግታ ሀናኔ እስካሁን ወሬቹህን ናፍቆታቹህን አልተወጣቹህም እንዴ?" አማኔን በአይኑ እንባዎች ሞልተዋል የሆነ የሚያሳዝን ነገር እየነገረን መሆኑ ገብቷት ነዉ መሰል "ዊይ በሉ ተጫወቱ ቤቱን ታፀጂዋለሽ ብየ ነበር በቃ ተይዉ እኔ አፀደዋለሁ ባይሆን ዝም ብለሽ ከምትቀመጭ የአባትሽ ልብሷች በሻንጣ እንደሆኑ ናቸዉ ደሞ አልታጠፉም ቁምሳ ሳጥኑ ላይ አጣጥፈሽ ክተችለት የአማኔም አብሮ አለ የታጠበዉንና ያልታጠበዉን ለይዉ ከአ.አ እንደመጣ ማንም አላስተካከለዉም" አለችኝ እኔም አማ ችግር የለዉም ቤቱን ላፅዳና አጣጥፌ ቦታዉ እመልሳለሁ አሁን ግን ቆይ አልኩ የአማኔን ታሪክ ለመስማት በጓጓ አንደበቴ እማ እሽ መቸ ስትል ጠየቀችኝ ትንሽ ብቻ ጠብቂኝ "ሀናኔ አሁን ጓረቢቴቸ አማንን ሊያዩ ይመጣሉ በቃ አንች ልብሱን ከሻንጣዉ አዉጥተሽ አጣጥፊዉ ቤቱን እኔ አፀደዋለሁ አለችኝ ወይ እማ እኔ አፀደዋለሁ አ.አ ይዘዉት የሄዱትን ሻንጣ ከሳሎን ቤት ይዘዉ መጣችና ሰጠችኝ አማኔ አንች አጣጥፈሽ እስከምትጨርሽ እኔ ኡዱ ላድርግ ስመለስ ታሪኩን እጨርስላቹሀለሁ እያለ ወጣ አይኑ አብጧል ፊቱ ፍም መስሎል ለማየት ያስፈራል እኔም ግራ ገብቶኝ እሽ ቶሎ ተመለስ እንጠብቅሀለን ብየ ልብሱን ከሻንጣ እያወጣሁ አጣጥፌ ወደ ቁምሳጥኑ ማስገባት ጀመርኩ


......ከመሀል አንድ የተጠቀለለ ፌስታል ላይ አይኔ አረፈ አይ አባቢ ይሄን ደግሞ ምን ሊያደርግ ይሆን ሻንጣ ዉስጥ ያስገባዉ ደግሞስ ምንድን ነዉ ብየ ፌስታሉን ስከፍተዉ የአማኔ መድሀኒት ነዉ ኧረረ የአማኔ መድሀኒት ተቀይሮል በፊት ነጭ የሽሮብ የምትመስል እቃ ዉስጥ ነበር መድሀኒቱ ያለዉ አሁን የራሱ ማሸጊያ እንደማንኛዉም አይነት መድሀኒት ነዉ እስኪ ብየ መድሀኒቱን ከጀርባዉ ከግልባቡ ሳነበዉ ግማሹ የአእምሮ ግማሹ የHiv ነዉ የሚለዉ መቸም የህክምና ተማሪ መድሀኒት ሲያይ መድሀኒቱን ለማወቅ እጁን ይበለዋል ከዛ ግራ ገባኝ አባቢ ተሰስተዉ ሰጠዉት ይሆናል ብየ መድሀኒቱን ይዤ ወደ አባቢ እሮጥኩ ሂጀ ነገርኩት አባቢ በኔ ማስተዋል ይደሰታል ብየ ስጠብቅ ያላሰብኩትን ለመዋጥ የሚከብድ ለማመን የሚያስደነግጥ መራራ እዉነት ነገረኝ እንደ
እንጨት ደርቄ ቀረሁ ማመን አቃተኝ ለካ ሰዉነቱን የሚያጥበዉ መድሀኒቱን የሚሰጠዉ አባቢ ብቸዉን ነበር እማን መድሀኒቱን ለአማን ስጭዉ የሚላት በጣም ስራ ሲበዛበት ከሀቅሙ በላይ ሲሆን ብቻ ነበር ግን ደግሞ አባቢ ሁሌም ስልነገሮችን ከአማን አጠገብ አንሱ ይለን ነበር ደጋግሞ እና አማን.....ቆይ እሽ አባቢ እስከዛሬ የደበቀን ለምን አማኔን እንዳንርቀዉ የአማኔን ሞራል ለመጠበቅ ወይስ ለምን ለነገሩ እስከዛሬ በነገረኝ እኔም በሱ ፍቅር ባልተሰቃየሁ ነበር ተወሳሰበብኝ ከመሀል አባቢ መድሀኒቱን ከጀ ወሰደና መድሀኒቱን እየፈታ በሽሮብ እቃ ማድረግ ሲጀምር ለምን ብየ ጠየቁት አሀ ለምን አደርገዋለሁ እናታቹህ እንደሆነች ታቃለች ነግሬታለሁ ለናንተም ያልነገርኳቹህ አማኔን እንዳትርቁት በእብደቱ ላይ ሞራል የሚነካ ንግግር እየተናገራቹህ አእምሮዉን እንዳትጎዱት.....ብቻ በብዙ ምክንያት ደብቄቹሀለሁ አሁን ግን በቃ አማኔም ተሽሎታል እወቁ አለኝ የምሰማዉን አላምን አልኩኝ ሰማይ ምድሩ ተደበላለቀብኝ ከመሀል ሪሀና መጣችና ሀናኔ ነይ አማኔ ታሪኩን ሊቀጥልልን ነዉ ብላ ጎትታ ወሰደችኝ የምን ታሪክ አልኳት በጣም ደንግጫለሁ አካሌ እዚህ ይሁን እንጂ ነፍሴ ከአካሌ ተለይቶ ተጉዟል ሪሁም የአማኔ ነዋ ስትለኝ አሀ እሽ ብየ ባልሰማም ብሰማም እየተርበተበትኩ ተቀምጨ ማዳመጥ ጀመርኩ


..... አማኔ ታሪኩን ካቋረጠበት " ምግቡን ሲስተር ሀዋ ሰጣህ በልተህ ጠጥተህ ከዛስ" ሪሀና ጠየቀች አማኔም "የማስታዉሰዉ ነገር የለም ጥዋት ስነሳ ራቁቴን ከሲስተር ሀዋ ጋር አንድ አልጋ ራሴን አገኘሁት የማየዉን አላምን አልኩኝ በህልሜ ይሁን በእዉኔ ብቻ አላቅም መጫህ ጀመርኩ ሲስተር ሀዋም "አቦ አትጩህብኝ ልተኛበት ምን ታካብዳለህ አለችኝ" ኧረ ማበዴ ነዉ ምን ላርግ ራሴን ጠላሁት የዛኔ ምድር ተዉጣ ብትዉጠኛ እንደኔ የታደለ ባልኖረ ነበር


ትዝ ሲለኝ ሲስተር ሀዋ የ Hiv በሽተኛ ናት ከዚህ ቡኋላ ምን ልሁን አላቅም ወዴት ልሂድ አላስታዉስም ብቻ ሱሚን ሳስታዉስ ታዛዝነኛለች ላንለያይ ምለን ነበር ምን ዋጋ አለዉ ያች የሰዉ አዉሬ ተጫወተችብኝ!......"

