Get Mystery Box with random crypto!

መራራ እዉነት ክፍል ....... ሰሚራ ሽኩር .... ከሱሚ ጋር በፍቅር አብረን መኖር | ISLAMIC SCHOOL

መራራ እዉነት
ክፍል

....... ሰሚራ ሽኩር


.... ከሱሚ ጋር በፍቅር አብረን መኖር ጀመርን ያየን ሁሉ ይቀናብን ነበር በጣም እወዳታለሁ እሷም ትወደኛለች አምናታለሁ ታምነኛለች ሁሌም በምንም ተአምር ላንለያይ ዘመን በማይሽረዉ በጌታችን ቃል ምለናል
....ከህመሟ ልታደጋት ብጠጋት በፍቅሯ ሳበችኝ የአላህ ነገር ይገርመኛል ሂወቴን ፤ህልሜን አጠለሹት ብላ ስታማርር አላህ ሰበብ አድርጎ አገናኘን በርግጥም የኛ ጌታ የተሻለ ነገር ሊሰጠን እንጂ እኛን በምንም ነገር አይጎዳንም !
.....ከሱሚ ጋር ከተጋባን በሁለተኛ አመታችን እኔ የሴት ልጂ አባት ሱሚ የሴት ልጂ እናት ለመሆን በቃን ቤታችን ይበልጥ ሞቀ በደስታ ደመቀ ሴት ልጂ በመሆኖ በጣም ደስ አለኝ የናቴ ምትክ !

.....አሁን እየጨነቀኝ የመጣ የሲስተር ሀዋ ነገር ነዉ ምኗንም ማወቅ አልቻልኩም በቃ ስታየኝ እንደደመኛዋ ነዉ
ሱሚን ለማየት እንኳን ፍቃደኛ አይደለችም ለምን?አላቅም
ያች የማቃት የዋህ ለሰዉ አዛኟ ሲስተር ሀዋ አልመስልህ አለችኝ

በዚህ መሀል ግራ ገብቶኝ ሱሚ በወለደች በሁለት አመቷ ሲስተር ሀዋ ከድሮዉ ይበልጥ ትቀርበኝ ጀመር አይዞህ ሚስትህ ስለወለደች ብቻዋን እንዳትሆን ሂድላት ያንተን ተራ እኔ እሸፍንልሀለሁ" ትለኝ ጀመር እኔም የዋህነቷ እየገረመኝ ይበልጥ እየቀረብኳት ሄድኩ ከለታት በአንዱ ቀን የኛ ሆስፒታል ሌላ ሀገር ቁጥር ሁለት ሆስፒታል አስገንብቶ ለሁላችንም ጥሪ ተገደረልን እኔ ደግሞ የሆስፒታሉ ዋና አስተባባሪ ስለነበርኩ መቅረት አልችልም ለመሄድ ወስኘ በማግስቱ እንደምመጣ ለሱሚ ቃል ገብቸላት እሷም በስስት አይኖቿ እየተመለከተች ስማ ሸኘችኝ እኔ ከሲስተር ሀዋና ከሌሎች ጓደኞቸ ጋር ስንጓዝ ዉለን ቀን ወደ ሰባት ሰአት አካባቢ ድክም ብሎን አዲሱ ሆስፒታል ደርሰን ወደ ዉስጥ ገባን ሻዉር ወስደን አዲሱን ሆስፒታል ስንጎበኝ ቆይተን በስብሰባዉ ታድመን ፕሮግራሙ ስናከብር ካመሸን ቡሀላ የራት ግቤዣ ነበረን ብዙ መጠጦችና ብዙ ምግቦች በየአይነት ቀርበዋል ሲስተር ሀዋ ከሁል ጊዜዉ በተለየ ዘንጣ ተዉባ የራት ግቢዣዉ ላይ መጣችና አጠገቤ ተቀመጠች ከዛ መጣሁ ብየ ሱሚ ላይ ደዉየ ራት እንደበላች ካረጋገጥኩ ቡኋላ እኔም ልበላ ወደ ተዘጋጀዉ ማአድ አቀናሁ ሲስተር ሀዋ ምግቡንም መጠጡንም ከምን ጊዜዉ በሰሀኔ አድርጋ እንደጠበቀችኝ አላቅም እኔ የተቀመጥኩበት የነበረዉ ወንበር ላይ ተቀምጧል ከዛ ብላ እያለች ሰሀኑን ወደ ጠረፒዛየ አስጠጋችልኝ መጠጡንም/የተከፈተ እስፕራይት ጠጣ አያለች ሰጠችኝ እኔም ስበላ ስጠጣ ስስቅ ስጫወት አምሽቸ ነበር"

