Get Mystery Box with random crypto!

መራራ እዉነት ክፍል ....... ሰሚራ ሽኩር አባቢ ጓደኛዉ የሰጠዉን ግማሹን ገንዘብ | ISLAMIC SCHOOL

መራራ እዉነት

ክፍል

....... ሰሚራ ሽኩር

አባቢ ጓደኛዉ የሰጠዉን ግማሹን ገንዘብ ይዞ የአማኔን መድሀኒት ለመግዛት በዛዉም አማኔን ቸክ ሊያስደርግ ወደ አዲስ አበባ ይዞት ሄደ

እኛም አላህ በሰላም ይመልሳቹህ እያልን ሸኘናቸዉ ግን ህክምናዉ ቀላል አልነበረም ወደ ስድስት ወር ሀኪም ቤት ክትትል ያስፈልገዉ ነበር ስድስት ወር ቆዩ እኛም ስድስት ወር ሙሉ በዱአ ጠንክረን፤ በናፍቆት አልቀን....... ጠበቅናቸዉ ረዥም ጊዜ ያአላህ! በስድስት ወር ዉስጥ ስንቱን ስቃይ አየንበት እኔ ትምህርቴን ለማቆረጥ ተገድጀ ነበር እማየ ግን አይቻልም አታቋርጭም ብላ እሷ በየሰዉ ቤቱ እንጀራ ጋጋሪነት ተቀጥራ የኔን የትምህርት ቤት ክፍያ መክፈል ጀመረች አባቢ አያቅም ሚስጥር ነዉ በዛ ላይ ጤፍ፤በርበሬ.....አልቆ ደረቅ ቂጣ እየበላን ኧረረረረ ያችን ስድስት ወር ማስታወስ አልፈልግም!

አማኔን አባቢ በስድስተኛ ወሩ ይዦት ሲመጣ አማኔ መሆኑን እስከምንጠራጠር ድረስ ዘንጦ ኢትዮጵያዊ መሆኑ እስከሚያጠራጥረን ድረስ ቀይ ዉብ ፤ ሲያዩት የሚያስደነግጥ ሁኖ በደንብ እያወራ ነበር የመጣ ።




.......ማመን አቃተን ሁላችንም ወደ አማኔ ተጠግተን አማኔ እኔን አስታወስከኝ ሀናን እህትህ ሀናን ነኝ መፀሀፍ ሳነብልህ የነበርኩት ሀናን አስታወስከኝ ስል ሪሀና ደግሞ አማኔ እኔ ሪሀና እህትህ የዛኔ ስተዉን ስትስቅብኝ የነበርኩት እህትህ ሪሀና አለች እማየም አማኔ እኔን መቸም አትረሳኝም እናትህ ስመክርና ስንከባከብህ የነበርኩት አለችዉ.........


አማንም እየሳቀና እያለቀሰ እንዴት እረሳቹሀለሁ ለኔ ብላቹህ መኪናቹህን ሸጣቹህ፤ለኔ ብላቹህ ከሞቀዉን ቤታቹህ ወጣቹህ፤ለኔ ብላቹህ የምትወዱትን ነገር አሳልፋቹህ ሰጣቹህ፤ለኔ ብላቹህ ተሰደባቹህ ለኔ ብላቹህ ያልሆናቹህትን ሆናቹህ .... ሁሉንም አባቢ ነግሮኛል እኔም አስታዉሳለሁ ብሎ ሰብስቦ አቀፈን እኛም እያለቀስን በደስታ ቀወጥነዉ

.....ወድያዉ ጓረቢቶቻችን ተሰብስበሙ የምን ጩኸት ነዉ ብለዉ መጡ እማየም "ልጆች ከደስታ ብዛት እየጫሁ ነዉ ለአላህ ምን ይዋልለታል ልጀ ዳና አማኔ ተሻለዉ ኑ ግቡ አዩት" ብላ ይዛቸዉ ገባች አማኔም ሰላም ካላቸዉ ቡሀላ አንተ አማን ነህ ሲሉ ጠየቁት ያዩቱን ማመን ከብዷቸዉ አማንም በነዛ ደስ በሚሉ ጥርሶቹ ፈገግ እያለ አወ አማን ነኝ ምነዉ ተቀየርኩባቹህ እንዴ አለ እነሱም አይ ......የሚሉት ጠፋባቸዉ ያኔ እብድ ሲሉ አእምሮን የሚነካ ነገር ሲናገሩ እንዳልነበረ ዛሬ ሁሉም አለፈ አልሀምዱሊላህ ምስጋና ለአለማቱ ጌታ የተገባ ይሁን! እያልኩ የአላህ ስራ እየገረመኝ አማኔን በትኩረት መመልከት ጀመርኩ በሀሳቤ እናቱ 4 አመት እሱን ፍለጋ ስትሰቃን ታየችኝ አባቱ በሱ ናፍቆት ሲንገበገብ ሳልኩት እህት ወንድሞቹ ተስፋቸዉ ተሞጦ ሙቷል ሲሉ ሳልኳቸዉ የአላህ ቤተሰባቹ እንዴት ሁነዉ ይሆን ስል አሰብኩ ለስድስት ወር አባቢና አማኔ ከቤት ቢጠፉ የሀዘን ቤት ነበር የመሰለ በዛ ላይ ናፍቆቱ ለአመታት ከቤተሰብ ርቆ እያልኩ ሳስብ አማኔ



