Get Mystery Box with random crypto!

መራራ እዉነት ክፍል ....... ሰሚራ ሽኩር ......እዛም እንደገባሁ ቤተሰቦቹ ጥሩ | ISLAMIC SCHOOL

መራራ እዉነት
ክፍል

....... ሰሚራ ሽኩር

......እዛም እንደገባሁ ቤተሰቦቹ ጥሩ አድርገዉ አስተናገዱኝ ትምህርት ቤትም ገባሁ ነገር ግን በአንዴ እማየ ናፈቀችኝ እኔጃ ሁሉም ነገር አስጠላኝ በዛ ላይ የነሱን ቋንቋ አልችልም ጨለማ መስሎ ታየኝ ጆርጂን ወደ ሀገሬ እንዲመልሰኝ ጠየቁት እሱም"ምን ማለትህ ነዉ አንተን እዚህ ለማምጣት ስንት እንደለፋሁ ታቅ የለ ደሞስ እናትህ መርቃ የሸኘችህ ተመቸኝም አልተቸኝም ብለህ እንድትሄድ ነዉ?
.... አማን ጠንከር ብለህ ተማር እናትህ የፈለገችዉ ቦታ ደርሰህ ህልሟን እዉን አድርግላት ስማ ላንተ ሳይሆን ለዛች ሳትበላ አብልታ ፤ሳትለብስ አልብሳ፤ሲያምህ ታማ ላሳደገችህ እናት ብለህ ቆይ እኔ እያለሁስ እኔ አግዛቹህ ነበር አሁን ሂደህ በዚህ እድሜህ ምን ልሰራ ነዉ..."የትያቄ ማእበል አወረደብኝ ወላሂ ልሂድ ብየ በመጠየቄ አፈርኩ አንገቴን አቀረቀርኩ ጆርጂም አይዞህ ቋንቋዉ ከባድ ይመስላል እንጂ ቀላል ነዉ እኔ አስተምርሀለሁ አለኝ ግን የሚቻል አልመስልህ አለኝ ፁህፉ ኧረ ኢላሂ ይሄን እኔ ፅፌ ላወራዉ ነዉ እል ነበር ለካስ የሰዉ ልጂ ተአምራዊ ነዉ የማይቻል ነገር የለም ከትንሽ ጊዜ ቡሀላ በደንብ መናገርና መፃም ጀመርኩ

.....ትምህርት ቤት ብዙ ጊዜ በዘር፤በሀይማኖት....የነሱ ካልሆን ለሁሌም መጨረሻ ተሰላፊ ነን እነሱ አጥፍተዉ የምንቀጣ እኛ እኩል ዉጤት አምጥተን የሚሸለዉ እነሱ ናቸዉ ብቻ ማን እንደሀገር !ሁሉ ነገሩ ይከብዳል በተለይ ከሰዉ በታች አድርገዉ ሲያዩን ልባችን ይደማል።

.....ጆርጂ ሁሌም ይከታተለኛል ጥሩ ዉጤት እንዳመጣ ያስጠነኛል የምፈልገዉን ነገር ሳልጠይቀዉ ያሟላልኛል ከትምህርት ቤትም የተሻልኩ ተማሪ ለመሆን በቃሁ እናቴን በዱአ እረስቻት አላቅም ከተለያየን አስራ ስምንት አመት ሆነን እኔም ትምህርቴን እናቴ እንደምትፈልገዉ ዶክተር ሁኘ ተመረኩ ከሶስት አመት በፊት በጎረቢት ስልክ እየወደልኩ አንዳንዴ አወራት ነበር


