Get Mystery Box with random crypto!

መራራ እዉነት ክፍል ......ሰሚራ ሽኩር ጓደኛዉ ጊዜ ሳያባክን መጣና ተፈራርመዉ ቤቱን | ISLAMIC SCHOOL

መራራ እዉነት
ክፍል

......ሰሚራ ሽኩር

ጓደኛዉ ጊዜ ሳያባክን መጣና ተፈራርመዉ ቤቱን ገዛዉ እኛም እቃችንን ጠቅልለን የኪራይ ቤት ማፈላለግ ጀመርን ከሸጥነዉ ቤት ራቅ ብሎ ሶስት ክፍያ ያለዉ ቤት በጥሩ ዋጋ ተከራየን የሰዉ ወሬ ግን አላስቀምጥ አለን ሁሌም"እንደዉ ይች ሞኝ ባሏ ከየትም ያመጣዉን ልጁን ለማሳከም ቤቱን ሲሸጥ ዝም ትላለች አይ"እያሉ እማየን ማስቀየም ጀመሩ እማየም ሰምታ ባልሰማ ታሳልፋቸዋለች

.....እማየንና አባቢን ለማጣላት ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም እማየና አባቢ ግን የሰዉ ወሬ ስለማይሰዉ በጣም ይተማመኑና ይዋደዱ ስለነበረ እነሱ ምንም ቢያወሩ አልሰማ አሏቸዉ እንደዉም እነሱ ለማጣላት በሚያደርጉት ሩጫ የአባቢና የእማየ ፍቅር ቀን ከቀን እየጨመረ ነበር የመጣ።


.......የአባቢ ጓደኛ ግማሽ ክፍያ ሰጠዉና ግማሹን አሁን የለኝም በሌላ ጊዜ ብሎ ገገመ አባቢ ሰጠኝ ብሎ ቢለምነዉም ጓደኛዉ "ምን የሚገዛህ አጠህ በገዛሁህ ላይ" እያለ ያሾፋል።
... አባየም ለሱ ባልሸጥለት ነሮ ያረብ! ምን አጠፋሁ ምን በደልኩህ....እያለ አምርሮ አነባ!





እኔም አባቢን ለማፅናናት አባቢ ለሱ ባልሸጥለት ነሮ እያልክ አትፀፀት አላህ በተከበረዉ ቁዱስ ቁርአኑ ላይ እንዲህ ይላል ስል ሊያረጋጉት የሚችሉትን ተናገርኩ
" በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ በማንም ላይ አትደርስም ሳንፈጥራት በፊት በመፅሀፉ የተመዘገበች ብትሆን እንጅ ።" የሚከሰቱት ነገሮች ሁሉ ቀድመው ተፅፈዋል ። ብዕሩ ደርቋል ፤ ወረቀቶቹ ተነስተዋል ።

ﻗُﻞ ﻟَّﻦ ﻳُﺼِﻴﺒَﻨَﺎ ﺇِﻻَّ ﻣَﺎ ﻛَﺘَﺐَ اﻟﻠَّﻪُ ﻟَﻨَﺎ

«አላህ ለኛ የጻፈልን (ጥቅም) እንጂ ሌላ አይነካንም፡፡ » በላቸው፡፡
(አት-ተውባህ 51)

የደረሰብህ ነገር ሁሉ ሊዘልህ አይችልም ነበር ፤ የዘለለህ ነገር ሁሉም ሊደርስብህ አይችልም ነበር ። ይህ አስተሳሰብ በልብህ ውስጥ ጠልቆ መግባት አለበት ። ሁሉም መከራና ችግሮች ቀላል ይሆኑልህ ዘንድ ።

ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሠላም " አሏህ የሚወደውን ሰው /በችግር / ይፈትነዋል " ብለዋል ። አባቢ አንተንም በትንሹ የሞከረህ ስለወደደህ ይሆናል

በመሆኑም ቢያምህ ፣ ልጅህ ቢሞት ፣ ንብረትህ ቢወድም፤ጎደኛህ ቢከዳህ አምርረህ አትዘን ። አሏህ እነዚህን ነገሮች እንድከሰቱ አስቀድሞ አዟል ። ውሳኔውም የእርሱና የእርሱ ብቻ ነው ። በዚህ ካመንን ጥሩ ምንዳ እናገኛለን ። ኃጢዓታችንም ይሰረዝልናል ።

እናንተ ችግር የደረሰባችሁ ሰወች መልካም ዜና ይጠብቃችኋል ። ስለዚህ ትዕግስተኞችና በጌታችሁ ደስተኞች ሁኑ ።

ﻻَ ﻳُﺴْﺄَﻝُ ﻋَﻤَّﺎ ﻳَﻔْﻌَﻞُ ﻭَﻫُﻢْ ﻳُﺴْﺄَﻟُﻮﻥَ

ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ (ፍጥረቶቹ) ግን ይጠየቃሉ፡፡
(አል-አንቢያዕ 23)

አሏህ ነገሮችን ሁሉ ቀድሞ እንደወሰነ በፅኑ ካላመንክ ችግሮችን እንደቀላል ማሳለፍ አትችልም ። ባንተ ላይ የሚደርሰው ነገር ሁሉ የተፃፈበት ብዕር ደርቋል ። ስለዚህ በአንተ እጅ ባልሆነና መቀየር በማትችለው ነገር ላይ ለምን የፀፀት ስሜት ይሰማሀል ? ብርጭቆውን ከመሰበር ፣ አጥሩን ከመውደቅ ፣ ጎርፉን ከመፍሰስ ፣ ነፋሱን ከመንፈስ ማዳን እችል ነበር ብለህ ታስባለህ ?! ወደድክም ጠላህም እነዚህን ነገሮች ማስቀረት አትችልም ። ቀድሞ የተፃፈ ሁሉ ይፈፀማል ።
ﻓَﻤَﻦ ﺷَﺎءَ ﻓَﻠْﻴُﺆْﻣِﻦ ﻭَﻣَﻦ ﺷَﺎءَ ﻓَﻠْﻴَﻜْﻔُﺮْ

