Get Mystery Box with random crypto!

መራራ እዉነት ክፍል ............ ሰሚራ ሽኩር .......ተመልሸ ወደ ቻይና ሂጀ | ISLAMIC SCHOOL

መራራ እዉነት
ክፍል

............ ሰሚራ ሽኩር


.......ተመልሸ ወደ ቻይና ሂጀ ስራ መጀመር ነበረብኝ ልሄድ ካሰብኩ ቡኋላ አንድ ወንድሜን ስመለስ እንደማየ ባጣዉስ ብየ ፈራሁ
ከዛ ወጀ ቻይና ልሄድ የነበርኩትን ጉዞ ሰርዠ እዚሁ ስራ ማፈላለግ ጀመርኩ በአንድ ቀን አንድ ትልቅ ሆስቲታል ዶክሜንቴን ሁሉ አስገባሁ በደስታ ተቀበሉኝ "

አላመንኩም!አማን ዳክተር ነዉ ደነገጥኩ እኔጃ ብቻ አላመንኩትም ግን ደግሞ አባቢ ያኔ አደጋ ሲያደርስ ካለ ነገር ልጁን በሂወት እንዲቆይ ሰበብ አልሆነም ደሞ ሀኪም ቤት ከ ዳ.ር ጋር ቀዶ ጥገና ክፍል ገብቶ ነበር እዛ ደግሞ ዳክተሮቹ ብቻ ነበር የሚገቡት ብሎናል



ነገሮች ሁሉ ተወሳሰቡብኝ እንዴት አልጠረጠርኩም ራሴት ታዘብኩት ግን ደግሞ አሁንም አላመንኩም ሰሞኑን ከምግቡ ይሆን ከጭንቀት ጨንጓራየን በጣም አሞኛል እንደዉም ይሄ ጥሩ አጋጣሚ ነዉ አማን ዳክተር ከነበረ ስለህመሜ በቂ እዉቀት ይኖረዋል ለነገሩ የሆድ ዉስጥ እስፔሻሊት ካልሆነ እንዴት ያቃል ምናልባትም ከአንገት በላይ ፤ የአጥንት.... እየተባሉ ዳክተሮች ሲለሚከፋፈሉ እሱ ላያቅ ይችላል ለማንኛዉም እስኪ ልጠይቀዉ ብየ ልጠይቀዉ ስል ሪሀና እማን ዳክተር ነዉ ደስ ሲል ሀናን ደስ ይበልሽ ጨንጓራየን አመመኝ ቆረጠኝ የለም አማን አለልሽ እሱ ያክምሻል ፐ በአንድ ቤት ሁለት ዳክተር እያለች ሳቀች


አማኔም "ሀናን ጨንጓራሽን ያምሽ ነበር እንዴ ቆይ ምግብ መመገብ ቀንሰሻል፤ሆድሽ አካባቢ ያቃጥልሻል....ሲል ጠየቀኝ እኔም አወ ያቃጥለኛል ምግብም ብዙም አይደለሁም አልኩት



አማኔም ይሄማ የጨጓራ ባክቴሪያ / H. pylori infection ይባላል

ሄሊኮባክተር ፓይሎሪ የሚባለዉ ባክቴሪያ የጨጓራ ኢንፌክሽን እንዲከሰት የሚያደርግ የባክቴሪያ አይነት ሲሆን ይህ ኢንፌክሽን በብዛት የሚከሰተዉ በልጅነት የዕድሜ ክልል ነዉ፡፡ ይህ ባክቴሪያ የጨጓራ ቁስለት እንዲከሰት ከሚያደርጉ ሁነኛ መንስዔዎች ዋነኛዉ ሲሆን ኢንፌክሽኑ በአለማችን ከግማሽ በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ አንደሚታይ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡

