Get Mystery Box with random crypto!

መራራ እዉነት ክፍል 26 ....... ሰሚራ ሽኩር .....እስከሚሻላት አብራን ብትኖር ብየ አ | ISLAMIC SCHOOL

መራራ እዉነት
ክፍል 26
....... ሰሚራ ሽኩር


.....እስከሚሻላት አብራን ብትኖር ብየ አሰብኩ ግን እሷ ከወንድ ጋር ለመኖር ፍቃደኛ ትሆን አይመስለኝም እንደዉም ሴት መስየ የቀረብኳት እኔ መሆኔን ብታቅ ምን እንደሚፈጠር ማሰብ ከባድ ነዉ እሽ የት ላድርጋት የት ልጣላት ብዙ አሰብኩ ምን አልባት እየተሻላት ስለሆነ ምንም አትለኝም ብየ እንደድሮዉ ሴት ሳልመስል ጋዉኔን ለብሸ ገባሁ "ዉጣ ዉጣ ዉጣ".... እያለች መንዘርዘር ጀመረች

....ሁኔታዋን ከዉጭ ሁና ስትከታተል የነበረችዋ ሲስተር ሀዋ ፈጠን ብላ መጣችና "ዶ.ር ሂድ እኔ አለሁ" አለችኝ ሱመያም አይ "ሽቲ የምትለብሰዋን ዶ.ር ጥሪልኝ እኔ ከሷ ዉጭ ማንንም አልፈልግም" አለች ሺቲ የምትለብሰዋ እኔን ማለቷ ነዉ


.....ሴት ለመምሰል ሽቲ የምለብስ እኔ መሆኔን ባወቅሽ እያልኩ አሰብኩ እሷም "ዶ.ር ዉጣ ዉጣ ሺቲ የምትለብሰዋን ስልክ የምትሰጠኝን ይዘሀት ና!" ትእዛዝ ነዉ መሰል
.....መጣለችኮ አልኳት "የት መቸ ሲስተር ሀዋን አላልኩህም ያች ሁሌም እየገባች ምግብ የምትሰጠኝን" አለች ካልመጣች ብላ ስትቀዉጠዉ ሲስተር ሀዋ እኔ እንደነበርኩ ለሷ ብየ ሴት እመስል እንደነበረ በደንብ አስረዳቻት እኔ አፍሬ አንገቴን ደፍቸ ከክላስ ወጣሁ።


ሱመያም ተከትላኝ መጣችህ "ስማ የምታድኑ እናንተ፤ የምታቆስሉ እናንተ፣ የምታስለቅሱ ፤የምታስቁ እናንተ፤የምትወስዱ የምትመልሱ፤የምትፈርዱ የምትሽሩ የምትጥሉ የምታነሱ እናንተ... በቃ ሁሉም ነገር በእጃቹህ ነዉ ስትፈልጉ የፈለጋቹሀትን ሴት ትጫወቱባታላቹህ ሲበቃቹህ እንደሸንኮራ መጣቹህ ትወረዉሯታላቹህ!!!
....ቆይ እኛ ሴቶች ምን አረግናቹህ ምን ብንበድላቹህ ነዉ የስቃይን ጥግ የምታሳዩን እእእ መልስልኛ ..."

ምን ልመልስ አንገቴን አቀረቀርኩ አሳዘነችኝ ሱመያ ተረጋጊ ብየ አረጋገኋት።
ሱሜ ስሚኝ በርግጥ ወንዶች ብዙ በደል አድርሰዉብሽ ሊሆን ይችላል አቃለሁ ነገር ግን እነሱ ሌላ ሰዉ ሌላ ወንድ እኔ ደግሞ ሌላ ሰዉ ሌላ ወንድ ነኝ።
ከዚህ በፊት በገጠመሽን እያስታወሽ ሀሉንም ሰዉ በአንድ አትፈርጂ!
..... ስስተር ሀዋ ነግራሻለች እንዴት አድርጌ ስለጤናሽ ስከታተል እንደነበረ አይዞሽ የደረሰብሽ አደጋ ባንች ብቻ የደረሰ አይደለም አንች ከገባሽ ቡኋላ እንኳን ካንች የሚያንሱ በአባታቸዉ፤በአጎት በወንድም፤በቅርብ ዘመድ.... ስንት ህፃን ሴቶች ተደፍረዉ ገብተዋል አንች ቢያንስ በማታቂዉ ሰዉ ነዉ የተደፈርሽ አስበሽዋል ስሜቱን በቅርብ ዘመድ ብትደፈሪ እና አልሀምዱሊላህ አትይም ብየ ካረጋግኋት ቡኋላ የተደፈሩትን በተኙበት ክፍል እየሄድኩ አሳየኋት ትንሽ ከተረጋጋች ቡኋላ ይቅርታ ጠይቃ አመሰገነችኝና ልትሄድ አንድ እርምጃ ስትራመድ እህ ሳንተዋወቅ አልኳት ስሟን ቦርሳዋጋ የነበረዉ አንዱ ደብተሯ ላይ አንብቤዉ እንጂ ስለሷ አላቅም


....."ሱመያ እባላለሁ የሁለተኛ አመት የ garment enginering ተማሪ ነኝ ብላ ራሷን አስተዋወቀችኝ እኔም አማን እንደምባል ከነገርኳት በኋላ አሁንም ልትሄድ አንድ እርምጃ ስትራመድ ወዴት ልትሄጂ ነዉ ስል ጠየቋት "ከሆስፒታል እንድወጣ ትዛዝ ተሰጦኛል ወዴት እንደምሄድ አላቅም እናትና አባት የለኝም ያሳደገኝ አጎቴ ነዉ መደፈሬን ካወቀ አያስገባኝም ይገለኛል የት እንደምሄድ አላቅም እግሬ ወደሚመራኝ መንገድ እጓዛለሁ ደህና ሁን" ብላ መራመድ ስትጀምር ምን እንደነካኝ አላቅም ከኔ እንድትለይ ፍቃደኛ አልነበርኩም በቃ ሳያት ወደድኳት መሰል እኔጃ ብቻ በደንብ እስከሚሻልሽ የኔ ቤት ክፍት ነዉ መኖር ትችያለች አልኳት"

የአማንን ታሪክ እየሰማሁ ከየት መጣ ሳልለዉ እንባየ እንደጎርፍ በሁለት ጉንጮቸ ይፈስ ጀመር ምን ሁኘ ይሆን አላቅም ምን አልባት ለአማን የነበረኝ ስሜት የወንድም አልነበረም ይሆናል የልቤን ጩኸት ዋጥ አድርጌ አማን እንዳያቅብኝ ቶሎ ቶሎ እንባየን እየጠረኩ ሲያሻኝም ባልወድ በጥርሴ ፈገግታ እየተደበኩ ታሪኩን ማዳመጥ ጀመርኩ



አማኔም በትዝታ ባህር ርቆ ተጉዞ ስለነበር ለኔ እንባ ትኩረት አልሰጠዉም ሚስኪን ሪሁየ እህቴ በአማን ንግግር ደንግጣ አይን አይኔን ትመለከት ጀመር እኔም የማለቅስ በሱመያ ታሪክ አዝኘ እንደሆነ ለማስመሰል በየመሀሉ አፌን መምጠጥ ጀመርኩ ኧረ ኢላሂ! ደስታየን አጣጥሜ ሳላበቃ በሀዘን ልቤ ተሰበረ ምን አለ ታሪኩን ባላቅ ብየ ተመኘሁ አይ ዱንያ አምርሬ ረገምኳት ጩሄ አይወጣልኝ ነገር የታፈነ ጩኸት ሆነብኝ ኧረ ምን ተሻለኝ ብቻ መጨረሻዉ እንዳሰብኩት እንዳይሆን ተመኘሁና ታሪኩን ማዳመጥ ጀመርኩ አማኔም ንግግሩን ቀጠለ ...."እሷም ካቅማማች ቡኋላ ብቻህን ነዉ የምትኖር ወይስ አለችኝ
አይ አብሽሪ ከወንድሜ ጋር ነዉ የምኖር ብያት እሷም ተስማምታ ወደ ቤቴ ልንሄድ ስንወጣ ሲስተር ሀዋ በክፋት አይኖ መመልከት ጀመረች አስተያየቷ አላማረኝም ሲስተር ችግር አለ ብየ ስጠይቃት "የምን ችግር ኧረ የለም እናንተ ወዴት እየሄዳቹህ ነዉ" አለችኝ እኔም ወደኔ ቤት እስከምትድን ድረስ ልትኖር እንደሆነ ስናግራት ፊቷ ቲማቲም መሰለ ያ ትላልቅ አይኗ ተጎለጎለ አስፈራችኝ ሲስተር ሲስተር አልኳት እሷም "አንተ ቤትማ አይቻልም ከኔ ጋር ትኖራለች ከኔ ጋር!"....ሱመያ አላስጨረሰቻትም

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot
......

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል
Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science