« የሻም ሰው ይመን፤ የሻም ሰው ይካድ» ፡፡
(አል-ከህፍ 29)

እጅህን ስጥ ፦ ስሜትህን በፀፀትና በቁጭት ከመጉዳቱ በፊት በቀደር እመን ። የምትችለውን ሁሉ ካደረግክ እና እንዳይደርስ የደከምክለት ነገር ከተከሰተ ያ ነገር የማይቀር እንደነበር እመን ። ይህን ባደርግ ኖሮ ይህ ይሆን ነበር አትበል ። ይልቁንም " ይህ የአሏህ ትዕዛዝ ነው ፤ እርሱ የሻውን ሰሪ ነው" በል ።

በእርግጥም ከችግር ጋር እፎይታ አለ ።
ﺇِﻥَّ ﻣَﻊَ اﻟْﻌُﺴْﺮِ ﻳُﺴْﺮًا

ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡
(አል-ሸርህ 6)

ከረሀብ በኋላ ጥጋብ ፣ ከጥማት በኋላ መጠጥ ፣ ከድካም በኋላ እንቅልፍ ፣ ከህመም በኋላ ጤና ፤ ከማጣት ቡኋላ ማግኘት ....አለ ። የጠፉት መንገዳቸውን ያገኛሉ ፤ የተቸገረው ችግሩ ያልፋል ፤ ጨለማው በብርሀን ይተካል ።

ﻓَﻌَﺴَﻰ اﻟﻠَّﻪُ ﺃَﻥ ﻳَﺄْﺗِﻲَ ﺑِﺎﻟْﻔَﺘْﺢِ ﺃَﻭْ ﺃَﻣْﺮٍ ﻣِّﻦْ ﻋِﻨﺪِﻩِ ﻓَﻴُﺼْﺒِﺤُﻮا ﻋَﻠَﻰٰ ﻣَﺎ ﺃَﺳَﺮُّﻭا ﻓِﻲ ﺃَﻧﻔُﺴِﻬِﻢْ ﻧَﺎﺩِﻣِﻴﻦَ

አላህም ድል መንሳትን ወይም ከእርሱ ዘንድ የኾነን ነገር (ማጋለጥን) ሊያመጣ በነፍሶቻቸው ውስጥ በደበቁትም ነገር ተጸጻቾች ሲሆኑ ተረጋገጠ፡፡
(አል-ማዒዳህ 52)

በርካታ ማይል የሚያካልለውን ሀሩር በረሃ ካየህ ከእሱ ቀጥሎ ሰፊ ጥላ ያለው ማራኪ አረንጓዴ መስክ መኖሩን ልብ በል ። እንባ በሳቅ ፣ ፍርሀት በመፅናናት ፣ መረበሽ በመረጋጋት ይተካል ። ነብዩሏህ ኢብራሂም አለይሂ ሠላም ሠወች እሳት ውስጥ ሲከቷቸው በአሏህ እርዳታ ሙቀቱ አልተሰማቸውም ነበር ።

ﻗُﻠْﻨَﺎ ﻳَﺎ ﻧَﺎﺭُ ﻛُﻮﻧِﻲ ﺑَﺮْﺩًا ﻭَﺳَﻼَﻣًﺎ ﻋَﻠَﻰٰ ﺇِﺑْﺮَاﻫِﻴﻢَ

«እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ፤ ሰላምም ሁኚ» አልን፡፡
(አል-ኢብራሂም 69)

ነብዩሏህ ሙሳ አለይሂ ሠላም በልበ ሙሉነት ፣ በጥንካሬና በፅኑ እምነት ፥
ﻗَﺎﻝَ ﻛَﻼَّ ۖ ﺇِﻥَّ ﻣَﻌِﻲَ ﺭَﺑِّﻲ ﺳَﻴَﻬْﺪِﻳﻦِ

(ሙሳ) «ተዉዉ! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፡፡ በእርግጥ ይመራኛል» አለ፡፡
(አል-ሹዐራዕ 62)

ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሠላም ከአቡበክር ሲድቅ ረድየሏሁ አንሁ ወአርዷህ ጋር ዋሻ ውስጥ ተደብቀው በነበሩበት ጊዜ ለአቡበክር አይዞህ አሏህ ከእኛ ጋር ነው አሏቸው ። ከዚያም ሰላምና ጥበቃ አገኙ ።

አንዳንድ ሰወች የሚታይባቸው ችግርና መከራ ብቻ ነው ። ይህ የሆነበት ምክንያት ከመኖሪያቸው በርና ግድግዳ ወዲህ ያለውን ነገር ብቻ ስለሚመለከቱ ነው ። ነገር ግን ከነዚያ መጋረጃዎች ባሻገር ያለውን ነገር መመልከት ያስፈልጋል ።

አትረበሽ!ነገሮች ባሉበት መቀጠል አይችሉም ። ቀናትና አመታች ይሽከረከራሉ ። መጭው አይታይም ። አንተ ልታውቅ ባትችልም በየቀኑ አሏህ ያዘዛቸው አዳድስ ነገሮች ይከሰታሉ ። በእርግጥም ከችግር ጋር ምቾት አለ!


አባቢ ጓደኛዉ የሰጠዉን ግማሹን ገንዘብ ይዞ የአማኔን መድሀኒት ለመግዛት በዛዉም አማኔን ቸክ ሊያስደርግ ወደ አዲስ አበባ ይዞት ሄደ

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science