Get Mystery Box with random crypto!

መራራ እዉነት ክፍል ....... ሰሚራ ሽኩር ለናቴ ብነግራት አትፈቅድልኝም ሳልናገር ወደ | ISLAMIC SCHOOL

መራራ እዉነት
ክፍል

....... ሰሚራ ሽኩር

ለናቴ ብነግራት አትፈቅድልኝም ሳልናገር ወደ አንድ እየተሰራ ወዳለ ፎቅ ተሸካሚ እንኳን ቢቀጥሩኝ ብየ አመራሁ

ፎቁን በኩንትራት የያዘዉ ሰዉየ ጆርጂ ይባላል በናቱ አሜሪካዊ ሲሆን በአባቱ ቻይናዊ ነዉ ጥሩ ፀባይ አለዉ አማረኛ በደንብ ይሰማል ለማዉራት ቢከብደዉም እየተንተባተበ ትንሽ ትንሽ ያቃል ለመግባባት አይቸገርም።
....እኔም በፍራት የቤተሰቤን ችግር ነገሬዉ እዚህ ጂብሰም፤ሲሚንቶ፤ኮርኔስ የመሳሰሉ ነገሮችን...... በመሸከም እንዳመላልስላቸዉና የተወሰነች ብር ብትከፍለኝ ብየ አናገርኩት ጆርጂም "አንተኮ ገና ህፃን ነህ አትችልም" ብሎ እንቢ አለኝ እኔም ተስፋ በመቁረጥ እግሬን ዘርግቸ ቁጭ ብየ ማልቀስ ጀመርኩ ጆርጂ በኔ ሁኔታ ልብ ተንክቶ "በቃ እሽ እኔ ትንሽ ገንዘብ እሰጥሀለሁ አንተ ዝም ብለህ ተማር" አለኝ እኔ ግን አልተስማማሁም የላቤን ገንዘብ ነዉ ለእማየ ማብላት ያለብኝ አልኩት እሱም በንግግሬ ተደንቆ አንተ ህፃን አይደለምህ ትልቅ ነህ የትንሽ ትልቅ አለሽ


.....ከዛ ቀን ጀምሬ ከጥዋት ትምህርቴን ስማር እቆይና ከሰአት ከጆርጂ ጋር አዉላለሁ ምግብም አሱ ጋር እመገባለሁ ጆርጂን በጣም እወደዋለሁ እንዳአባትም ይመክረኛል፤አጋዥ መፅሀፎችን ይገዛልኛል ብቻ ደስ የሚል ፀባይ ያለዉ የዋህ ሰዉ ነዉ።

እማየ ሁሌም ከሰአት ቁርአን ቤት ቁርአን ስቀራ የምዉል ይመስላታል ካፏ የማይለየዉ የሁል ጊዜም ምክሯ ሰላትና ቁርአንህን አደራ!!!ነዉ
...እኔም ሰላቴን በሰአቱ እሰግዳለሁ ቁርአኔን ደግሞ እሁድ እሁድ ስራም ትምህርትም ስለማይኖር እቀራለሁ
አንዳንዴ ስራ ስዉል ድክም ሲለኝ ሱቢህ ሲሰገድ እየሰማሁ ለመነሳት ይከብደኛል የዛኔ እማየ በጆክ ዉሀ ይዛ ትመጣና "ትናሳለህ አትነሳም" ስትለኝ አምስት ደቂቃ አልቆይም ስነሳ"
...... ልጆችን ስናሳድግ በኢማናቸዉ ጠንካራ አድርገን ቁርአን እንዲቀሩ፤ሰላት እንዲሰግዱ ካላደረግናቸዉ ተለቀዉ እንደፈለጉ ካደጉ ቡኋላ ሲያድጉ ይስተካከላሉ ማለት ከዝንብ ማር እንደመጠበቅ ነዉ።



ኢማም አሕመድ ኢብኑ ሐንበል በእናታቸው እጅ እንዴት እንዳደጉ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ
“እናቴ ገና በ10 ዓመቴ ነው ቁርኣንን በቃሌ እንድሐፍዝ ያደረገችኝ፡፡ የሱብሒ ሰላት ሳይደርስ በፊት ትቀስቅሰኝ ነበር፡፡ በዚያ እጅግ ቀዝቃዛ በሆነው የባግዳድ ከተማ በለሊት ተነስታ ለዉዱእ የሚሆን ዉሃ አሙቃ ታቀርብልኛለች፡፡ ልብሴን ታለብሰኝና በጉፍታዋና ነሒጃቧ በሚገባ ከተሸፋፈነች በኋላ መስጂዱ ከኛ አካባቢ ራቅ ስለሚልና ጨለማም ስለሆነ እጄን ይዛ መስጂድ አድርሳኝ ትመለሣለች”
እሳቸውም አላሳፈሯትም
ዝሆን እንኳ ቢገረፍ አቋሙን ሊቀይር የሚችልበትን ግርፊያ በስተርጅና ተገርፈው በዓላማቸው ፀንተዋል።
ገራፊያቸው የአንድ ቀኑን ትዝታ እንዲህ ይተርከው ይዟል:- "ከዕለታት አንድ ቀን ቁርአን የአላህ ቃል አይደለም እንዲሉ ተገደው ራሳቸውን በተደጋጋሚ ስተው እስኪወድቁ ድረስ ብዙ እንግልትና ግርፋት ደረስባቸው ጀርባቸው ቀልቶ ሰንበር አውጥቶ ተዝለፍልፈው ሲወድቁ ስመለከት አዝኜ አንድ ኩባያ ውሀ አቀበልኳቸው ቀና ብለው በትኩረት ተመለከቱኝና ዛሬ ፆመኛ ነኝ በማለት መለሱልኝ። አያቹህ የናታቸዉ አስተዳደግ ጠንካራ ኢማን እንዲኖራቸዉ እንዴት እንዳረገ....