.....ከሶስት አመት ቡኋላ ግን ስልኳም እቢ አለ አግኝቻት አላቅም ብቻ ሰላም ትሁንልኝ እኔም ሰሞኑን መሄዴ አይቀርም የመጠሁበትን አላማ አሳክቸ ጨርሻለሁ ብየ ጆርጂን ጠየኩት ጆርጂም በደስታ እናትህን አይተህ ትመጣለህ ብሎ እያለቀሰ ላከኝ እኔም እያለቀስኩ አመስግኘዉ ወደ ሀገሬ መጣሁ ምንገድ ላይ ልቤ መረጋጋት አልቻለም ዝም ብሎ ጭንቅ ጭንቅ ይለኝ ጀመር


.... አሁን እንዲህ አድጌ ስታየኝ ምን ትል ይሆን ስል አሰኩ ያ ሁሉ ችግር ከእንግዲህ ያበቃል ....ያረብ እናቴን በሰላም ላግኛት በጣም ንፍቅ ብላኛለች እያልኩ ወደ ቤት ገባሁ ሰርፕራይዝ ነዉ መምጣቴን ማንም አያቅም ለማየ ሂጃብ መስገጃ....ያልያዝኩት ነገር የለኝም
ለወንድሜም ብዙ ነገር ይዘዣለሁ


.... ቤት እንደደረስኩ ቤቶች ብየ ገባሁ አንዲት ሴት መጣችና ምንድን ነዉ አለችኝ እኔም ደንገጥ ብየ እማስ አልኳት ማን ነች እማ ስትል ጠየቀችኝ ግራ ገባኝ እእእእ እዚህ የነበሩት ይሄኮ የኛ ቤት ነበር እናንተ እነማን ናቹህ ወንድሜስ.....

"ቆይ አንተ የማማ ፋጡማ ልጂ ነህ" ስትል ጠየቀችኝ እኔም አወ የሷ ልጂ ነኝ "ዉይ አላህ ለጀነት ይበላቸዉ እንዴት ያሉ ጥሩ ሰዉ ነበሩ ይሄን ቤት ወንድምህ ነዉ ከሶስት አመት በፊት እናታቹህ ስትሞት የሸጠልን" አለችኝ


የምሰማዉ በህልሜ ነዉ ወይስ በዉኔ እማ አልሞተችም ትሰሚያለሽ እማ አልሞተኝም ብየ የልጂቷን አንገት ጠቅጠቄ ያዝኩት ከመሀሌ ወንድምህ መጣ ብሎ ማን እንደነገረዉ አላቅም ወንድሜ ሙሀመድ መጣና ተጨምጭሞ ማልቀስ ጨመረ እንዴት እንደለየኝ አላቅም አስራ አምስት አመት ሙሉ ተለያይተን ለነገሩ እሱ ጠቆር ማለቱ እኔ ነፃ ማለቴ ነዉ እንጂ መንታ ነዉ የምንመስለዉ።

ሙሀመድ እማየ መሞቷን ሲነግረኝ
አላመንኩም እማ መጥታቸለሁ እይኝ! እማየ እይኝ ዶክተርኮ ሆንኩልሽ! እማ ህልምሽ እዉን ሆነልሽ! እማ አቤት በይኝ! አማ ያ ሁሉ ችግርኮ በኔ በልጂሽ አሁን ሊያልፍልሽ ነዉ! እናቴ ያልፋል ብለሽኝ አልነበረ ሲያልፍ ሳታይ አማ ......ብጮህ ብነሳ ብወድቅ ከየት ትምጣ ላትመለስ ወደ ዘላለማዊዉ ሂወት ሂዳለች አላህ ለጀነት ይበላት።
እኔም ለብዙ ቀን አዘንኩ ለጆርጂም ነገርኩት አይዞህ ብሎ አፅናናኝ

....ተመልሸ ወደ ቻይና ሂጀ ስራ መጀመር ነበረብኝ ልሄድ ካሰብኩ ቡኋላ አንድ ወንድሜን ስመለስ እንደማየ በጣዉስ ብየ ፈራሁ


Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science

ማንኛዉም ሀሳብ አስተያየት
@Meh_Ani_bot

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል