Get Mystery Box with random crypto!

መራራ እዉነት ክፍል ..... ሰሚራ ሽኩር ...አማኔ ማልቀስ ጀመረ በዚህ ጊዜ ሱሚ አግ | ISLAMIC SCHOOL

መራራ እዉነት
ክፍል

..... ሰሚራ ሽኩር

...አማኔ ማልቀስ ጀመረ በዚህ ጊዜ ሱሚ አግብታ ወልዳ ጥሩ ሂወት እየኖረች ይሆናል።
ወይም ቃሌን ብላ እኔን በተስፋ እየጠበቀችኝ ይሆናል ብቻ አላህየ የሱሚን ነገር አደራ አንተዉ ከክፉ ነገር ጠብቅልኝ ያረብ እያለ እጁን ወደ ላይ ወደ ጌታዉ አነሳ...

....... ለማመን የሚከብድ መራራ እዉነት ሆነብኝ ታሪኩ ከልቤ አዘንኩ አሁን ይሄ ሚስኪን ምን አደረገኝ ብላ ነዉ አጠጥታ እንዲያብድና የ Hiv በሽተኛ እንዲሆን ያደረገችዉ እንደዛ ሰዉ ሁሉ ሲርቃት አማኔ ስለቀረባት ወይስ ስላገባና ስለወለደ ቅናት...ነዉ እንዲህ እንድትጨክን ያደረጋት ብታቀዉ ነሮስ አማኔ ለሷ ከወንድም ከሁሉም በላይ ነበር ምን አይነት ጭንቅላት ቢኖራት ነዉ ይሄን ያሳሰባት ያረብ አሁንም የስራወን እንዳታጠዉ አምርሬ ረገምኳት በዚህ ስሜቴ አጠገቤ ብትሆን ብየ አሰብኩ የምገላት መሰለኝ

...እና የአማኔ ማበድ ስበቦ እሷ ነበረች ማለት ነዉ እሷን ብሎ ዶክተር ገደል በገባች ምናለ በሂወቴ አንዴ አግኝቻት በሰደብኳት...ከራሴ ጋር አወራ ጀመር

አማኔ ግን መጨረሻዉ ምን ይሆን ቤተሰብን አይፈልጋቸዉም እንደዉም በሂወት እንደሌለ ሰዉ በፍቅራቸዉ መጎዳትን ይመርጣል እነሱ እሱን ካዩ ቡሀላ የሚጎዱ ይመስለዋል ብቻ ዉስብስብ ነዉ በዛ ላይ አማኔ የHiv....በሽተኛ ነዉ አሁን አላህ ብሎትስ ቢገናኙ ብየ አሰብኩ አይ ባይገናኙ ይሻላል ከተገናኙ ሁለቱም ይጎዳሉ አልኩ።
... ግን ምኑ ይታወቃል የሚፈጠረዉ ነገር አይታወቅም!
ቢያንስ የአማኔን ልጂና ሚስቱን እኔ ባቃቸዉና ለአማኔ ልጁን ባሳየሁትና በተደሰተ ስል አሰብኩ ግን እንዴት ከአማኔ አድራሻቸዉን ልቀበል ብዙ መፍትሄዎችን አሰብኩ ነገር ግን ምንም መፍትሄ አላገኘሁም ምን ዝም ብየ ብጠይቀዉ አልናገርም ሊለኝ ነዉ እንኳን ያሉበትን ሀገር ታሪኩንስ ነገረኝ አይደል ስል አሰብኩ.....


አማኔ ግን በፊት የት ሆስፒታል ነበር የምትሰራ ልጂህና ሚስትህስ የት ነቸዉ ያሉት ስል ጠየቁት አማኔም ቆጫ ብሎ "ምን ያድርግልሻል እኔ በሂወት እንዳለሁ አንድም ሰዉ እንዲያቅ አልፈልግም በቃ ተይኝ ሳልፈልግ ታሪኬን ነግሬሻለሁ ከዚህ በላይ ግን አልችልም በቃ አልችልም"
... እያለቀሰ በእዝነትና በልቅሶ ብዛት በደከሙ አይኖቹ አስተዛዝኖ ነገረኝ
እኔም ኧረ አማኔ አብሽር እኔም እንድትገናኙና አንድ ላይ ላትሆኑ ተያይታቹህ እንድትጎዱ አልፈልግም! ደሞኮ አማኔ እስከዛሬ ሱሚም አግብታ ወልዳ ይሆናል እንደዉ ልጂህን ማግኘት ብችልና ይዠልህ ብመጣ....ብየ ነበር በቃ ተወዉ ብየ አዝኘ ተነሳሁ


.....አማኔም በልጁ ናፍቆት ስለተጎዳ ሂጀ ይዠለት የምመጣ መሰለዉ አቅማማና "እንግዲያዉስ ማግኘት ከቻልሽ በአካል ማምጣት ሞክሪ ግን ሱሚ ልጆን ስጣጠዉ እንዳትጎዳብኝ ደሞ አንድም ነገር ስለኔ ሳትተነፍሽ በሆነ ነገር አታለሽ/ምክንያት ፈጥረሽ ለአንድ ቀን ብቻ የልጀን አይን ልየዉ በአካል ካልቻልሽ ደግሞ ፎቶቸዉን ልለምንሽ ምን ያህል እንደናፈቁኝ ብታቂ"....

አንተ ብቻ ያሉበትን ቤታቹህን ንገረኝ ብየ አድራሻ ተቀበልኩት አባቢን በሶስት ቀናት ዉስጥ እንደምመለስ ነግሬዉ ፈቅዶልኝ እማየ መርቃ ሁሉም በደስታ ሸኙኝ

....ሱሚንና ልጇን ላግኛቸዉ አላግኛቸዉ የማቀዉ ነገር የለም በዛ ላይ ሱሚ አግብታ ይሆን ....ጨነቀኝ እሽ ባገኛቸዉስ ምናቹህ ነኝ እላቸዋለሁ ምን ብየስ የአማንን ልጁን ይዠለት እሄዳለሁ ተወሳሰበብኝ ያረብ!አንተዉ አቅልልልኝ ብየ ዱአየን አደረኩ።

....ያለኝ ሀገር ያለኝ ቦታና ቤት በነገረኝ መሰረት ሄድኩኝ ቤቱ ተደራራቢ ሶስት ፎቅ ነዉ አይ ቤቱን ተሳሳትኩ መሰል ብየ ተመለስኩ በድጋሚ የሰጠኝን አድራሻ ሳይ አልተሳሳትኩም ቤቱ የራሱ ነዉ ተገረምኩ አማኔ በጣም ሀብታም ነበር ማለት ነዉ ስል አሰብኩ

....ቁሜ ብዙ ካሰብኩ ቡሀላ በሩ ላይ የተገጠመዉን ደዉል ነካሁት ወድያዉ ቆንጂየ ልጂ በሩን ከፈተችልኝ ሱሚ ያላት መሆኖን ለማወቅ ጊዜ አልፈጀብኝም እንዳላትም አፍንጫዋ ቀጥ ያለ ቀጠን ያለች የምታምር እንስት ናት ግን ቀይ አይደለችም ትንሽ ጠቆር ያለች ነበረች...ምናልባት ናፍቆቱ ይሆናል እንዲህ ያጠቆራት እያልኩ ሳስብ "ማን ነሽ ማንን ፈልገሽ ነዉ የመጣሽዉ!" ስትል ጠየቀችኝ ማን ልበላት ምን ልመልስ....

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science