ወደ አማኔ ታሪክ ስንመለስ
"እናቴ ለኔ እናት ብቻ አልነበረችም ሁሉ ነገሬ ነበረች ሲያመኝ ከኔ በላይ ታማ ሲጨንቀኝ ተጨንቃ ፤ሳትበላ አብልታ....ነዉ ያሳደገችኝ ዉለታዋን በምን ይሆን የምክሳት ሁሌም አስባለሁ
የናት ዉለታዋ

ቃላት ቢደረደር በብዙ ጋጋታ
መቸ ይገልፀዋል የናትን ዉለታ
የናትን ዉለታ እንዴት ችየ ላዉራዉ
የሁሉም ተምሳሌት መሆኖን አቃለሁ
ሀዘኖን አርቀህ ደስታዋን አብዛላት ብየ እየተማፀንኩ
ከዛ ከጭንቁ ቀን ከዉልደቷ ጀመርኩ
ስትወልድ ያለዉ ስቃይ እንዴት ይገለፃል
ከሀሊቁ በቀር ማንስ ያቅላታል
ያየችዉስ ስቃይ በምንስ ይተካል
ከወለደች በላይ ጭንቀቱ ይብሳል
ከመዉለዷ በፊት ካለዉም ይለያል
እሷ ሳትበላ ልጇን ታበላለች
አልበላም ሲላትም በጣም ታስባለች
ለምን ይሆን ብላ ከባዱን ታዝናለች
ከታመመ ደግሞ እንቅልፏን ታጣለች
በሀሳብ ተጠምዳ ብትሰለሰላለች
እስከሚያድጉ ድረስ በጭንቀት ታያለች

እሰይ አደጉልኝ ነፍስም አወቁልኝ
ስራ ስለያዙ ሀሳቤን አረፍኩኝ
ብላ ሳትጨርስ ምነዉ አመሸብኝ
ምን ነክቶብኝ ይሆን ልጀ የቀረብኝ..
.
.
ከመዉለዷ በፊት የጀመረ ስቃይ
ማብቂያዉ ቢሆን እንጂ እዱንያን ስትለይ
ሌላም ማብቂያ የለዉ
አላህ ያሳምረዉ
ደርቦ ደራርቦ ጀዘዋን ይክፈለዉ!
..... ሰሚራ ሽኩር

....አንድ ቀን ጆርጂ የሚሰጠኝን ገንዘብ ለእማየ ሰጠኋት እማም ከየት አመጣኋዉ ስትል አፋጠጠችብኝ እኔም ሁሉንም ነገርኳት እማየ በኔ ትደሰትብኛለች ብየ አይን አይኖን ሳይ የእማየ አይኖች በእንባ ሞልተዋል ደነገጥኩ እማ ምነዉ እኔ ልጂሽኮ በሀላል እንጂ በሀራም አይደለም ገንዘቡን ያመጣሁት አልኳት እማም እንባዎች እየወረዱ "አቃለሁ የኔ ልጂ ሳሳድግህም ሀላልን እንጂ ሀራምን እንዳትነካ አድርጌ ነዉ" አለችኝ እሽ እማ ምን ያስለቅስሻል ስላት "እኔ የሚያስለቅሰኝ ሁለት ልጆቸን ማሳደግ አለመቻሌ ነዉ አንተን በዚህ በጨቅላ እድሜህ ከሀቅምህ በላይ ስራ ለመስራት ተገደድክ"

......እንባየን መቆጣጠር አልቻልኩም ተይይዘን አለቀስን እማ ለትንሽ ቀን ነዉ ይሄ ሁሉ ስቃይ ያልፋል ብየ ወደ ጆርጂ አመራሁ ጆርጂን ስራ ቦታ አጠሁት ወዴት ሂዶ ይሆን ብየ ስፈልገዉ አማኔ ብሎ አንገቴን ከኋላየ አቀፈኝ በጣም ተግባብተናል የእማየን ሁኔታም አስረድቸዋለሁ

አንድ ቀን ጆርጂ እናትህን አስተዋዉቀኝ ብሎኝ እማየን ላሳየዉ ይዤዉ ወደ ቤታችን አቀናሁ.....

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science