አማኔ ማልቀስ ጀመረ እኔም እንባየን መቆጣጠር አልቻልኩም "በዚህ ጊዜ ሱሚ አግባታ ወልዳ ጥሩ ሂወት እየኖረች ይሆናል ወይም ቃሌን ብላ እኔን በተስፋ እየጠበቀችኝ ይሆናል ብቻ አላህየ የሱሚን ነገር አደራ አንተዉ ከክፉ ነገር ጠብቅልኝ" ያረብ አያለ እጁን ወደ ላይ ወደ ጌታዉ አነሳ......

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል
Join

t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
7.1K views02:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-22 06:32:24 መራራ እዉነት
ክፍል 27

......... ሰሚራ ሽኩር


.....ሲስተር ችግር አለ ብየ ስጠይቃት "የምን ችግር ኧረ የለም እናተ ወዴት እየሄዳቹህ ነዉ" አለችን እኔም ወደኔ ቤት እስከምትድን ድረስ ልትኖር አንደሆነ ስነግራት ፊቷ ቲማቲም መሰለ ያ ትላልቅ አይኗ ተጎለጎለ አስፈራችኝ ሲስተር ሲስተር አልኳት "አንተ ቤትማ አይቻልም ከኔ ጋር ትኖራለች ከኔ ጋር!".....ሱመያ አላስጨረሰቻትም ከዶ.ር አማን ጋር ነዉ የምሄድ አለች አልሀምዱሊላህ ከሷ ጋር ብትል እኔጃ ሱመያ ከኔ እንድትለይ ለምን እንደማልፈልግ አላቅም የሲስተር ሀዋም ሱመያን በክፋት እይኖ አየቻት።
.... እኔ በጣም ግራ ገብቶኛል ሱመያ ከኔ ጋር ወደቤት እሄዳለሁ ካለች ጀምሮ ባህሪዋ ተቀይሮብኛል

.....ሱመያን እኔ ቤት ወስጃት ቤቴን በደንብ አሳየኋት ወንድሜ ሙሀመድንም አስተዋወቋት እሷም በደስታ ተዋዉቃ ከኛ ጋር መኖር ጀመረች ያ ፍዝዝዝ ብሎ የነበረ ቤት አሁን የወጉ ደርሶት ቡና ይፈላበት፤ ምግብ ይዘጋጂበት ...ጀመረ እኔም ሱመያን በጊዜ ሂደት እየወደድኳት ለሷ ያለኝ ስሜት/ፍቅር እየጨመረ መጣ እሷም በተመሳሳይ
.... "ከወደድከኝ ኒካህ አስረህ አግባኝ ካልሆነ ጫፌን እንዳትነካ ወጥቸ እሄዳለሁ" እያለች መቀለድ ጀመረች
እንዳለችዉም አጎቷን አስፈቅጀ ኒካህ አስረን ደስ የሚል የሚያስቀና ሂወት መኖር ጀመርን"

ምንድን ነዉ የምታወራዉ! ስል ሳላስበዉ ጫሁኩ ወይኔ ጉዴ ምን እንደነካኝ አላቅም አማኔንና ሪሀናን አስደነገጥኳቸዉ ከገቡበት የትዝታ ባህር አወጣኋቸዉ ግን ወላሂ አዉቄኮ አይደለም ምን እንደነካኝ አላቅም እንባየን ደጋግሜ ብጠርገዉም መልሶ ይፈሳል ልቤ በፍጥነት ይመታል ሰዉነቴ ይንዘረዘራል ለመናገር አፌ ይየያዛል ኢላሂ ምን ነካኝ አሁንስ የኔ ተራ ነዉ መሰል ማበዴ ነዉ ለራሴ ፈራሁ እራሴን እንደምንም አረጋግቸ ለምን እንደጮሁኩ ሲጠይቁኝ በማግባቱ ደስ ብሎኝ እንደሆነ ነገርኳቸዉ የልቤን አላህ እንጂ ማን ያቃል በቃ ለኸይሩ ነዉ ደሞስ ወንድምነቱ አይበልጥብኝም እንዴ አይ ሀናን ከራሴ ጋር ንግግር ጀመርን በመጨረሻም ራሴን አረጋገሁ በቃ አማን ሱመያን አ*ፍ*ቅ*ሮ......አግብቶታል አለቀ!!! ለኔ አማኔ ወንድሜ እንጂ ሌላ አይደለም

ከአማን ታሪክ እንመለስና ግን ፍቅር ማለት ምን ማለት ይሆን? ምንጩና መኖሪያዉስ የት ነዉ .....

እውነተኛ ፍቅር ምንጩ ልብ ነው። ጎጆውን የቀለሰው ከውስጥ ነው። ውሎና አዳሩ እዚያው
ነው። ህያው ሆኖ የሚንቀሳቀሰው በልብ አዳራሽ ውስጥ ነው። በተቀራኒው ቅብ የሆነ ፍቅር
መገኛው ከልብ ውጭ ባሉት የሰውነት ክፍሎች ነው። ለዚህም ነው እውነተኛ ፍቅር ዝንተ
ዓለም ሲቆይ ሁለተኛው በበኩሉ የሰውነት መጥፋትን ተከትሎ አብሮ የሚከስመው። ነብዩ
ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) «(አላህ) የኸዲጃን ፍቅር ችሮኛል» ብለው ሲናገሩ ለርሷ የነበራቸው
ፍቅር ምን ያህል ጥልቀት እንደነበረው ይጠቁማል። የፍቅር ክብደት ምን ያህል እንደሆነም
ያሳያል።
.
.
እውነተኛ ፍቅር ቃል ኪዳን ነው!!!ሀሰተኛ ፍቅር ማስመሰል ነው!በነብዩ ሙሐመድ
(ሰ.ዐ.ወ) ዘመን አንዲት አሮጊት ነበረች። ነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ለመጠየቅ በመጣች
ቁጥር ከተቀመጡበት ተነስተው በአክብሮትና በፍቅር የመቀበል ልምድ ነበራቸው። በነብዩ
ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አስደናቂ ባህሪ የተገረመችው እናታችን ዓኢሻ «ለዚህች አሮጊት
ለምንድን ነው የምትቆመው?» ብላ ነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ጠየቀቻቸው። «በኸዲጃ
ዘመን ትጠይቀን ነበር» ብለው መለሱላት።
.
.
በማስመሰል የታጀበ ፍቅር ፋና አልባ ነው። የሚያልፍ ጊዜ እንጂ የሚታወስ አሻራ የለውም።
ከአንጀት የሚነበብ ትዝታ ስሌሌለው የታሪክ ገፆቹ በሙሉ ወና ናቸው። የማስመሰል ፍቅር
በተፋቃሪዎች ምላሥ ላይ ማርን በአደራ እንደማስቀመጥ ነው። እውነተኛ ፍቅር ግን
በአይምሮ ላይ ተነቅሶ የሚቀር ትዝታ ነው። ለዚህም ነው ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
ወርቃማውን የኸዲጃ ዘመን ለአፍታ እንኳ ያልዘነጉት። ትዝታው በልባቸው በጥልቀት ተምሶ
ተቀብሯል። ከህሊናቸው ማህደር በክብር ሰፍሯል። የኸዲጃ ዘመን አይረሴ ሆኗል። ለርሷ
የነበራቸው ፍቅር ማራኪ ነበር !
.
.
እውነተኛ ፍቅር ህይወትን በጥበብ የምናጣጥምበት ቅመም ነው። ታላቁ ነብይ ሙሐመድ
(ሰ.ዐ.ወ) ፍቅር በነገሰበት የዓኢሻ እቅፍ ውስጥ ቁርኣን ይቀሩ ነበር። በአንድ ማዕድ
አብረው ይመገባሉ። በተከበረው እጃቸው ያጎርሷታል። ውኃ በጠጣችበት እቃ ይጠጣሉ።
ሆነ ብለው አፏ የነካበትን ቦታ ለይተው በመምረጥ በርሱ ይጎነጫሉ። ፆመኛ ሆነው
ይስሟታል። ከዚያም ወደ መስጂድ ይገባሉ። በአንድ መታጠቢያ ዕቃ ላይ ሆነው በጋራ
ሰውነታቸውን ይታጠባሉ። ምንኛ ያማረ ፍቅር ነው! ምንኛ አስደማሚ ትስስር ነው!!! ድንቅ
በሆነው የህይወታቸው ምዕራፍ ውስጥ ፍቁድ የሆነውን ተፈጥሯዊ ስሜታቸውን ማስተናገድ
በሚችሉበት ሁናቴ እያሉ ራሳቸውን ገዝተው የዓኢሻ ዕቅፍ ውስጥ ሆነው በቅዱስ
አንደበታቸው የፈጣሪያቸውን ቃል ( ቁርአን) ይቀሩ ነበር።
.
.
እውነተኛ ፍቅር መንፈስ እና አካል የተጋመዱበት ሚስጢር ነው። የስጋ አስፈልጎትና
የመንፈስ ቀለብ የሚጣመሩበት የተለየ የግንኙነት ነጥብ ነው። ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
«በዱንያ ውስጥ ካሉ (ፀጋዎች) እኔ ዘንድ ሴት እና ሽቶ የተወደዱ ናቸው። ሶላት ደግሞ
የዓይን መርጊያየ (የደስታ ምንጭ) ተደርጎልኛል» ብለዋል።
.
.
ፍቅር የሌለው ህይወት ውበት አልባ ነው። በህይወት ውስጥ የመኖር ስሜት ከነጠፈ ፍቅር
በህይወት ውስጥ መኖር አይችልም። በውበት የታጀበ ምቹ የህይወት ድባብ በሌለበት
ተጨባጭ ህያው የሆነ ስሜት መፋፋት አይችልም። እንግዲህ ይህ ሁሉ «ጥበብ»
ይጠይቃል። ጥበብ በፍቅር ውስጥ ጥንዶችን የሚያገናኝ አምባሳደር ነው። ሁለት የህይወት
አጋሮችን የሚያስተሳስር ታማኝ ልዑክ ነው። ጫፍ እና ጫፍ የነበሩ አካላትን የሚያገናኝ
ድልድይ ነው


