Get Mystery Box with random crypto!

መራራ እዉነት ክፍል ........ ሰሚራ ሽኩር አንድ ቀን ጆርጂ እናትህን አስተዋዉቀኝ | ISLAMIC SCHOOL

መራራ እዉነት
ክፍል

........ ሰሚራ ሽኩር


አንድ ቀን ጆርጂ እናትህን አስተዋዉቀኝ ብሎኝ እማየን ላሳየዉ ይዤዉ ወደ ቤታችን አቀናሁ

እማየ ጥጥ እየፈተለች ነበር የደረስን ጭኗ ጠቁሮ ብልዝ ብሎ ጆርጂ አየዉ ...እማየም አማኔ ማን ነዉ ስትል ጠየቀችኝ እማ ጆርጂ ይባላል ከሱ ጋር ነዉ የምሰራ ብየ አስተዋወኳት ።
...... አረፍ በሉ ብላን ወደ ዉስጥ የሚበላ ነገር ልታመጣልን ሄደች ምን ልታመጣ ይሆን ብየ ተጨነኩ
.... እንጀራ በበርበሬ ይዛ መጣች ቤት ያፈራዉን ብሉ ወጥ አልሰራሁም ብላ አቀረበችልን እማ ጆርጂ በርበሬ የሚበላ አይመስለኝም ከሱ ጋር ሁሌም ሩዝ ነዉ የምበላ አልኳት ጃርጂም እየተንተባተበ በርበሬ እበላለሁ አትጨነቂ ብሎ ግድ አለግድ መብላት ጀመረ አንድ ጉራሽ በአንድ ብርጭቆ ዉሀ እያወሀደ

....የምር ጆርጂ ሰዉ አክባሪ የሰዉ ምንነት የገበዉ ስላለዉ የማይንጠራራ ከሁሉም ጋር መግባባት የሚችል ጥሩ ሰዉ ደግ ሰዉ ነዉ።

እንዲህ እንዲህ እያልን በኩንትራት የያዘዉ ፎቅ አለቀ እሱ ደስ ሲለዉ እኔ ከሱ መለየቴ ከፍኝ ወደ ሀገሩ ሊመለስ ነዉ እማየም በጣም ትወደዉ ነበር አዘንኩ ጆርጂም "አይዞህ አትዘን እኔ በጉዲፈቻ አሳድገዋለሁ ብየ ይዠህ እሄዳለሁ አለኝ ደነገጥኩ ደስታና ሀዘን ባንዴ ወረሩኝ ደስ ያለኝ ከጆርጂ ጋር ቻይና መሄዴ ሲሆን የከፋኝ እናቴን እንዴት ትቻት እሄዳለሁ የሚለዉ ነበር ......ግራ ገባኝ እማየን ነገርኳት እሷም በጣም አዘነች ነገር ግን አዛ ጥሩ የትምህርት እድል እንደማገኝ ጆርጂ ሲነግራለት ቅር ቢላትም መርቃ ሸኘችን

ቻይና ዉስጥ
....... ኢስልምናን ለመጀመሪያ ጊዜ ቻይና የደረሰው በዑመር (ረ.ዐ) ኸሊፋነት ዘመን በታላቁ ሰሃባ ‹‹ሰዓድ ኢብን አቢ-ወቃስ›› (ረዐ) እንደሆነ ይነገራል።

በቻይና የመጀመሪያውን መስጂድ ያሰራውም ሰዓድ ሲሆን ‹‹ሑዓሼንግ›› የሚባልና አሁንም በይዞታ የሚገኝ የ1300 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ መስጂድ ነው።

በአገሪቱ 80 ሚሊዮን የሚገመቱ ሙስሊሞች እንዳሉ የሚገመት ሲሆን ከህዝቡን 2% ገደማ ይሸፍናሉ።

ሙስሊሞቹ በብዛት የሚኖሩበት ቦታ ‹‹ዢንጂያንግ›› ሲባል ከአፍጋስታን፣ ፓኪስታን፣ ህንድ፣ ታጃኪስታን እና ሌሎች ጋር የሚዋሰን ሰፊ ግዛት ነው።

‹‹ዢንጂያንግ›› ቀድሞ የዑስማያ ኸሊፌት የተርኪስታን ግዛት የነበረ ሲሆን ኸሊፋው ከወደቀ በኋላ በ1949 ቻይና በሐይል ልትወስደው ችላለች። ግዛቱም ከቻይና ሰፊው ሲሆን በማዕድን የበለፀገ ነው።

ቻይና ውስጥ ሁለት አይነት ነገድ ያላቸው ሙስሊሞች ያሉ ሲሆን ‹‹ሐም›› እና ‹‹ኡግሁር›› ይባላሉ። ሐሞች ቻይናዊ ሲሆኑ ኡግሁር ደግሞ በመልካቸውም የተለዩ የመካከለኛው ኤዥያ ዝርያዎች እንደሆኑ ይታመናል።

በቻይና ሁሉም ሙስሊሞች መድሎ ቢደርስባቸው ከፍተኛ በደል የሚፈፀምባቸው ግን የኡግሁር ሙስሊሞች ናቸው።

የኡግሁር ሙስሊሞች ከሌላው በተለየ በደል የሚደርስባቸው አንደኛው በዘራቸው ቻይናዊ ስላልሆኑ ሁለተኛው ደግሞ አካባቢው በማዕድን የበለፀገ ስለሆነ መንግስቱ ህዝቡን የማጥፋት ዕቅድ እንዳለው ይነገራል።

ቻይና በኡግሁር ሙስሊሞች ላይ ከምትፈፅመው ግፍ መካከል ወላጅና ልጅን መነጣጠል፣ በማጎሪያ ካምፖች ማሰር፣ አካላቸውን መበለት፣ ሰላት፣ ፆምና ቁርኣን መከልከል፣ አልኮል ማስጠጣት፣ የአሳማና ውሻ ስጋ ማስበላት፣ መግደል እና ሌሎችንም ይፈፅማሉ።

የቻይና መንግስት ይህን ሁሉ አሰቃቂ ግፍ እየፈፀመ ድርጊቱ ‹‹ሽብርተኝነት›› አልተባለም።

በዑመር (ረዐ) ዘመን የቻይና መንግስት ለፋርስ ንጉስ መጠጊያ እንኳን ለመስጠት ኸሊፋውን በመፍራት እንቢ ማለቱ ይነገራል። ዛሬ የሙስሊም አገራት የኡግሁር ሙስሊሞች አሰቃቂ ግፍ እየተፈፀመባቸው እያዩ ከቻይና ጋር የንግድ እንቅስቃሴያቸውን እንኳን ማቆም አልቻሉም።

‹‹አይሁዶችንና እነዚያን ያጋሩትን ለእነዚያ ለአመኑት በጠላትነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የበረቱ ሆነው በእርግጥ ታገኛለህ።››
(ማዒዳህ 82) በርግጥም ጌታየ እዉነት ተናገረ

......እዛም እንደገባሁ ቤተሰቦቹ ጥሩ አድርገዉ አስተናገዱኝ ትምህርት ቤትም ገባሁ ነገር ግን በአንዴ እማየ ናፈቀችኝ እኔጃ ሁሉም ነገር አስጠላኝ በዛ ላይ የነሱን ቋንቋ አልችልም ጨለማ መስሎ ታየኝ ጃርጂን ወደ ሀገሬ እንዲመልሰኝ ጠየቁት....

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science