Get Mystery Box with random crypto!

መራራ እዉነት ክፍል 25 ........ ሰሚራ ሽኩር ........ወይ ዛሬ በጣም ደስ አለኝ ግን | ISLAMIC SCHOOL

መራራ እዉነት
ክፍል 25
........ ሰሚራ ሽኩር

........ወይ ዛሬ በጣም ደስ አለኝ ግን ታሪኩን አልጨረሰልንም ዳ.ር ከሆንክ ቡኋላስ ታሪኩን ቀጥልልን ስል ጠየቁት አማኔም ታሪኬ ምንም አያደርግላቹህም ያስጠላል።
....ግን ታሪኬ ትምህርት የምታገኙበት ስለመሰለኝ እነግራቹሀለሁ ብሎ ታሪኩን መናገር ጀመረ

ዳክተር ሁኘ ስሰራ ብዙ አይነት ሰዎች፤ ብዙ አይነት ህመሞች ያጋጥሙኝ ነበረ
ሱሜንም(ሱመያ) ያገኘኋት እዚሁ ሀኪም ቤት ነበር ብሎ አዮኖች እንባን ያዘንቡ ጀመር ከብዙ አመታት በፊት የተፈጠረዉ አጋጣሚ በትዝታ እንዲህ ሲል አጫወተን

.....እሁድ ቀን ሆስፒታል አዳሪ ተረኛ እኔ ነበርኩ ታካሚዎችን እስከ ስድት(6) ሰአት ካስተናገድኩ ቡኋላ እንቅልፌን መቋቋም አልቻልኩም ቀንም በዝራ ቪዚ ስለነበርኩ ጋዉኔን ሳላወልቅ ከተቀመጥኩበት የተሽከርካሪ ወንበር ሳልነዛ እንቅልፍ ወሰደኝ ለሊት ወደ አስራ አንድ ሰአት ይመስለኛል ሁለት ወጣቶች አንድ በጣም ዉብ የሆነችን ወጣት አንዱ በእቅፉ ይዛ አንዱ ጫማዋንና ሂጃቧን ይዘዉ ዶክተር ዳክተር! እያሉ በጩኸት ወደኔ መጡ

....እኔም ከእንቅልፌ ደንግጨ ነበርና የተነሳሁ ምን ተፈጠረ አልኳቸዉ እነሱም ይችን ህፃን ተጫዉተዉባት እባክህ ፍጠን የምታደርገዉን አድርግ ስታቃስት ስትጮህ ቆይታ ከሁን ነዉ ራሷን የሳተች ሳይ የልጂቷ ፀጉር በጣም ረዥም ነዉ በልጁ እጂ ወደ ታች ወርዶል፤ መልኳ በጣም ቀይ አፍንጨዋ ቀጥ ያለ ቀጠን ያለች ልብሷ በደም የተነከረ ዉብ ቆንጆ እንስት ናት ።

እኔም በፍጥነት ግልኮስ ተክየላት እነሱ ከየትና እንዴት እንዳገኟት ጠየኳቸዉ ያገኟት ሱቢሂን ለመስገድ ከቤታቸዉ ሲወጡ መንገድ ላይ ነበር ስትጮህ የደረሱላት ማን እንደዚህ እንደተጫወተባት የሚያዉቁት ነገር አልነበረም ብቻ በጣም ጥሩ ልጆች ናቸዉ እስከምትነቃ ለሰአታት ከጠበቋት ቡኋላ ነቃች ሁላችንም አጠገቧ ነበርን ሁላችንንም አልያቹህ አለችን ሀኪም ቤቱን በዛ በለሊት በጩኸት ቀወጠችዉ።

ፈራናትና ሁላችንም ወጣን ለነገሩ ሲስተር ሀዋ አለች የኔ አጋዥ እሷ ናት ሲስተር ሀዋ ስትገባ ምንም አላለቻትም እኛን ግን ስታይ እየጮኸች፤እያለቀሰች ፊቷን አዙራ በፍራት ትንቀጠቀጠች።

....በወንዷች ከባድ ጉዳት ስለደረሰባት ወንዶች ሁሉ አንድ አይነት ነዉ የሚመስሏት ለማንኛዉም ሲስተር ሀዋ ስላለች ትንከባከባታለች አብሹሩ ብየ ያመጧትን ልጆች ወደ ቤታቸዉ ላኳቸዉ

ሪሀና "አማኔ ሲስተር ሀዋ ማን ናት" ስትል ወሬዉን አቋረጠችዉ

አማኔም "ሲስተር ሀዋ ማለት ከተመደብኩኝ ቀን ጀምራ አይዞህ የምትለኝ፤ከጎኔ ሁሌም የማትጠፋ በጣም የማዝንላት ሚስጥሯን የምትነግረኝ የምነግራት የሀኪም ቤት ጓደኛየ ናት

የሲስተር ሀዋ እናትና አባቶቿ የHiv በሽተኛ ናቸዉ ሲስተር ሀዋንም ሲወልዱ በቂ ክትትል አላደረጉላትም ነበር ሲስተር ሀዋ የHiv በሽተኛ ሆነች።
ስለሆነች ሁሉም ዶክተሮች ይርቋታል


አንድን ታማሚ ካገለልነዉ ለኛ ጥሩ አስተሳሰብ አይኖረዉም በጥላቻ በክፋት ያየናል እንደዉም አላህን የማይፈራ ከሆነ እኛንም ለተጠቃበት በሽታ ሊዳርገን ይችላል ስለዚህ እንጠንቀቅ በተቻለን መጠን አንራቃቸዉ በመጠኑ እየተጠነቀቅን እንቅረባቸዉ።

.....እኔ ግን ሲስተር ሀዋ ታሳዝነኛለች ሁሌም አብሬት እበላለሁ፣ እጠጣለሁ፣ አብሬት አዉላለሁ ፤እሷን ለማፅናናት የማላረገዉ ነገር የለኝም እንደዉም ሰዉ እሷን መቅረብ የጀመረ እኔ እዛ ሀኪም ቤት ገብቸ አብሬት ስበላ ስጠጣ ሲያዩ ነዉ
በዚህም ደስ ይላታል "በአንተ ሁሉን ነገር ረሳሁት እንደአዲስ የተፈጠርኩ መሰለኝ አማኔ ዉለታህን የምመልስ ያድርገኝ" ትለኝ ነበር እኔ ሞኙ አምናታለሁ እንደእህቴ እቀርባታለሁ፤ እረዳታለሁ ገንዘብ ከፈለገች ከፈለገችዉ በላይ በቸክ እፈርምላታለሁ ደሞዜንም በሆስፒታሉ ከሚሰሩት ከሁሉም የተሻለ ስለነበረ የሚቸግረኝ አንዳች ነገር የለም ይሄን እንተወዉና ስለሱመያ ልንገራቹህ" ሲል ንግግሩን ቀጠለ



"ሱመያን ጤንነቷን ቸክ ላረግ ስገባ ትጫሀለች ትንቀጠቀጣለች የምትገባበት ይጨንቃታል ወላሂ ከልቤ አዘንኩ ምን አይነት ሰዉ መሰል ሰይጣን ይሆን የተጫወተብሽ እላለሁ ሰዉ ስሜቱን የሚከተል ምን አይነት በግ ሁኗል አሁን ይችን ሚስኪን ጨክነዉ .....ስል አስባለሁ

የግድ ጤንነቷን መከታተል ነበረብኝ ስገባ ትጮሀለች ምን ላርግ ሳስብ ወንድ በመሆኖ ከሆነ የጠላችኝ መሆን እንጂ መምሰል ቀላል ነዉ።ለምን ሴት መስየ አልገባም አልኩና ፂሜን በትልቅ ማስክ ሸፍኘ፣ ከሱሪየ በላይ የሲስተር ሀዋን ሽቲ ደርቤ፣ እጀን ጓንት አልብሸ፤ ፀጉሬን በሂጃብ ሸፍኔ.... መግባት ጀመርኩ ሪሀና ወሬዉን አቋርጣ ተክ ብላ ሳቀች ለምን እንደሳቀች አማን ሲጠይቃት
"የምር ወንድሜ አማን ሳልኩህ ሴት ነዉ የምትመስለዉ" እኔ ታሪኩን ለማወቅ በጣም ጓጉቸ ስለነበር ከዛስ አልኩ አማንም "ከዛ ሱመያም አትፈራኝም ሴት ነዉ የምመስላት ደሞ ስልክ የላት ደዉየ ለቤተሰቦቿ የተፈጠረዉን አልናገር ቤተሰባቿም ሆኑ ጓደኛ የሚባል ይኑራት አይኑሯት የማቀዉ ነገር የለም ብቻ እየገባሁ ስለ ጤንነቷ አረጋግጨ ላወራት እፈልግና ድምፄ የወንድ እንደሆነ ካወቀች ትርቀኛለች አልና እወጣለሁ በዚህ ማሀል ስመላለስ ሳያት ምግቧን በስአቱ ስሰጣት እየተሻላት ማልቀሷን ትታ ፈገግ ማለት ጀመረች እንዳይደብራት ብየም ሲም የሌለዉ ስልክ አስቂኝ ቀልዶችና የተለያዩ ሀዲሶች የተጫኑበትን ሰጠኋት እሷም እየተሻላት ስትመጣ ሆስፒታሉ አልጋ ለሌላ ተረኛ እንድትለቅ አዘዘ የት ትሂድ ወዴት አዉጥተን እንጣላት ግራ ሲገባኝ ቤት ወንድሜ ብቻ ነዉ ያለ አብራን እስከሚሻላት ድረስ ብትኖር ብየ አሰብኩ ግን እሷ ከወንድ ጋር ለመኖር ፍቃደኛ ትሆን አይመስለኝም እንደዉም ሴት መስየ የቀረብኳት እኔ መሆኔን ብታቅ ምን እንደሚፈጠር ማሰብ ከባድ ነዉ እሽ የት ላድርጋት የት ልጣላት........

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot


በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል
Join

t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science