ግን የአማን ታሪክ ትንሽ ቢያስከፋኝም ቢሰሙት የማይሰለች ጣፋጭ ታሪክ ነዉ እኔጃ ብቻ የሱን ታሪክ ስስማ ሁሉ ነገሩ ያስገርመኛል
ታሪኩ ደስ ብሎኛል የታሪኩ መጨረሻ እንደሚያምር ተስፋ እያደረኩ ወደ ታሪኩ ልመልሳቹህ አማን ቀጠለ
......"ከሱሚ ጋር በፍቅር አብረን መኖር ጀመርን ያየን ሁሉ ይቀናብን ነበር በጣም እወዳታለሁ እሷም ትወደኛለች ታምነኛለች አምናታለሁ ሁሌም በምንም ታአምር ላንለያይ ዘመን በማይሽረዉ በጌታችን ቃል ምለናል

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot
.
.
በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል
Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
8.0K views03:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-20 21:50:59 መራራ እዉነት
ክፍል 26
....... ሰሚራ ሽኩር


.....እስከሚሻላት አብራን ብትኖር ብየ አሰብኩ ግን እሷ ከወንድ ጋር ለመኖር ፍቃደኛ ትሆን አይመስለኝም እንደዉም ሴት መስየ የቀረብኳት እኔ መሆኔን ብታቅ ምን እንደሚፈጠር ማሰብ ከባድ ነዉ እሽ የት ላድርጋት የት ልጣላት ብዙ አሰብኩ ምን አልባት እየተሻላት ስለሆነ ምንም አትለኝም ብየ እንደድሮዉ ሴት ሳልመስል ጋዉኔን ለብሸ ገባሁ "ዉጣ ዉጣ ዉጣ".... እያለች መንዘርዘር ጀመረች

....ሁኔታዋን ከዉጭ ሁና ስትከታተል የነበረችዋ ሲስተር ሀዋ ፈጠን ብላ መጣችና "ዶ.ር ሂድ እኔ አለሁ" አለችኝ ሱመያም አይ "ሽቲ የምትለብሰዋን ዶ.ር ጥሪልኝ እኔ ከሷ ዉጭ ማንንም አልፈልግም" አለች ሺቲ የምትለብሰዋ እኔን ማለቷ ነዉ


.....ሴት ለመምሰል ሽቲ የምለብስ እኔ መሆኔን ባወቅሽ እያልኩ አሰብኩ እሷም "ዶ.ር ዉጣ ዉጣ ሺቲ የምትለብሰዋን ስልክ የምትሰጠኝን ይዘሀት ና!" ትእዛዝ ነዉ መሰል
.....መጣለችኮ አልኳት "የት መቸ ሲስተር ሀዋን አላልኩህም ያች ሁሌም እየገባች ምግብ የምትሰጠኝን" አለች ካልመጣች ብላ ስትቀዉጠዉ ሲስተር ሀዋ እኔ እንደነበርኩ ለሷ ብየ ሴት እመስል እንደነበረ በደንብ አስረዳቻት እኔ አፍሬ አንገቴን ደፍቸ ከክላስ ወጣሁ።


ሱመያም ተከትላኝ መጣችህ "ስማ የምታድኑ እናንተ፤ የምታቆስሉ እናንተ፣ የምታስለቅሱ ፤የምታስቁ እናንተ፤የምትወስዱ የምትመልሱ፤የምትፈርዱ የምትሽሩ የምትጥሉ የምታነሱ እናንተ... በቃ ሁሉም ነገር በእጃቹህ ነዉ ስትፈልጉ የፈለጋቹሀትን ሴት ትጫወቱባታላቹህ ሲበቃቹህ እንደሸንኮራ መጣቹህ ትወረዉሯታላቹህ!!!
....ቆይ እኛ ሴቶች ምን አረግናቹህ ምን ብንበድላቹህ ነዉ የስቃይን ጥግ የምታሳዩን እእእ መልስልኛ ..."

