Get Mystery Box with random crypto!

መራራ እዉነት ክፍል ....... ሰሚራ ሽኩር .......ለማወቅ በጓጓ አንደበት የዚህን አ | ISLAMIC SCHOOL

መራራ እዉነት
ክፍል
....... ሰሚራ ሽኩር

.......ለማወቅ በጓጓ አንደበት የዚህን አላልህም እዚህማ አብረንህ ነበርን እኔ ያልኩኝ እዚህ ሳትመጣ በፊት ቤተሰቦችህ የትና እንዴት ናቸዉ? አንተስ ምን ሁኔታ ላይ ነበርክ?ስል ጠየቁት አማኔም አይኑን ወደ መሬት ወርዉሮ ባዘነ ፊት"ምን ያደርግልሻል የኔ ታሪክ
..... እኔኮ የሚነገር ታሪክ የለኝም በቃ ታሪክ የለኝም! ብሎ ማልቀስ ጀመረ
አባቢ "አንች ልጂ ምን መሆንሽ ነዉ ለምን የሚያስጨንቀዉን ማስታወስ የማይፈልገዉን የትናንት ሂወቱን ትጠይቂዋለሽ ትናንትኮ ታሪክ ሁኖ አልፏል በቃ ሙቷል ላይመለስ አምልጧል ትናንት ጥሩም ሆነ መጥፎ ላይደገም ለዛሬና ለነገ ሂወታችን ትምህርት ሁኖን አልፏል።
የትናንት ሂወቱን እያስታወሰ ባለፈ ነገር የሚያለቅስ ሞኝ ነዉ ትናንት የሆነዉ ሁሉ መሆን ስላለበት ነዉ የምሆነዉም መሆን ያለበት ነዉ! አላህ ከመወለዳችን በፊት ሁሉንም ፅፎታል የተፃፈዉም ተግባራዊ ይሆናል ከኛ የሚጠበቀዉ ሰበብ ማድረስ ብቻ ነዉ።
.... ግን ሀናኔ እንዲህ የሚያስጨንቀዉን ጥያቄ ስጠይቂዉ ሁለተኛ እንዳልሰማሽ ሁለተኛ!" ብሎ ተቆጣኝ እህ አባቢ ምን አጠፋሁ እያልኩ ወደ ክላሴ ገባሁ እማኔና ሪሀና ተከትለዉኝ መጡና አማኔ ይቅርታ አለኝ እኔም ይቅርታ ማለት ያለብኝ እኔ ነኝ ይቅርታ አልኩት "አይ እኔ ነኝ ይቅርታ መጠየቅ ያለብኝ አስቆጣሁሽ አይለል በአላህ ይቅርታ አለኝ እኔም ጣጣ የለዉም ይቅርታ አድርጌልሀለሁ አንተም ይቅርታ አድርግልኝ አልኩት አደረገልኝ ግን ዉዶቸ ተበድላቹህ ይቅርታ አድርጋቹህ ታዉቃላቹህ? ወይም እናንተ ሌላዉን በድሏቹህ ይቅርታ ጠይቃቹህ ታዉቃላቹህ?
ሁሌም አዉቀንም ሆነ ሳናቅ የምንናገረዉ ፤የምንሰረዉ ስራ የማንን ልብ እንደሚሰብር ማንን እንደሚያስቀይም አናቅም ይቅርታ እናድርግ ጣአሙን አድርገን እንጂ አናቀዉም
በአንድ ሰዉ ተበድላቹህ ወይም ተከድታቹህ ይቅርታ ማድረግ እንኳን ማሰብም ሊከብድ ይችላል ነገር ግን
ቂም፤ምሬት፤ህመም...... በዉስጣችን ስንይዝ ራሳችንን እንጎዳለን። ስለዚህ ለሁሉም ነገር ይቅርታ አድርገን መርሳት ጥሩ መፍትሄ ነዉ።


