Get Mystery Box with random crypto!

መራራ እዉነት ክፍል ........... ሰሚራ ሽኩር ......ምን አልባት ናፍቆቱ ይሆናል | ISLAMIC SCHOOL

መራራ እዉነት
ክፍል

........... ሰሚራ ሽኩር

......ምን አልባት ናፍቆቱ ይሆናል እንዲህ ያጠቆራት እያልኩ ሳስብ ማን ነሽ?ማንን ፈልገሽ ነዉ የመጣሽ ? ስትል ጠየቀችኝ ማን ልበላት ምን ልመልስ ግራ ገባኝ
.....እእእእእ ያማን ያማን ምንልበል በቃ ያማን ዘመድ ነኝ ብየ ብገላገልስ አልኩና እዉነት ለመናገር ልክ እንደህቴ እንደሪሁየ የለለ አስመሳይ ነኝ እንድታምነኝ የአማን ዘመድ ነኝ
ዉይ አታቂኝም እንዴ የአክስቱ ልጂ ነኝ አማኔ ካየኝ ያቀኛል አማኔን ጥሪልኝ እሱን ለአንድ ጉዳይ ፈልጌዉ ነዉ አልኳት

.... ልብ አለማለቷ ነዉ እንጂ ዉሸቴን እንደሆነ ትንሽ ይለይ ነበር ያዉ መንተባተብ ፊቴን ማላብ እየዋሸሁ መሆኑን ያስታዉቃል።
እሷም "አማኔ አማኔ...." ምን ትበለኝ አይ የታመመዉን ማገገም የተሳነዉን ቁስሏን ነከሁኝ መሰል ከአይኖቿ እንባ እየወረዱ እዝን ብላ "ለመሆኑ አንች ማን ነሽ" ስትል ጠየቀችኝ ስሜ ሀናን ይባላል አልኩና ዘመድ መሆኔን እንድታምን አማን ስለዘመዶቹ የነገረኝን ታሪክ አጣፍጨ ነገርኳት እሷም እዉነት ዘመድ ብትሆንነዉጂ ይሄን ሁሉ ታሪክ ከየት ታቃለች እያለች የምታስብ ትመስላለች ዘመድ መሆኔን እርግጠኛ ስትሆን ነይ ግቢ ወደቤት ብላ ካስገባችኝ ቡኋላ ምግብ አቀረበችልኝ አይ ሱሚ በልተሽ መሞቱን ብታቂ ይሻላል በበዶ ሄድሽ ሀዘኑን አትችይዉም ብላ ይሆን ስል አሰብኩ መቸም በሂወት እንዳለ አታቅም ማን ይነግራታል! አይ እዱንያ ፈተናሽ መብዛቱ ኑሮሽ መምረሩ አታላይ የዉሸት ኑሮ ደስታሽ ትንሽ ሀዘንሽ ብዙ ዉስብስብ መራራ ኢጭ!!!


....ለማንኛዉም የመጠሁበት አላማ ሊሳካ ነዉ መሰል አላቅም ወደ ሱሚ ጠጋ አልኩና አማኔ አይመጣም እንዴ እስኪ ደዉይለት እኔ ለመሄድ እቸኩላለሁ ጉዳይ አለብኝ አልኳት ሱሚም "እእእእእእ እማኔ አማኔ.." እንባዋ እንደጎርፍ መዉረድ ጀመረ ምን ብላ ትንገረኝ ሆስፒታል ሊያስመርቅ እንደወጣ አልመጣም ወይስ ሞተ ብላ ግራ በተጋባ በናፍቆት በተቆራረጠ ድምፅ "ሀናን አማኔ ሀናን አማኔ በሂወት የለም! ከዚህ የተሻለ ቦታ ሂዷል በቃ ሙቷል አማን ሞተ አማን ጥሎን ሄደ" ....እሪ ብላ ማልቀስ ጀመረች

....ወይኔ ጉዴ ምን ልበል እኔዉ እንድትነግረኝ ጠይቄ እኔዉ ደነገጥኩ ሙቷል ብላ ነዉ ያሰበች ለነገሩ እንደዚህ እየተዋወዱ በሂወት ቢኖር ጨክኖ ሳያየኝ ከኔ እርቆ መኖር አይችልም ብላ ስለምታስብ ነዉ ሙቷል የምትል
እይ መኖሩን ባወቅሽ ስል በዝነት አየኋት በፍቅር እንደተጎዳች ማንም አይቶ ይመሰክራል።