ምን ልመልስ አንገቴን አቀረቀርኩ አሳዘነችኝ ሱመያ ተረጋጊ ብየ አረጋገኋት።
ሱሜ ስሚኝ በርግጥ ወንዶች ብዙ በደል አድርሰዉብሽ ሊሆን ይችላል አቃለሁ ነገር ግን እነሱ ሌላ ሰዉ ሌላ ወንድ እኔ ደግሞ ሌላ ሰዉ ሌላ ወንድ ነኝ።
ከዚህ በፊት በገጠመሽን እያስታወሽ ሀሉንም ሰዉ በአንድ አትፈርጂ!
..... ስስተር ሀዋ ነግራሻለች እንዴት አድርጌ ስለጤናሽ ስከታተል እንደነበረ አይዞሽ የደረሰብሽ አደጋ ባንች ብቻ የደረሰ አይደለም አንች ከገባሽ ቡኋላ እንኳን ካንች የሚያንሱ በአባታቸዉ፤በአጎት በወንድም፤በቅርብ ዘመድ.... ስንት ህፃን ሴቶች ተደፍረዉ ገብተዋል አንች ቢያንስ በማታቂዉ ሰዉ ነዉ የተደፈርሽ አስበሽዋል ስሜቱን በቅርብ ዘመድ ብትደፈሪ እና አልሀምዱሊላህ አትይም ብየ ካረጋግኋት ቡኋላ የተደፈሩትን በተኙበት ክፍል እየሄድኩ አሳየኋት ትንሽ ከተረጋጋች ቡኋላ ይቅርታ ጠይቃ አመሰገነችኝና ልትሄድ አንድ እርምጃ ስትራመድ እህ ሳንተዋወቅ አልኳት ስሟን ቦርሳዋጋ የነበረዉ አንዱ ደብተሯ ላይ አንብቤዉ እንጂ ስለሷ አላቅም


....."ሱመያ እባላለሁ የሁለተኛ አመት የ garment enginering ተማሪ ነኝ ብላ ራሷን አስተዋወቀችኝ እኔም አማን እንደምባል ከነገርኳት በኋላ አሁንም ልትሄድ አንድ እርምጃ ስትራመድ ወዴት ልትሄጂ ነዉ ስል ጠየቋት "ከሆስፒታል እንድወጣ ትዛዝ ተሰጦኛል ወዴት እንደምሄድ አላቅም እናትና አባት የለኝም ያሳደገኝ አጎቴ ነዉ መደፈሬን ካወቀ አያስገባኝም ይገለኛል የት እንደምሄድ አላቅም እግሬ ወደሚመራኝ መንገድ እጓዛለሁ ደህና ሁን" ብላ መራመድ ስትጀምር ምን እንደነካኝ አላቅም ከኔ እንድትለይ ፍቃደኛ አልነበርኩም በቃ ሳያት ወደድኳት መሰል እኔጃ ብቻ በደንብ እስከሚሻልሽ የኔ ቤት ክፍት ነዉ መኖር ትችያለች አልኳት"

የአማንን ታሪክ እየሰማሁ ከየት መጣ ሳልለዉ እንባየ እንደጎርፍ በሁለት ጉንጮቸ ይፈስ ጀመር ምን ሁኘ ይሆን አላቅም ምን አልባት ለአማን የነበረኝ ስሜት የወንድም አልነበረም ይሆናል የልቤን ጩኸት ዋጥ አድርጌ አማን እንዳያቅብኝ ቶሎ ቶሎ እንባየን እየጠረኩ ሲያሻኝም ባልወድ በጥርሴ ፈገግታ እየተደበኩ ታሪኩን ማዳመጥ ጀመርኩ



አማኔም በትዝታ ባህር ርቆ ተጉዞ ስለነበር ለኔ እንባ ትኩረት አልሰጠዉም ሚስኪን ሪሁየ እህቴ በአማን ንግግር ደንግጣ አይን አይኔን ትመለከት ጀመር እኔም የማለቅስ በሱመያ ታሪክ አዝኘ እንደሆነ ለማስመሰል በየመሀሉ አፌን መምጠጥ ጀመርኩ ኧረ ኢላሂ! ደስታየን አጣጥሜ ሳላበቃ በሀዘን ልቤ ተሰበረ ምን አለ ታሪኩን ባላቅ ብየ ተመኘሁ አይ ዱንያ አምርሬ ረገምኳት ጩሄ አይወጣልኝ ነገር የታፈነ ጩኸት ሆነብኝ ኧረ ምን ተሻለኝ ብቻ መጨረሻዉ እንዳሰብኩት እንዳይሆን ተመኘሁና ታሪኩን ማዳመጥ ጀመርኩ አማኔም ንግግሩን ቀጠለ ...."እሷም ካቅማማች ቡኋላ ብቻህን ነዉ የምትኖር ወይስ አለችኝ
አይ አብሽሪ ከወንድሜ ጋር ነዉ የምኖር ብያት እሷም ተስማምታ ወደ ቤቴ ልንሄድ ስንወጣ ሲስተር ሀዋ በክፋት አይኖ መመልከት ጀመረች አስተያየቷ አላማረኝም ሲስተር ችግር አለ ብየ ስጠይቃት "የምን ችግር ኧረ የለም እናንተ ወዴት እየሄዳቹህ ነዉ" አለችኝ እኔም ወደኔ ቤት እስከምትድን ድረስ ልትኖር እንደሆነ ስናግራት ፊቷ ቲማቲም መሰለ ያ ትላልቅ አይኗ ተጎለጎለ አስፈራችኝ ሲስተር ሲስተር አልኳት እሷም "አንተ ቤትማ አይቻልም ከኔ ጋር ትኖራለች ከኔ ጋር!"....ሱመያ አላስጨረሰቻትም

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot
......

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል
Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
7.8K views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-20 06:41:27 መራራ እዉነት
ክፍል 25
........ ሰሚራ ሽኩር

........ወይ ዛሬ በጣም ደስ አለኝ ግን ታሪኩን አልጨረሰልንም ዳ.ር ከሆንክ ቡኋላስ ታሪኩን ቀጥልልን ስል ጠየቁት አማኔም ታሪኬ ምንም አያደርግላቹህም ያስጠላል።
....ግን ታሪኬ ትምህርት የምታገኙበት ስለመሰለኝ እነግራቹሀለሁ ብሎ ታሪኩን መናገር ጀመረ

ዳክተር ሁኘ ስሰራ ብዙ አይነት ሰዎች፤ ብዙ አይነት ህመሞች ያጋጥሙኝ ነበረ
ሱሜንም(ሱመያ) ያገኘኋት እዚሁ ሀኪም ቤት ነበር ብሎ አዮኖች እንባን ያዘንቡ ጀመር ከብዙ አመታት በፊት የተፈጠረዉ አጋጣሚ በትዝታ እንዲህ ሲል አጫወተን

.....እሁድ ቀን ሆስፒታል አዳሪ ተረኛ እኔ ነበርኩ ታካሚዎችን እስከ ስድት(6) ሰአት ካስተናገድኩ ቡኋላ እንቅልፌን መቋቋም አልቻልኩም ቀንም በዝራ ቪዚ ስለነበርኩ ጋዉኔን ሳላወልቅ ከተቀመጥኩበት የተሽከርካሪ ወንበር ሳልነዛ እንቅልፍ ወሰደኝ ለሊት ወደ አስራ አንድ ሰአት ይመስለኛል ሁለት ወጣቶች አንድ በጣም ዉብ የሆነችን ወጣት አንዱ በእቅፉ ይዛ አንዱ ጫማዋንና ሂጃቧን ይዘዉ ዶክተር ዳክተር! እያሉ በጩኸት ወደኔ መጡ

....እኔም ከእንቅልፌ ደንግጨ ነበርና የተነሳሁ ምን ተፈጠረ አልኳቸዉ እነሱም ይችን ህፃን ተጫዉተዉባት እባክህ ፍጠን የምታደርገዉን አድርግ ስታቃስት ስትጮህ ቆይታ ከሁን ነዉ ራሷን የሳተች ሳይ የልጂቷ ፀጉር በጣም ረዥም ነዉ በልጁ እጂ ወደ ታች ወርዶል፤ መልኳ በጣም ቀይ አፍንጨዋ ቀጥ ያለ ቀጠን ያለች ልብሷ በደም የተነከረ ዉብ ቆንጆ እንስት ናት ።

