Get Mystery Box with random crypto!

መራራ እዉነት ክፍል 27 ......... ሰሚራ ሽኩር .....ሲስተር ችግር አለ ብየ ስጠይ | ISLAMIC SCHOOL

መራራ እዉነት
ክፍል 27

......... ሰሚራ ሽኩር


.....ሲስተር ችግር አለ ብየ ስጠይቃት "የምን ችግር ኧረ የለም እናተ ወዴት እየሄዳቹህ ነዉ" አለችን እኔም ወደኔ ቤት እስከምትድን ድረስ ልትኖር አንደሆነ ስነግራት ፊቷ ቲማቲም መሰለ ያ ትላልቅ አይኗ ተጎለጎለ አስፈራችኝ ሲስተር ሲስተር አልኳት "አንተ ቤትማ አይቻልም ከኔ ጋር ትኖራለች ከኔ ጋር!".....ሱመያ አላስጨረሰቻትም ከዶ.ር አማን ጋር ነዉ የምሄድ አለች አልሀምዱሊላህ ከሷ ጋር ብትል እኔጃ ሱመያ ከኔ እንድትለይ ለምን እንደማልፈልግ አላቅም የሲስተር ሀዋም ሱመያን በክፋት እይኖ አየቻት።
.... እኔ በጣም ግራ ገብቶኛል ሱመያ ከኔ ጋር ወደቤት እሄዳለሁ ካለች ጀምሮ ባህሪዋ ተቀይሮብኛል

.....ሱመያን እኔ ቤት ወስጃት ቤቴን በደንብ አሳየኋት ወንድሜ ሙሀመድንም አስተዋወቋት እሷም በደስታ ተዋዉቃ ከኛ ጋር መኖር ጀመረች ያ ፍዝዝዝ ብሎ የነበረ ቤት አሁን የወጉ ደርሶት ቡና ይፈላበት፤ ምግብ ይዘጋጂበት ...ጀመረ እኔም ሱመያን በጊዜ ሂደት እየወደድኳት ለሷ ያለኝ ስሜት/ፍቅር እየጨመረ መጣ እሷም በተመሳሳይ
.... "ከወደድከኝ ኒካህ አስረህ አግባኝ ካልሆነ ጫፌን እንዳትነካ ወጥቸ እሄዳለሁ" እያለች መቀለድ ጀመረች
እንዳለችዉም አጎቷን አስፈቅጀ ኒካህ አስረን ደስ የሚል የሚያስቀና ሂወት መኖር ጀመርን"

ምንድን ነዉ የምታወራዉ! ስል ሳላስበዉ ጫሁኩ ወይኔ ጉዴ ምን እንደነካኝ አላቅም አማኔንና ሪሀናን አስደነገጥኳቸዉ ከገቡበት የትዝታ ባህር አወጣኋቸዉ ግን ወላሂ አዉቄኮ አይደለም ምን እንደነካኝ አላቅም እንባየን ደጋግሜ ብጠርገዉም መልሶ ይፈሳል ልቤ በፍጥነት ይመታል ሰዉነቴ ይንዘረዘራል ለመናገር አፌ ይየያዛል ኢላሂ ምን ነካኝ አሁንስ የኔ ተራ ነዉ መሰል ማበዴ ነዉ ለራሴ ፈራሁ እራሴን እንደምንም አረጋግቸ ለምን እንደጮሁኩ ሲጠይቁኝ በማግባቱ ደስ ብሎኝ እንደሆነ ነገርኳቸዉ የልቤን አላህ እንጂ ማን ያቃል በቃ ለኸይሩ ነዉ ደሞስ ወንድምነቱ አይበልጥብኝም እንዴ አይ ሀናን ከራሴ ጋር ንግግር ጀመርን በመጨረሻም ራሴን አረጋገሁ በቃ አማን ሱመያን አ*ፍ*ቅ*ሮ......አግብቶታል አለቀ!!! ለኔ አማኔ ወንድሜ እንጂ ሌላ አይደለም

ከአማን ታሪክ እንመለስና ግን ፍቅር ማለት ምን ማለት ይሆን? ምንጩና መኖሪያዉስ የት ነዉ .....