እኔም ወደድኩት እላለሁ አይ ሀናኔ ሱመያን ሳያት ፍቅር ምን አንደሆነ ገባኝ ጠቁራለች በሱ አሳብ በአማኔ ናፍቆት ይሆናል ሚስኪን እያልኩ ሳስብ በአንዴ ፊቴ ተቀያየረ በጣም ተናደድኩ ደነገጥኩ ግራ ገባኝ

.......አንድ በግምት ስድስት አመት የሚሆናት የምታምር ህፃን "ኡሚ ኡሚየ" እያለች የተቀመጥንበት ክፍል መጣች አማኔን ነዉ የምትመስል ሱሚም እንባዎቿን ጠራርጋ "መጣሽልኝ ሀያቴ" አለችና መጣሁ ብላ ወደ ዉስጥ ገባች ትንሽ ቆይታ "አይዞሽ ተጫወች ሙሀመድ ላይ ደዉየለታለሁ አሁን ይመጣል" ..... ለወሬዋ ቦታ አልሰጠሁትም ያችን ህፃን እየተመለከትኩ የአማኔ ልጂ ናት ወይስ ብየ አሰብኩ አወ የአማኔ ልጂ ናት እሱን ነዉ የምትመስል አልሀምዱሊላህ

አይ አሁን የአማኔ ወንድም ከመጣ ጉዴ ፈላ በቃ ዘመዳችን አይደለችም ይል ይሆን ቢል በማስመሰል ተክኛለሁ ማሳመን አይከብደኝም ስል ራሴን አረጋጋሁ ከቆይታ ቡሀላ አንድ የአራት አመት ልጂ እየወደቀ እየተነሳ እኛ ወዳለንበት ሳሎን ቤት መጣ አሚሬ ተነሳህ የኔ ልጂ አለችና አቅፋ ምግብ መስጠት ጀመረች

....ያረቢ ምን እየሆነ እንዳለ ግራ ገባኝ ቆይ አግብታ ነዉ ስል አሰብኩ ለነገሩ አራት አመት ሙሉ ሳታገባ እሱን መጠበቅ ከባድ ነዉ እንኳን አገባች አማን በሂወት እንዳለ ብነግራት ትዳሯን ማበላሸት ነዉ ለነገሩ አማን በሂወት እንዳለ ብታቅ የHiv በሽተኛ ስለሆና የመገናኘት እድላቸዉ 0% ነዉ........ ብዙ አሰብኩ

.... እንዲሁ ሳስብ የቤት መኪና ይዞ የአማን ወንድም ሙሀመድ መጣና ተተዋወቅን ነጋዴ ነዉ አማን እንዳለዉም ሙሀመድ ትንሽ ጠቆር ማለቱ ነዉ ከአማን የሚለየዉ እንጂ መንታ ነዉ የሚመስሉት።
.....ዘመዳቸዉ እንደሆንኩ ሱመያ ነገረችዉ
ዘመዳችን አይደለችም ይላል ብየ በፍራት አይን አይኑን ሳይ "እይ የኔ ነገር ሁሌም ስራ ስለምዉሉ ዘመድ ይኑረን አይኑረን የማቀዉ ነገር የለም በይ ተንግዲህ እንደዋወላለን አትጥፊ" ብሎ ስልኩን ሰጠኝ ።

.... አልሀምዱሊላህ በጣም ጨንቆኝ ነበር
በቃ ልሂድ እየመጣሁ እዘይራቹሀለሁ ብየ ተነሳሁ ምን አደርጋለሁ የሱመያን ባለቤት ለማወቅ ለማየት ጓጉቸ ነበር ብጠብቅ ብጠብቅ አልመጣም ጊዜዉም እየመሸ መጣ ልሂድ ብየ ተነሳሁ አይቻልም አሉኝ ለነገሩ እኔም የአማኔን ልጂ ሳልይዝ ከዚህ ቤት አልወጣም እንደዉ ላስመስል ብየ እንጂ

ግን እሽ ብለዉ ቢሸኙኝ ወዴት አድር ነበር ቢሸኙኝ አባቢ ወንድም ቤት አድር ነበር ሁሉንም አቅጀ አስቤበት ነዉ የመጣሁ ኢንሻአላህ የመጠሁበት አላማ ይሳካል

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot


በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science