እኔም በፍጥነት ግልኮስ ተክየላት እነሱ ከየትና እንዴት እንዳገኟት ጠየኳቸዉ ያገኟት ሱቢሂን ለመስገድ ከቤታቸዉ ሲወጡ መንገድ ላይ ነበር ስትጮህ የደረሱላት ማን እንደዚህ እንደተጫወተባት የሚያዉቁት ነገር አልነበረም ብቻ በጣም ጥሩ ልጆች ናቸዉ እስከምትነቃ ለሰአታት ከጠበቋት ቡኋላ ነቃች ሁላችንም አጠገቧ ነበርን ሁላችንንም አልያቹህ አለችን ሀኪም ቤቱን በዛ በለሊት በጩኸት ቀወጠችዉ።

ፈራናትና ሁላችንም ወጣን ለነገሩ ሲስተር ሀዋ አለች የኔ አጋዥ እሷ ናት ሲስተር ሀዋ ስትገባ ምንም አላለቻትም እኛን ግን ስታይ እየጮኸች፤እያለቀሰች ፊቷን አዙራ በፍራት ትንቀጠቀጠች።

....በወንዷች ከባድ ጉዳት ስለደረሰባት ወንዶች ሁሉ አንድ አይነት ነዉ የሚመስሏት ለማንኛዉም ሲስተር ሀዋ ስላለች ትንከባከባታለች አብሹሩ ብየ ያመጧትን ልጆች ወደ ቤታቸዉ ላኳቸዉ

ሪሀና "አማኔ ሲስተር ሀዋ ማን ናት" ስትል ወሬዉን አቋረጠችዉ

አማኔም "ሲስተር ሀዋ ማለት ከተመደብኩኝ ቀን ጀምራ አይዞህ የምትለኝ፤ከጎኔ ሁሌም የማትጠፋ በጣም የማዝንላት ሚስጥሯን የምትነግረኝ የምነግራት የሀኪም ቤት ጓደኛየ ናት

የሲስተር ሀዋ እናትና አባቶቿ የHiv በሽተኛ ናቸዉ ሲስተር ሀዋንም ሲወልዱ በቂ ክትትል አላደረጉላትም ነበር ሲስተር ሀዋ የHiv በሽተኛ ሆነች።
ስለሆነች ሁሉም ዶክተሮች ይርቋታል


አንድን ታማሚ ካገለልነዉ ለኛ ጥሩ አስተሳሰብ አይኖረዉም በጥላቻ በክፋት ያየናል እንደዉም አላህን የማይፈራ ከሆነ እኛንም ለተጠቃበት በሽታ ሊዳርገን ይችላል ስለዚህ እንጠንቀቅ በተቻለን መጠን አንራቃቸዉ በመጠኑ እየተጠነቀቅን እንቅረባቸዉ።

.....እኔ ግን ሲስተር ሀዋ ታሳዝነኛለች ሁሌም አብሬት እበላለሁ፣ እጠጣለሁ፣ አብሬት አዉላለሁ ፤እሷን ለማፅናናት የማላረገዉ ነገር የለኝም እንደዉም ሰዉ እሷን መቅረብ የጀመረ እኔ እዛ ሀኪም ቤት ገብቸ አብሬት ስበላ ስጠጣ ሲያዩ ነዉ
በዚህም ደስ ይላታል "በአንተ ሁሉን ነገር ረሳሁት እንደአዲስ የተፈጠርኩ መሰለኝ አማኔ ዉለታህን የምመልስ ያድርገኝ" ትለኝ ነበር እኔ ሞኙ አምናታለሁ እንደእህቴ እቀርባታለሁ፤ እረዳታለሁ ገንዘብ ከፈለገች ከፈለገችዉ በላይ በቸክ እፈርምላታለሁ ደሞዜንም በሆስፒታሉ ከሚሰሩት ከሁሉም የተሻለ ስለነበረ የሚቸግረኝ አንዳች ነገር የለም ይሄን እንተወዉና ስለሱመያ ልንገራቹህ" ሲል ንግግሩን ቀጠለ



"ሱመያን ጤንነቷን ቸክ ላረግ ስገባ ትጫሀለች ትንቀጠቀጣለች የምትገባበት ይጨንቃታል ወላሂ ከልቤ አዘንኩ ምን አይነት ሰዉ መሰል ሰይጣን ይሆን የተጫወተብሽ እላለሁ ሰዉ ስሜቱን የሚከተል ምን አይነት በግ ሁኗል አሁን ይችን ሚስኪን ጨክነዉ .....ስል አስባለሁ

የግድ ጤንነቷን መከታተል ነበረብኝ ስገባ ትጮሀለች ምን ላርግ ሳስብ ወንድ በመሆኖ ከሆነ የጠላችኝ መሆን እንጂ መምሰል ቀላል ነዉ።ለምን ሴት መስየ አልገባም አልኩና ፂሜን በትልቅ ማስክ ሸፍኘ፣ ከሱሪየ በላይ የሲስተር ሀዋን ሽቲ ደርቤ፣ እጀን ጓንት አልብሸ፤ ፀጉሬን በሂጃብ ሸፍኔ.... መግባት ጀመርኩ ሪሀና ወሬዉን አቋርጣ ተክ ብላ ሳቀች ለምን እንደሳቀች አማን ሲጠይቃት
"የምር ወንድሜ አማን ሳልኩህ ሴት ነዉ የምትመስለዉ" እኔ ታሪኩን ለማወቅ በጣም ጓጉቸ ስለነበር ከዛስ አልኩ አማንም "ከዛ ሱመያም አትፈራኝም ሴት ነዉ የምመስላት ደሞ ስልክ የላት ደዉየ ለቤተሰቦቿ የተፈጠረዉን አልናገር ቤተሰባቿም ሆኑ ጓደኛ የሚባል ይኑራት አይኑሯት የማቀዉ ነገር የለም ብቻ እየገባሁ ስለ ጤንነቷ አረጋግጨ ላወራት እፈልግና ድምፄ የወንድ እንደሆነ ካወቀች ትርቀኛለች አልና እወጣለሁ በዚህ ማሀል ስመላለስ ሳያት ምግቧን በስአቱ ስሰጣት እየተሻላት ማልቀሷን ትታ ፈገግ ማለት ጀመረች እንዳይደብራት ብየም ሲም የሌለዉ ስልክ አስቂኝ ቀልዶችና የተለያዩ ሀዲሶች የተጫኑበትን ሰጠኋት እሷም እየተሻላት ስትመጣ ሆስፒታሉ አልጋ ለሌላ ተረኛ እንድትለቅ አዘዘ የት ትሂድ ወዴት አዉጥተን እንጣላት ግራ ሲገባኝ ቤት ወንድሜ ብቻ ነዉ ያለ አብራን እስከሚሻላት ድረስ ብትኖር ብየ አሰብኩ ግን እሷ ከወንድ ጋር ለመኖር ፍቃደኛ ትሆን አይመስለኝም እንደዉም ሴት መስየ የቀረብኳት እኔ መሆኔን ብታቅ ምን እንደሚፈጠር ማሰብ ከባድ ነዉ እሽ የት ላድርጋት የት ልጣላት........