እማየ እኛ ወደተቀመጥንበት ክፍል መጣችና" በፈገግታ ሀናኔ እስካሁን ወሬቹህን ናፍቆታቹህን አልተወጣቹህም እንዴ?" አማኔን በአይኑ እንባዎች ሞልተዋል የሆነ የሚያሳዝን ነገር እየነገረን መሆኑ ገብቷት ነዉ መሰል "ዊይ በሉ ተጫወቱ ቤቱን ታፀጂዋለሽ ብየ ነበር በቃ ተይዉ እኔ አፀደዋለሁ ባይሆን ዝም ብለሽ ከምትቀመጭ የአባትሽ ልብሷች በሻንጣ እንደሆኑ ናቸዉ ደሞ አልታጠፉም ቁምሳ ሳጥኑ ላይ አጣጥፈሽ ክተችለት የአማኔም አብሮ አለ የታጠበዉንና ያልታጠበዉን ለይዉ ከአ.አ እንደመጣ ማንም አላስተካከለዉም" አለችኝ እኔም አማ ችግር የለዉም ቤቱን ላፅዳና አጣጥፌ ቦታዉ እመልሳለሁ አሁን ግን ቆይ አልኩ የአማኔን ታሪክ ለመስማት በጓጓ አንደበቴ እማ እሽ መቸ ስትል ጠየቀችኝ ትንሽ ብቻ ጠብቂኝ "ሀናኔ አሁን ጓረቢቴቸ አማንን ሊያዩ ይመጣሉ በቃ አንች ልብሱን ከሻንጣዉ አዉጥተሽ አጣጥፊዉ ቤቱን እኔ አፀደዋለሁ አለችኝ ወይ እማ እኔ አፀደዋለሁ አ.አ ይዘዉት የሄዱትን ሻንጣ ከሳሎን ቤት ይዘዉ መጣችና ሰጠችኝ አማኔ አንች አጣጥፈሽ እስከምትጨርሽ እኔ ኡዱ ላድርግ ስመለስ ታሪኩን እጨርስላቹሀለሁ እያለ ወጣ አይኑ አብጧል ፊቱ ፍም መስሎል ለማየት ያስፈራል እኔም ግራ ገብቶኝ እሽ ቶሎ ተመለስ እንጠብቅሀለን ብየ ልብሱን ከሻንጣ እያወጣሁ አጣጥፌ ወደ ቁምሳጥኑ ማስገባት ጀመርኩ