..... ፈገግ ብሎ "ሀናኔ ምን ፊቴጋ የሚታይ ነገር አለ አፈጠጥሽብኝ" አለና ሁለት እጆቹን ፊቱጋ አድርጎ ፊቱን ሸፈነዉ
....ሀሀሀ ናፍቀኸኝ ስለነበር ነዉ አታፍጥጭ ካልከኝ እሽ አላፈጥም ብየ ፊቴን አዞሮ ጠቀመጥኩ አማኔ
"እንዴ ሀናኔ እየቀለድኩ ነዉ ይሄዉ እንደፈለግሽ እይኝ" ብሎ ወደኔ ተጠጋ እኔ ግን አኩርፌሀለሁ አልኩት
..."እሽ ምን ላርግ"
አንድ ጥያቄ ጠይቄህ ከመለስክልኝ እዞራለሁ
"እሽ የፈለግሽዉን ጠይቂ የምችል ከሆነ እመልሳለሁ"
እርግጠኛ ነህ ስል ደጋግሜ ጠየኩት እሱም አወ አለኝ ልጠይቀዉ ያሰብኩ ስለቤተሰቡ ሁኔታ የት እንዳሉ ነበር ግን ፈራሁ በቃ ጥያቄዉን ለሌላ ጊዜ እጠይቀሀለሁ ለዛሬ ይለፍህ ስል አባቢ እየሰማ ነበር "ኧረ አንች ልጂ ከምንገድኮ ነዉ የመጣን እሱንም በወሬ አታድክሚዉ ይረፍ ምግብም አልበላንም አቅርቢልን" ብሎን ምግብ ላቀርብ ተነሳሁ


......ብከፋፍት የሚበላ ነገር የለም ለካ እማየ አባየ የሰጣትን ብር ጨርሰዋለች ጤፍ መግዣ አጣ አልገዛችም ለዛ ነበር ደረቅ ቂጣ ለሳምንት ስትሰጠን የነበረ የአላህ መቸ ይሆን ይሄ ችግር የሚያበቃ ስል አማየ ሁለት እንጀራ ከሱቅ በዱቤ ይዛ መጣችና ትንሽየ ወጥ ነበረ አቀረበችላቸዉ አባየ ነይ አብረሽን ብይ አላት


እማየም በቅርብ እንደበላች ነገረቻቸዉ እኔም ቢርበኝም አሁን በላሁ አልኩኝ ሪሀና "አባቢ አዉቀዉ ነዉ ትናንት ምሳ የደረቀ ቂጣ እንደበሉ ናቸዉ ጤፉ ካለቀ ቆይቶል እማየም መግዣ አጣ አልገዛችም ለብዙ ቀን ቂጣ ነዉ እየመረረን የበላን"አለች አይ ህፃን መሆን ሁሉ ነገራቸዉ ግልፅ ነዉ

.....አባቢም "ለምን አልነገርሽኝም"አለ
እማየም ብር ይቸግርሀል ብየ ምናልባት ብናግርህና ብሩን ብትልክልኝ አንተም ሆንክ አማኔ በብር እጥረት የምትጉላሉ መሰለኝ ከዛ የቀረችዉን ዱቄት በርበሬዉ ዘይቱም ሲያልቅ እየጋገርኩ በደረቁ መመገብ ጀመርን ለመሆኑ ብር ተረፈህ እንዴ ስትል ጠየቀችዉ
አባቢም እዝን ብሎ "እንኳን ብር ሊተርፈን ለትራንስፖርት እንኳን አጠን ዳክተሮቹ ናቸዉ የሰጡን" አለ አየህ እኔም እንደማይበቃቹህ ገምቸ ነዉ ብር ላክልኝ ያላልኩህ አለች።

አባቢም "ዉዴ የኔ ባትሆኑ ይቆጨኝ ነበር ይሄ አስተሳሰብሽኮ ነዉ እንድወድሽ ሁሌም እንድናፍቅሽ የሚያደርገኝ" ......አልጨረሰም አማን "ዉይ ፍቅራቹህ ያስቀናል በሉ እኛንም የሚያካትት ወሬ አምጡ" አለ እኔ ከመሀል አማን ግን የድሮዉን ሁሉንም ነገር ታስታዉሳለህ ስል ጠየቁት
አማኔም አወ እዚህ ምን እንዳደረኩ አባቢ ነግሮኛል እኔም አስታዉሳለሁ ልንገርሽ አለኝ ለማወቅ በጓጓ አንደበት የዚህን አላልኩህም እዚህማ አብረንህ ነበርን እኔ ያልኩኝ እዚህ ሳትመጣ በፊት ቤተሰቦቹህ የትና እንዴት ናቸዉ? አንተስ ምን ሁኔታ ላይ ነበርክ? ስል ጠየኩት አማኔም......

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል


Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science