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot


በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል
Join

t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
7.8K viewsedited  03:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-19 20:23:57 መራራ እዉነት
ክፍል

............ ሰሚራ ሽኩር


.......ተመልሸ ወደ ቻይና ሂጀ ስራ መጀመር ነበረብኝ ልሄድ ካሰብኩ ቡኋላ አንድ ወንድሜን ስመለስ እንደማየ ባጣዉስ ብየ ፈራሁ
ከዛ ወጀ ቻይና ልሄድ የነበርኩትን ጉዞ ሰርዠ እዚሁ ስራ ማፈላለግ ጀመርኩ በአንድ ቀን አንድ ትልቅ ሆስቲታል ዶክሜንቴን ሁሉ አስገባሁ በደስታ ተቀበሉኝ "

አላመንኩም!አማን ዳክተር ነዉ ደነገጥኩ እኔጃ ብቻ አላመንኩትም ግን ደግሞ አባቢ ያኔ አደጋ ሲያደርስ ካለ ነገር ልጁን በሂወት እንዲቆይ ሰበብ አልሆነም ደሞ ሀኪም ቤት ከ ዳ.ር ጋር ቀዶ ጥገና ክፍል ገብቶ ነበር እዛ ደግሞ ዳክተሮቹ ብቻ ነበር የሚገቡት ብሎናል



ነገሮች ሁሉ ተወሳሰቡብኝ እንዴት አልጠረጠርኩም ራሴት ታዘብኩት ግን ደግሞ አሁንም አላመንኩም ሰሞኑን ከምግቡ ይሆን ከጭንቀት ጨንጓራየን በጣም አሞኛል እንደዉም ይሄ ጥሩ አጋጣሚ ነዉ አማን ዳክተር ከነበረ ስለህመሜ በቂ እዉቀት ይኖረዋል ለነገሩ የሆድ ዉስጥ እስፔሻሊት ካልሆነ እንዴት ያቃል ምናልባትም ከአንገት በላይ ፤ የአጥንት.... እየተባሉ ዳክተሮች ሲለሚከፋፈሉ እሱ ላያቅ ይችላል ለማንኛዉም እስኪ ልጠይቀዉ ብየ ልጠይቀዉ ስል ሪሀና እማን ዳክተር ነዉ ደስ ሲል ሀናን ደስ ይበልሽ ጨንጓራየን አመመኝ ቆረጠኝ የለም አማን አለልሽ እሱ ያክምሻል ፐ በአንድ ቤት ሁለት ዳክተር እያለች ሳቀች


አማኔም "ሀናን ጨንጓራሽን ያምሽ ነበር እንዴ ቆይ ምግብ መመገብ ቀንሰሻል፤ሆድሽ አካባቢ ያቃጥልሻል....ሲል ጠየቀኝ እኔም አወ ያቃጥለኛል ምግብም ብዙም አይደለሁም አልኩት



አማኔም ይሄማ የጨጓራ ባክቴሪያ / H. pylori infection ይባላል

ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ የሚባለዉ ባክቴሪያ የጨጓራ ኢንፌክሽን እንዲከሰት የሚያደርግ የባክቴሪያ አይነት ሲሆን ይህ ኢንፌክሽን በብዛት የሚከሰተዉ በልጅነት የዕድሜ ክልል ነዉ፡፡ ይህ ባክቴሪያ የጨጓራ ቁስለት እንዲከሰት ከሚያደርጉ ሁነኛ መንስዔዎች ዋነኛዉ ሲሆን ኢንፌክሽኑ በአለማችን ከግማሽ በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ አንደሚታይ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡

የህመሙ ምልክቶች
ብዙዎች የሄሊኮባክተር ፓይሎሪ እንፌክሽን የተፈጠረባቸዉ ሰዎች ምንም አይነት የህመም ምልክቶች አይታይባቸዉም/ላይኖራቸዉ ይችላል ፡፡ የህመም ምልክቶች የሚታይባቸዉም
የሆድ ላይ ህመም ወይም የማቃጠል ስሜት
ጨጓራዎ ባዶ ሲሆን የሚባባስ የጨጓራ ላይ ህመም
ማቅለሽለሽ ፤የምግብ ፍላጎት መቀነስ፤ በተደጋጋሚ ማስገሳት፤ የሆድ መንፋት
የክብደት መቀነስ .....ናቸዉ፡፡


ከፍተኛና የማያቋርጥ የሆድ ላይ ህመም ካጋጠመሽ
የመዋጥ ችግር ካለብሽ
• ደም የተቀላቀለበት ወይም የአስፓልት ሬንጅ የመሰለ/ የጠቆረ ሰገራ ከወጣሽ
ቀይ ወይም የቡና አተላ የመሰለ ነገር ካስታወከዎ በአፋጣኝ የህክምና ሀኪም ቤት መሄድ አለብሽ አለኝ

ገረመኝ አሁን ዳክተር እንደነበረ እርግጠኛ ሆንኩኝ ሪሀና "አማኔ ጨንጓራ ባክቴርያ እንዴት ሊፈጠር ይችላል ለኢንፌክሽኑ የሚያጋልጡ ነገሮች ምንምን ናቸዉ የማቀዉ ነገር የለም" ስትል በደንብ እንዲያብራራላት ጠየቀች አማኔም


ለኢንፌክሽኑ ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮች
በተፋፈገ/በተጨናነቀ ቦታ መኖር
ንፁህ የዉሃ አቅርቦት በሌለበት መኖር
በማደግ ላይ ባሉ/ባላደጉ አገሮች/ የሚኖሩ ሰዎች፡ ንፅህናዉ በማይጠበቅ ሁኔታ ዉስጥ መኖር
የሄሊኮባክተር ፓይሎሪ ባክቴሪያል እንፌክሽን ካለዉ ሰዉ ጋር መኖር የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች ደግሞ

የደም ምርመራ
የትንፋሽ ምርመራ/ዩሪያ ብሬዝ ቴስት
የሰገራ ምርመራ ናቸዉ፡፡

ሊደረግ የሚችል ህክምና
የባክቴሪያዉ እንፌክሽን መኖሩ ከተረጋገጠ የህክምና ባለሙያ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ባክቴሪያዉን ሊያጠፋ የሚችሉ መድሃኒቶች ሊያዝላቹህ ይችላል ።

ሀናን ምንም አላለኝ ብለሽ ዝም አትበይ ሊያደርሰዉ የሚችለዉ ጉዳት/ Complications ብዙ ነዉ

ከጨጓራ ባክቴሪያ እንፌክሽን ጋር ተያይዞ ሊመጡ የሚችሉ ጉዳቶች
ቁስለት፡- የጨጓራ ባክቴሪያ የጨጓራ መከላከያ እንዲጎዳ ያደርጋል፡፡ በዚህ የተነሳ የጨጓራ አሲዱ ጨጓራ ላይ ቁስል አንዲከሰት ያደርጋል፡፡
የጨጓራ ሽፋን እንዲቆጣ ያደርጋል- የጨጓራ ባክቴሪያ ጨጓራን በመቆጥቆጥ እንዲቆጣ ያደርገዋል፡፡
የጨጓራ ካንሰር፡- የጨጓራ ባክቴሪያ ለተወሱ የጨጓራ ላይ ካንሰሮች መከሰት ዋነኛ መንስኤ ሊሆን ይችላል፡


ወይ ዛሬ በጣም ደስ አለኝ ግን ታሪኩን አልጨረሰልንም ዳክተር ከሆንክ ቡሀላስ ታሪኩን ቀጥልልን ስል ጠየቁት አማኔም ታሪኬ ምንም አያደርግላቹህም ያስጠላል።
..... ግን ከታሪኬ ትምህርት የምታገኙበት ስለመሰለኝ እነግራቹሀለሁ ብሎ ታሪኩን መናገር ጀመረ