......ከመሀል አንድ የተጠቀለለ ፌስታል ላይ አይኔ አረፈ አይ አባቢ ይሄን ደግሞ ምን ሊያደርግ ይሆን ሻንጣ ዉስጥ ያስገባዉ ደግሞስ ምንድን ነዉ ብየ ፌስታሉን ስከፍተዉ የአማኔ መድሀኒት ነዉ ኧረረ የአማኔ መድሀኒት ተቀይሮል በፊት ነጭ የሽሮብ የምትመስል እቃ ዉስጥ ነበር መድሀኒቱ ያለዉ አሁን የራሱ ማሸጊያ እንደማንኛዉም አይነት መድሀኒት ነዉ እስኪ ብየ መድሀኒቱን ከጀርባዉ ከግልባቡ ሳነበዉ ግማሹ የአእምሮ ግማሹ የHiv ነዉ የሚለዉ መቸም የህክምና ተማሪ መድሀኒት ሲያይ መድሀኒቱን ለማወቅ እጁን ይበለዋል ከዛ ግራ ገባኝ አባቢ ተሰስተዉ ሰጠዉት ይሆናል ብየ መድሀኒቱን ይዤ ወደ አባቢ እሮጥኩ ሂጀ ነገርኩት አባቢ በኔ ማስተዋል ይደሰታል ብየ ስጠብቅ ያላሰብኩትን ለመዋጥ የሚከብድ ለማመን የሚያስደነግጥ መራራ እዉነት ነገረኝ እንደ
እንጨት ደርቄ ቀረሁ ማመን አቃተኝ ለካ ሰዉነቱን የሚያጥበዉ መድሀኒቱን የሚሰጠዉ አባቢ ብቸዉን ነበር እማን መድሀኒቱን ለአማን ስጭዉ የሚላት በጣም ስራ ሲበዛበት ከሀቅሙ በላይ ሲሆን ብቻ ነበር ግን ደግሞ አባቢ ሁሌም ስልነገሮችን ከአማን አጠገብ አንሱ ይለን ነበር ደጋግሞ እና አማን.....ቆይ እሽ አባቢ እስከዛሬ የደበቀን ለምን አማኔን እንዳንርቀዉ የአማኔን ሞራል ለመጠበቅ ወይስ ለምን ለነገሩ እስከዛሬ በነገረኝ እኔም በሱ ፍቅር ባልተሰቃየሁ ነበር ተወሳሰበብኝ ከመሀል አባቢ መድሀኒቱን ከጀ ወሰደና መድሀኒቱን እየፈታ በሽሮብ እቃ ማድረግ ሲጀምር ለምን ብየ ጠየቁት አሀ ለምን አደርገዋለሁ እናታቹህ እንደሆነች ታቃለች ነግሬታለሁ ለናንተም ያልነገርኳቹህ አማኔን እንዳትርቁት በእብደቱ ላይ ሞራል የሚነካ ንግግር እየተናገራቹህ አእምሮዉን እንዳትጎዱት.....ብቻ በብዙ ምክንያት ደብቄቹሀለሁ አሁን ግን በቃ አማኔም ተሽሎታል እወቁ አለኝ የምሰማዉን አላምን አልኩኝ ሰማይ ምድሩ ተደበላለቀብኝ ከመሀል ሪሀና መጣችና ሀናኔ ነይ አማኔ ታሪኩን ሊቀጥልልን ነዉ ብላ ጎትታ ወሰደችኝ የምን ታሪክ አልኳት በጣም ደንግጫለሁ አካሌ እዚህ ይሁን እንጂ ነፍሴ ከአካሌ ተለይቶ ተጉዟል ሪሁም የአማኔ ነዋ ስትለኝ አሀ እሽ ብየ ባልሰማም ብሰማም እየተርበተበትኩ ተቀምጨ ማዳመጥ ጀመርኩ


..... አማኔ ታሪኩን ካቋረጠበት " ምግቡን ሲስተር ሀዋ ሰጣህ በልተህ ጠጥተህ ከዛስ" ሪሀና ጠየቀች አማኔም "የማስታዉሰዉ ነገር የለም ጥዋት ስነሳ ራቁቴን ከሲስተር ሀዋ ጋር አንድ አልጋ ራሴን አገኘሁት የማየዉን አላምን አልኩኝ በህልሜ ይሁን በእዉኔ ብቻ አላቅም መጫህ ጀመርኩ ሲስተር ሀዋም "አቦ አትጩህብኝ ልተኛበት ምን ታካብዳለህ አለችኝ" ኧረ ማበዴ ነዉ ምን ላርግ ራሴን ጠላሁት የዛኔ ምድር ተዉጣ ብትዉጠኛ እንደኔ የታደለ ባልኖረ ነበር


ትዝ ሲለኝ ሲስተር ሀዋ የ Hiv በሽተኛ ናት ከዚህ ቡኋላ ምን ልሁን አላቅም ወዴት ልሂድ አላስታዉስም ብቻ ሱሚን ሳስታዉስ ታዛዝነኛለች ላንለያይ ምለን ነበር ምን ዋጋ አለዉ ያች የሰዉ አዉሬ ተጫወተችብኝ!......"

አማኔ ማልቀስ ጀመረ እኔም እንባየን መቆጣጠር አልቻልኩም "በዚህ ጊዜ ሱሚ አግባታ ወልዳ ጥሩ ሂወት እየኖረች ይሆናል ወይም ቃሌን ብላ እኔን በተስፋ እየጠበቀችኝ ይሆናል ብቻ አላህየ የሱሚን ነገር አደራ አንተዉ ከክፉ ነገር ጠብቅልኝ" ያረብ አያለ እጁን ወደ ላይ ወደ ጌታዉ አነሳ......

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል
Join

t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science