ዉዶቸ ዓለም በአዎንታዊና አሉታዊ ነገሮች የተሞላች ናት፡፡ ከአንድ መልካም ነገር ጎን ሌላ መጥፎ ነገር አለ፡፡ በአንድ መጥፎ ነገር ውስጥም ሌላ መልካም ነገር ይገኛል፡፡ ከዚህም የተነሣ በሌሎች ሰዎች መገፋታችን ወይም እኛ ሰዎችን መግፋታችን አይቀርም፡፡ ይህ አውቀነውም ሆነ ሳናውቀው በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ መከሰቱ የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ሕይወታችን ከሌሎች ጋር የተቋጠረና የተነካካ ነው፡፡ እኛነታችን ሌሎችን ይፈልጋል፡፡ እኛም ለሌሎች እናስፈልጋለን ፡፡ ሁሉም ሰው ከሌሎች የሚቀበለው ነገር አለው፡፡ ለሌሎች ሰጪም ነው፡፡

መሳሳት የሰው ልጅ ባህሪ ነው፡፡ ዳሩ ግን መሳሳት የጥንካሬ እንጂ የድክመት ምልክት አይደለም፡፡ ስህተት የእንቅስቃሴና የሕይወት ምልክት ነው፡፡ ሰለዚህም መሳሳት በየትኛውም የሕይወት ገጽ ላይ ሊከሰት የሚችለው ፡፡ በአንድ ዓይነት ሁኔታ ላይ በተደጋጋሚ መንገድ መሳሳትና ማጥፋት አስቀያሚ ድክመት ነው፡፡ ከተሳሳትን ይቅርታ እንጠይቅ ፡፡ ከተገፋንም በይቅርታ እንለፍ፡፡ ይህ የአእምሮ ብስለትና የመንፈስ ጥንካሬ ማሳያ ነው፡፡

ይቅርታ ማድረግ ጥሩ ነው ጨርሶ መርሳት ደግሞ እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡



ሰዎች በቀልን ትተው ይቅርታ ማድረግን የማይመርጡበት ምክንያት ዋጋው ስለሚወደድባቸውና የነርሱ ትንሽነትም ስለማይመጥነው ነው፡፡

አማኔ ጋር ይቅርታ ተበብለን አማኔ "ይቅርታሽ ከዉስጥ አይመስለኝም" አለኝ
ሪሀና "አወ ከዉስጧ አይደለም ታሪክህን ለማወቅ ሁላችንም ጓጉተን ነበር"

.....አማኔም "እሽ የኔ ታሪኩ ቢመራቹህም ለወደፊት ሂወታቹህ ትምህርት ይሆናቹሀልና ማወቁ ደስ ካሰኛቹህ ታሪኬን እናግራቹሀለሁ " ብሎ ታሪኩን እንዲህ መናገር ጀመረ

.....አባቴን አላቀዉም እናቴ ታናሽ ወንድሜን እርጉዝ እንደሆነች ነዉ የሞተ።
እናቴ ናት ብቸዋን ጪኗ እስከሚደማ ድረስ ጥጥ እየፈተለች እስከ አስር አመቴ ድረስ ያሳደገችኝ አንድ ታናሽ ወንድም አለኝ ሌላ እህትም ሆነ ወንድም የለኝም
በትምህርቴ በጣም ጎበዝ ስለነበርኩ እናቴን ለማገዝ ትምህርቴን ላቋርጠዉ ብላት እናቴ አይቻልም እኔ የምለፋዉ አንተን ጥሩ ደረጃ ለማድረስ ነዉ ደሞ ኢንሻአላህ ነገ ዶ.ር ሁነህልኝ ባንተ ያልፋልኛል።
....የኔ ልጂ የዛሬን ችግር አትይ ነገ ያልፋል ብቻ አንተ ጠንክረህ ተማርልኝ ትለኝ ነበር እኔ ግን የሷን ልፋት እያየሁ ተቀምጨ መማር ከበደኝ አንድ ቀን ለምን ከጠዋት እየተማርኩ ከሰአት የተለያዩ የጉልበት ስራዎችን እየሰራሁ እናቴን አላሳርፋትም ብየ አሰብኩ ለናቴ ብነግራት አትፈቅድልኝም ሳልናገር ወደ አንድ እየተሰራ ወዳለ ፎቅ ተሸካሚ እንኳን ቢቀጥሩኝ ብየ አመራሁ

ኢንሻአላህ ይቀጥላል

Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science