እውነተኛ ፍቅር ምንጩ ልብ ነው። ጎጆውን የቀለሰው ከውስጥ ነው። ውሎና አዳሩ እዚያው
ነው። ህያው ሆኖ የሚንቀሳቀሰው በልብ አዳራሽ ውስጥ ነው። በተቀራኒው ቅብ የሆነ ፍቅር
መገኛው ከልብ ውጭ ባሉት የሰውነት ክፍሎች ነው። ለዚህም ነው እውነተኛ ፍቅር ዝንተ
ዓለም ሲቆይ ሁለተኛው በበኩሉ የሰውነት መጥፋትን ተከትሎ አብሮ የሚከስመው። ነብዩ
ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) «(አላህ) የኸዲጃን ፍቅር ችሮኛል» ብለው ሲናገሩ ለርሷ የነበራቸው
ፍቅር ምን ያህል ጥልቀት እንደነበረው ይጠቁማል። የፍቅር ክብደት ምን ያህል እንደሆነም
ያሳያል።
.
.
እውነተኛ ፍቅር ቃል ኪዳን ነው!!!ሀሰተኛ ፍቅር ማስመሰል ነው!በነብዩ ሙሐመድ
(ሰ.ዐ.ወ) ዘመን አንዲት አሮጊት ነበረች። ነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ለመጠየቅ በመጣች
ቁጥር ከተቀመጡበት ተነስተው በአክብሮትና በፍቅር የመቀበል ልምድ ነበራቸው። በነብዩ
ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አስደናቂ ባህሪ የተገረመችው እናታችን ዓኢሻ «ለዚህች አሮጊት
ለምንድን ነው የምትቆመው?» ብላ ነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ጠየቀቻቸው። «በኸዲጃ
ዘመን ትጠይቀን ነበር» ብለው መለሱላት።
.
.
በማስመሰል የታጀበ ፍቅር ፋና አልባ ነው። የሚያልፍ ጊዜ እንጂ የሚታወስ አሻራ የለውም።
ከአንጀት የሚነበብ ትዝታ ስሌሌለው የታሪክ ገፆቹ በሙሉ ወና ናቸው። የማስመሰል ፍቅር
በተፋቃሪዎች ምላሥ ላይ ማርን በአደራ እንደማስቀመጥ ነው። እውነተኛ ፍቅር ግን
በአይምሮ ላይ ተነቅሶ የሚቀር ትዝታ ነው። ለዚህም ነው ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
ወርቃማውን የኸዲጃ ዘመን ለአፍታ እንኳ ያልዘነጉት። ትዝታው በልባቸው በጥልቀት ተምሶ
ተቀብሯል። ከህሊናቸው ማህደር በክብር ሰፍሯል። የኸዲጃ ዘመን አይረሴ ሆኗል። ለርሷ
የነበራቸው ፍቅር ማራኪ ነበር !
.
.
እውነተኛ ፍቅር ህይወትን በጥበብ የምናጣጥምበት ቅመም ነው። ታላቁ ነብይ ሙሐመድ
(ሰ.ዐ.ወ) ፍቅር በነገሰበት የዓኢሻ እቅፍ ውስጥ ቁርኣን ይቀሩ ነበር። በአንድ ማዕድ
አብረው ይመገባሉ። በተከበረው እጃቸው ያጎርሷታል። ውኃ በጠጣችበት እቃ ይጠጣሉ።
ሆነ ብለው አፏ የነካበትን ቦታ ለይተው በመምረጥ በርሱ ይጎነጫሉ። ፆመኛ ሆነው
ይስሟታል። ከዚያም ወደ መስጂድ ይገባሉ። በአንድ መታጠቢያ ዕቃ ላይ ሆነው በጋራ
ሰውነታቸውን ይታጠባሉ። ምንኛ ያማረ ፍቅር ነው! ምንኛ አስደማሚ ትስስር ነው!!! ድንቅ
በሆነው የህይወታቸው ምዕራፍ ውስጥ ፍቁድ የሆነውን ተፈጥሯዊ ስሜታቸውን ማስተናገድ
በሚችሉበት ሁናቴ እያሉ ራሳቸውን ገዝተው የዓኢሻ ዕቅፍ ውስጥ ሆነው በቅዱስ
አንደበታቸው የፈጣሪያቸውን ቃል ( ቁርአን) ይቀሩ ነበር።
.
.
እውነተኛ ፍቅር መንፈስ እና አካል የተጋመዱበት ሚስጢር ነው። የስጋ አስፈልጎትና
የመንፈስ ቀለብ የሚጣመሩበት የተለየ የግንኙነት ነጥብ ነው። ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
«በዱንያ ውስጥ ካሉ (ፀጋዎች) እኔ ዘንድ ሴት እና ሽቶ የተወደዱ ናቸው። ሶላት ደግሞ
የዓይን መርጊያየ (የደስታ ምንጭ) ተደርጎልኛል» ብለዋል።
.
.
ፍቅር የሌለው ህይወት ውበት አልባ ነው። በህይወት ውስጥ የመኖር ስሜት ከነጠፈ ፍቅር
በህይወት ውስጥ መኖር አይችልም። በውበት የታጀበ ምቹ የህይወት ድባብ በሌለበት
ተጨባጭ ህያው የሆነ ስሜት መፋፋት አይችልም። እንግዲህ ይህ ሁሉ «ጥበብ»
ይጠይቃል። ጥበብ በፍቅር ውስጥ ጥንዶችን የሚያገናኝ አምባሳደር ነው። ሁለት የህይወት
አጋሮችን የሚያስተሳስር ታማኝ ልዑክ ነው። ጫፍ እና ጫፍ የነበሩ አካላትን የሚያገናኝ
ድልድይ ነው


ግን የአማን ታሪክ ትንሽ ቢያስከፋኝም ቢሰሙት የማይሰለች ጣፋጭ ታሪክ ነዉ እኔጃ ብቻ የሱን ታሪክ ስስማ ሁሉ ነገሩ ያስገርመኛል
ታሪኩ ደስ ብሎኛል የታሪኩ መጨረሻ እንደሚያምር ተስፋ እያደረኩ ወደ ታሪኩ ልመልሳቹህ አማን ቀጠለ
......"ከሱሚ ጋር በፍቅር አብረን መኖር ጀመርን ያየን ሁሉ ይቀናብን ነበር በጣም እወዳታለሁ እሷም ትወደኛለች ታምነኛለች አምናታለሁ ሁሌም በምንም ታአምር ላንለያይ ዘመን በማይሽረዉ በጌታችን ቃል ምለናል

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot
.
.
በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል
Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science