የህመሙ ምልክቶች
ብዙዎች የሄሊኮባክተር ፓይሎሪ እንፌክሽን የተፈጠረባቸዉ ሰዎች ምንም አይነት የህመም ምልክቶች አይታይባቸዉም/ላይኖራቸዉ ይችላል ፡፡ የህመም ምልክቶች የሚታይባቸዉም
የሆድ ላይ ህመም ወይም የማቃጠል ስሜት
ጨጓራዎ ባዶ ሲሆን የሚባባስ የጨጓራ ላይ ህመም
ማቅለሽለሽ ፤የምግብ ፍላጎት መቀነስ፤ በተደጋጋሚ ማስገሳት፤ የሆድ መንፋት
የክብደት መቀነስ .....ናቸዉ፡፡


ከፍተኛና የማያቋርጥ የሆድ ላይ ህመም ካጋጠመሽ
የመዋጥ ችግር ካለብሽ
• ደም የተቀላቀለበት ወይም የአስፓልት ሬንጅ የመሰለ/ የጠቆረ ሰገራ ከወጣሽ
ቀይ ወይም የቡና አተላ የመሰለ ነገር ካስታወከዎ በአፋጣኝ የህክምና ሀኪም ቤት መሄድ አለብሽ አለኝ

ገረመኝ አሁን ዳክተር እንደነበረ እርግጠኛ ሆንኩኝ ሪሀና "አማኔ ጨንጓራ ባክቴርያ እንዴት ሊፈጠር ይችላል ለኢንፌክሽኑ የሚያጋልጡ ነገሮች ምንምን ናቸዉ የማቀዉ ነገር የለም" ስትል በደንብ እንዲያብራራላት ጠየቀች አማኔም


ለኢንፌክሽኑ ሊያጋልጡ የሚችሉ ነገሮች
በተፋፈገ/በተጨናነቀ ቦታ መኖር
ንፁህ የዉሃ አቅርቦት በሌለበት መኖር
በማደግ ላይ ባሉ/ባላደጉ አገሮች/ የሚኖሩ ሰዎች፡ ንፅህናዉ በማይጠበቅ ሁኔታ ዉስጥ መኖር
የሄሊኮባክተር ፓይሎሪ ባክቴሪያል እንፌክሽን ካለዉ ሰዉ ጋር መኖር የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች ደግሞ

የደም ምርመራ
የትንፋሽ ምርመራ/ዩሪያ ብሬዝ ቴስት
የሰገራ ምርመራ ናቸዉ፡፡

ሊደረግ የሚችል ህክምና
የባክቴሪያዉ እንፌክሽን መኖሩ ከተረጋገጠ የህክምና ባለሙያ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ባክቴሪያዉን ሊያጠፋ የሚችሉ መድሃኒቶች ሊያዝላቹህ ይችላል ።

ሀናን ምንም አላለኝ ብለሽ ዝም አትበይ ሊያደርሰዉ የሚችለዉ ጉዳት/ Complications ብዙ ነዉ

ከጨጓራ ባክቴሪያ እንፌክሽን ጋር ተያይዞ ሊመጡ የሚችሉ ጉዳቶች
ቁስለት፡- የጨጓራ ባክቴሪያ የጨጓራ መከላከያ እንዲጎዳ ያደርጋል፡፡ በዚህ የተነሳ የጨጓራ አሲዱ ጨጓራ ላይ ቁስል አንዲከሰት ያደርጋል፡፡
የጨጓራ ሽፋን እንዲቆጣ ያደርጋል- የጨጓራ ባክቴሪያ ጨጓራን በመቆጥቆጥ እንዲቆጣ ያደርገዋል፡፡
የጨጓራ ካንሰር፡- የጨጓራ ባክቴሪያ ለተወሱ የጨጓራ ላይ ካንሰሮች መከሰት ዋነኛ መንስኤ ሊሆን ይችላል፡


ወይ ዛሬ በጣም ደስ አለኝ ግን ታሪኩን አልጨረሰልንም ዳክተር ከሆንክ ቡሀላስ ታሪኩን ቀጥልልን ስል ጠየቁት አማኔም ታሪኬ ምንም አያደርግላቹህም ያስጠላል።
..... ግን ከታሪኬ ትምህርት የምታገኙበት ስለመሰለኝ እነግራቹሀለሁ ብሎ ታሪኩን መናገር ጀመረ

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት

@Meh_Ani_bot

ኢንሻአላህ ይቀጥላል

Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science