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot

ኢንሻአላህ ይቀጥላል

Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
7.2K views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-19 06:32:03 መራራ እዉነት
ክፍል

....... ሰሚራ ሽኩር

......እዛም እንደገባሁ ቤተሰቦቹ ጥሩ አድርገዉ አስተናገዱኝ ትምህርት ቤትም ገባሁ ነገር ግን በአንዴ እማየ ናፈቀችኝ እኔጃ ሁሉም ነገር አስጠላኝ በዛ ላይ የነሱን ቋንቋ አልችልም ጨለማ መስሎ ታየኝ ጆርጂን ወደ ሀገሬ እንዲመልሰኝ ጠየቁት እሱም"ምን ማለትህ ነዉ አንተን እዚህ ለማምጣት ስንት እንደለፋሁ ታቅ የለ ደሞስ እናትህ መርቃ የሸኘችህ ተመቸኝም አልተቸኝም ብለህ እንድትሄድ ነዉ?
.... አማን ጠንከር ብለህ ተማር እናትህ የፈለገችዉ ቦታ ደርሰህ ህልሟን እዉን አድርግላት ስማ ላንተ ሳይሆን ለዛች ሳትበላ አብልታ ፤ሳትለብስ አልብሳ፤ሲያምህ ታማ ላሳደገችህ እናት ብለህ ቆይ እኔ እያለሁስ እኔ አግዛቹህ ነበር አሁን ሂደህ በዚህ እድሜህ ምን ልሰራ ነዉ..."የትያቄ ማእበል አወረደብኝ ወላሂ ልሂድ ብየ በመጠየቄ አፈርኩ አንገቴን አቀረቀርኩ ጆርጂም አይዞህ ቋንቋዉ ከባድ ይመስላል እንጂ ቀላል ነዉ እኔ አስተምርሀለሁ አለኝ ግን የሚቻል አልመስልህ አለኝ ፁህፉ ኧረ ኢላሂ ይሄን እኔ ፅፌ ላወራዉ ነዉ እል ነበር ለካስ የሰዉ ልጂ ተአምራዊ ነዉ የማይቻል ነገር የለም ከትንሽ ጊዜ ቡሀላ በደንብ መናገርና መፃም ጀመርኩ

.....ትምህርት ቤት ብዙ ጊዜ በዘር፤በሀይማኖት....የነሱ ካልሆን ለሁሌም መጨረሻ ተሰላፊ ነን እነሱ አጥፍተዉ የምንቀጣ እኛ እኩል ዉጤት አምጥተን የሚሸለዉ እነሱ ናቸዉ ብቻ ማን እንደሀገር !ሁሉ ነገሩ ይከብዳል በተለይ ከሰዉ በታች አድርገዉ ሲያዩን ልባችን ይደማል።

.....ጆርጂ ሁሌም ይከታተለኛል ጥሩ ዉጤት እንዳመጣ ያስጠነኛል የምፈልገዉን ነገር ሳልጠይቀዉ ያሟላልኛል ከትምህርት ቤትም የተሻልኩ ተማሪ ለመሆን በቃሁ እናቴን በዱአ እረስቻት አላቅም ከተለያየን አስራ ስምንት አመት ሆነን እኔም ትምህርቴን እናቴ እንደምትፈልገዉ ዶክተር ሁኘ ተመረኩ ከሶስት አመት በፊት በጎረቢት ስልክ እየወደልኩ አንዳንዴ አወራት ነበር


.....ከሶስት አመት ቡኋላ ግን ስልኳም እቢ አለ አግኝቻት አላቅም ብቻ ሰላም ትሁንልኝ እኔም ሰሞኑን መሄዴ አይቀርም የመጠሁበትን አላማ አሳክቸ ጨርሻለሁ ብየ ጆርጂን ጠየኩት ጆርጂም በደስታ እናትህን አይተህ ትመጣለህ ብሎ እያለቀሰ ላከኝ እኔም እያለቀስኩ አመስግኘዉ ወደ ሀገሬ መጣሁ ምንገድ ላይ ልቤ መረጋጋት አልቻለም ዝም ብሎ ጭንቅ ጭንቅ ይለኝ ጀመር


.... አሁን እንዲህ አድጌ ስታየኝ ምን ትል ይሆን ስል አሰኩ ያ ሁሉ ችግር ከእንግዲህ ያበቃል ....ያረብ እናቴን በሰላም ላግኛት በጣም ንፍቅ ብላኛለች እያልኩ ወደ ቤት ገባሁ ሰርፕራይዝ ነዉ መምጣቴን ማንም አያቅም ለማየ ሂጃብ መስገጃ....ያልያዝኩት ነገር የለኝም
ለወንድሜም ብዙ ነገር ይዘዣለሁ


.... ቤት እንደደረስኩ ቤቶች ብየ ገባሁ አንዲት ሴት መጣችና ምንድን ነዉ አለችኝ እኔም ደንገጥ ብየ እማስ አልኳት ማን ነች እማ ስትል ጠየቀችኝ ግራ ገባኝ እእእእ እዚህ የነበሩት ይሄኮ የኛ ቤት ነበር እናንተ እነማን ናቹህ ወንድሜስ.....

"ቆይ አንተ የማማ ፋጡማ ልጂ ነህ" ስትል ጠየቀችኝ እኔም አወ የሷ ልጂ ነኝ "ዉይ አላህ ለጀነት ይበላቸዉ እንዴት ያሉ ጥሩ ሰዉ ነበሩ ይሄን ቤት ወንድምህ ነዉ ከሶስት አመት በፊት እናታቹህ ስትሞት የሸጠልን" አለችኝ


የምሰማዉ በህልሜ ነዉ ወይስ በዉኔ እማ አልሞተችም ትሰሚያለሽ እማ አልሞተኝም ብየ የልጂቷን አንገት ጠቅጠቄ ያዝኩት ከመሀሌ ወንድምህ መጣ ብሎ ማን እንደነገረዉ አላቅም ወንድሜ ሙሀመድ መጣና ተጨምጭሞ ማልቀስ ጨመረ እንዴት እንደለየኝ አላቅም አስራ አምስት አመት ሙሉ ተለያይተን ለነገሩ እሱ ጠቆር ማለቱ እኔ ነፃ ማለቴ ነዉ እንጂ መንታ ነዉ የምንመስለዉ።

ሙሀመድ እማየ መሞቷን ሲነግረኝ
አላመንኩም እማ መጥታቸለሁ እይኝ! እማየ እይኝ ዶክተርኮ ሆንኩልሽ! እማ ህልምሽ እዉን ሆነልሽ! እማ አቤት በይኝ! አማ ያ ሁሉ ችግርኮ በኔ በልጂሽ አሁን ሊያልፍልሽ ነዉ! እናቴ ያልፋል ብለሽኝ አልነበረ ሲያልፍ ሳታይ አማ ......ብጮህ ብነሳ ብወድቅ ከየት ትምጣ ላትመለስ ወደ ዘላለማዊዉ ሂወት ሂዳለች አላህ ለጀነት ይበላት።
እኔም ለብዙ ቀን አዘንኩ ለጆርጂም ነገርኩት አይዞህ ብሎ አፅናናኝ

....ተመልሸ ወደ ቻይና ሂጀ ስራ መጀመር ነበረብኝ ልሄድ ካሰብኩ ቡኋላ አንድ ወንድሜን ስመለስ እንደማየ በጣዉስ ብየ ፈራሁ


Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት
@Meh_Ani_bot

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል
7.4K viewsedited  03:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-18 07:02:10 መራራ እዉነት
ክፍል

........ ሰሚራ ሽኩር


አንድ ቀን ጆርጂ እናትህን አስተዋዉቀኝ ብሎኝ እማየን ላሳየዉ ይዤዉ ወደ ቤታችን አቀናሁ

እማየ ጥጥ እየፈተለች ነበር የደረስን ጭኗ ጠቁሮ ብልዝ ብሎ ጆርጂ አየዉ ...እማየም አማኔ ማን ነዉ ስትል ጠየቀችኝ እማ ጆርጂ ይባላል ከሱ ጋር ነዉ የምሰራ ብየ አስተዋወኳት ።
...... አረፍ በሉ ብላን ወደ ዉስጥ የሚበላ ነገር ልታመጣልን ሄደች ምን ልታመጣ ይሆን ብየ ተጨነኩ
.... እንጀራ በበርበሬ ይዛ መጣች ቤት ያፈራዉን ብሉ ወጥ አልሰራሁም ብላ አቀረበችልን እማ ጆርጂ በርበሬ የሚበላ አይመስለኝም ከሱ ጋር ሁሌም ሩዝ ነዉ የምበላ አልኳት ጃርጂም እየተንተባተበ በርበሬ እበላለሁ አትጨነቂ ብሎ ግድ አለግድ መብላት ጀመረ አንድ ጉራሽ በአንድ ብርጭቆ ዉሀ እያወሀደ

....የምር ጆርጂ ሰዉ አክባሪ የሰዉ ምንነት የገበዉ ስላለዉ የማይንጠራራ ከሁሉም ጋር መግባባት የሚችል ጥሩ ሰዉ ደግ ሰዉ ነዉ።

እንዲህ እንዲህ እያልን በኩንትራት የያዘዉ ፎቅ አለቀ እሱ ደስ ሲለዉ እኔ ከሱ መለየቴ ከፍኝ ወደ ሀገሩ ሊመለስ ነዉ እማየም በጣም ትወደዉ ነበር አዘንኩ ጆርጂም "አይዞህ አትዘን እኔ በጉዲፈቻ አሳድገዋለሁ ብየ ይዠህ እሄዳለሁ አለኝ ደነገጥኩ ደስታና ሀዘን ባንዴ ወረሩኝ ደስ ያለኝ ከጆርጂ ጋር ቻይና መሄዴ ሲሆን የከፋኝ እናቴን እንዴት ትቻት እሄዳለሁ የሚለዉ ነበር ......ግራ ገባኝ እማየን ነገርኳት እሷም በጣም አዘነች ነገር ግን አዛ ጥሩ የትምህርት እድል እንደማገኝ ጆርጂ ሲነግራለት ቅር ቢላትም መርቃ ሸኘችን

ቻይና ዉስጥ
....... ኢስልምናን ለመጀመሪያ ጊዜ ቻይና የደረሰው በዑመር (ረ.ዐ) ኸሊፋነት ዘመን በታላቁ ሰሃባ ‹‹ሰዓድ ኢብን አቢ-ወቃስ›› (ረዐ) እንደሆነ ይነገራል።

በቻይና የመጀመሪያውን መስጂድ ያሰራውም ሰዓድ ሲሆን ‹‹ሑዓሼንግ›› የሚባልና አሁንም በይዞታ የሚገኝ የ1300 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ መስጂድ ነው።

በአገሪቱ 80 ሚሊዮን የሚገመቱ ሙስሊሞች እንዳሉ የሚገመት ሲሆን ከህዝቡን 2% ገደማ ይሸፍናሉ።

ሙስሊሞቹ በብዛት የሚኖሩበት ቦታ ‹‹ዢንጂያንግ›› ሲባል ከአፍጋስታን፣ ፓኪስታን፣ ህንድ፣ ታጃኪስታን እና ሌሎች ጋር የሚዋሰን ሰፊ ግዛት ነው።

‹‹ዢንጂያንግ›› ቀድሞ የዑስማያ ኸሊፌት የተርኪስታን ግዛት የነበረ ሲሆን ኸሊፋው ከወደቀ በኋላ በ1949 ቻይና በሐይል ልትወስደው ችላለች። ግዛቱም ከቻይና ሰፊው ሲሆን በማዕድን የበለፀገ ነው።

ቻይና ውስጥ ሁለት አይነት ነገድ ያላቸው ሙስሊሞች ያሉ ሲሆን ‹‹ሐም›› እና ‹‹ኡግሁር›› ይባላሉ። ሐሞች ቻይናዊ ሲሆኑ ኡግሁር ደግሞ በመልካቸውም የተለዩ የመካከለኛው ኤዥያ ዝርያዎች እንደሆኑ ይታመናል።

በቻይና ሁሉም ሙስሊሞች መድሎ ቢደርስባቸው ከፍተኛ በደል የሚፈፀምባቸው ግን የኡግሁር ሙስሊሞች ናቸው።

የኡግሁር ሙስሊሞች ከሌላው በተለየ በደል የሚደርስባቸው አንደኛው በዘራቸው ቻይናዊ ስላልሆኑ ሁለተኛው ደግሞ አካባቢው በማዕድን የበለፀገ ስለሆነ መንግስቱ ህዝቡን የማጥፋት ዕቅድ እንዳለው ይነገራል።

ቻይና በኡግሁር ሙስሊሞች ላይ ከምትፈፅመው ግፍ መካከል ወላጅና ልጅን መነጣጠል፣ በማጎሪያ ካምፖች ማሰር፣ አካላቸውን መበለት፣ ሰላት፣ ፆምና ቁርኣን መከልከል፣ አልኮል ማስጠጣት፣ የአሳማና ውሻ ስጋ ማስበላት፣ መግደል እና ሌሎችንም ይፈፅማሉ።

የቻይና መንግስት ይህን ሁሉ አሰቃቂ ግፍ እየፈፀመ ድርጊቱ ‹‹ሽብርተኝነት›› አልተባለም።

በዑመር (ረዐ) ዘመን የቻይና መንግስት ለፋርስ ንጉስ መጠጊያ እንኳን ለመስጠት ኸሊፋውን በመፍራት እንቢ ማለቱ ይነገራል። ዛሬ የሙስሊም አገራት የኡግሁር ሙስሊሞች አሰቃቂ ግፍ እየተፈፀመባቸው እያዩ ከቻይና ጋር የንግድ እንቅስቃሴያቸውን እንኳን ማቆም አልቻሉም።

‹‹አይሁዶችንና እነዚያን ያጋሩትን ለእነዚያ ለአመኑት በጠላትነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የበረቱ ሆነው በእርግጥ ታገኛለህ።››
(ማዒዳህ 82) በርግጥም ጌታየ እዉነት ተናገረ

......እዛም እንደገባሁ ቤተሰቦቹ ጥሩ አድርገዉ አስተናገዱኝ ትምህርት ቤትም ገባሁ ነገር ግን በአንዴ እማየ ናፈቀችኝ እኔጃ ሁሉም ነገር አስጠላኝ በዛ ላይ የነሱን ቋንቋ አልችልም ጨለማ መስሎ ታየኝ ጃርጂን ወደ ሀገሬ እንዲመልሰኝ ጠየቁት....

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science
7.8K views04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