Get Mystery Box with random crypto!

መራራ እዉነት ክፍል ....... ሰሚራ ሽኩር .....'አይዞህ እኛ ሁሌም ከጎንህ ነን | ISLAMIC SCHOOL

መራራ እዉነት
ክፍል

....... ሰሚራ ሽኩር

....."አይዞህ እኛ ሁሌም ከጎንህ ነን ይሄን ወርቅ ሽጥና የአማኔን መድሀኒት ግዛ"አለችዉ አባቢ ግን አይቻልም አለ

....እማየም እኔም አባቢ ወርቁ መሸጥ አለበት የግድ የአማን መድሀኒት በዚህ ሳምንት ዉስጥ መገዛት አለበት አልን አባቢ "እና ለመሸጥ ወሰናቹህ" አለን እኛም አወ መከፈል ያለበትን ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ ነን አልነዉ አባቢ በፍቅር አይኑ እየተመለከተኝ "ሀናኔ አንች እንኳን በጣም የምትወጂዉን በጣም የምትሳሽለትን ወርቅ ልትሸጪ ተስማማሽ" አለኝ እኔም አብሽር አባቢ አላህ አንድን ነገር አይወስድም ከዛ የተሻለ ሊሰጠን ቢሆን እንጂ አልኩ
.....አባቢም ቡዙ ካቅማማ ቡኋላ አማራጭ ስላልነበረዉ እሽ ብሎ ሊሸጠዉ ሄደ እማየ ከመሄዱ በፊት "ተጠንቅቀህ ሌቦች በዝተዋል እንዳይሰርቁህ" ብላ በተደጋጋሚ ነገረዋለች እባቢም ችግር የለዉም ብሏት ወርቁን ሊሸጠዉ ሄደ እኛም ስንት ይሸጥ ይሆን እያል አባቢን በጉጉት ስንጠብቀዉ ቀረብን ለብዙ ሰአት ጠበቅነዉ አልመጣም ስንደዉል ስልኩ ዝግ ነዉ ሰአቱ እየሮጠ ጊዜዉ እየመሸ ሄደ አባቢ አልመጣም እማየ ምን ሁኖ ይሆን እያለች መጨነቅ ጀመረች


....... እኔም በጣም ተጨነኩ ከመሀል በሩ ተንኳኳ እየሮጥኩ ስከፍተዉ አባቢ ነዉ አልሀምዱሊላህ ደህና መጣህ ደሞ እስካሁን የቆየህ ታክሲ አጠህ ነዉ አልኩት አባቢ ዝም ብሎ እቤት ገባ።

.... እንባ እያነቀዉ አዉፍ በሉኝ ሌቦች ወርቁን ከእጀ መንትፈዉኝ ሮጡ ተከተልኩ ተከተልኩ.... መጨረሻ ላይ ስሮጥ ቆይቸ እነሱም ጠፉኝ እኔም ፖሊስ ጣቢያ ሂጀ ሁኔታዉን ነግሬቸዉ መጣሁ እያለ ማልቀስ ጀመረ
......እማየ ሀዘንናፍቅር ከፊቷ እየተነበበ "ዉዴ!አይዞህ ለኸይር ነዉ ሌባች ይያዛሉ ወርቁም ይገኛል" ስትል አበረታታችዉ አባቢም እንዳልሽዉ ያድርግልኝ አለ እኔም ኧረ አባቢ ለዚህ ደግሞ ታዝናለህ እንዴ ይሄኮ ተራ ነገር ነዉ ሰዉ እንኳን ቁስ ነገር ሂወቱን ያጣ የለ አብሽር አልኩ ዉስጤ ግን እዉነት ለመናገር ከፍቶኛል ያአላህ ካልተገኘስ መድሀኒቱ የኛ የትምህርት ቤት ክፍያ በምን ገንዘብ ሊከፈል ነዉ ስል አሰብኩ ማሰቡ ሲደክመኝ በቃ ለኸይሩ ነዉ አልኩ።

......ነግቶ አባቢ ሌቦቹ ተይዘዉ እንደሆነ እስኪ አዲስ ነገር ካለ ብሎ ወደ ፓሊስ ጣቢያ አቀና እኔም ወደ ትምህርት ቤት ሊሄድ ስዘጋጂ የትምህርት ቤት ጓደኞቸ ተሰብስበዉ ሊጠይቁን መጡ ደነገጥኩ ችግሬን እንኳን ለአላህ እንጂ ለሰዉ ተናግሬ አላቅም ምክንያቱም ችግር ፈቺ አላህ እንጂ ሰዉ አይደለም።
.... ማታ ከመተኛቴ በፊት ያረብ ቢያንስ ለአማኔ መድሀኒት መግዣ የሚሆን ገንዘብ እናግኝ አባቢም ወርቁን አግኝቶ ከጭንቀቱ ይገላገል ስል ነበር .......... ብቻ አላህ ዱአየን ተቀብሎኝ የተወሰነ ብር አዋጠዉ ብርና ፍራፍሬ ይዘዉ መጠዉ አማኔን አይተዉት ሄዱ እንዴት መታመሙን አወቁ ስል ሪሀናን ጠየቋት ሪሀናም እኔ እስር ቤት እንደገበሁ ሲደዉሉ ወንድሟን አሞባት ብያቸዉ ነበረ።
.... ዛሬ ለመጠየቅ መጡ አለች
.... ይዘዉት የመጡት ብር ለመድሀኒት መግዣ ባይበቃም ለመጨመሪያ ይሆናል አልሀምዱሊላህ እያልን ከእማየ ጋር ስንመካከር አባቢ ምንም አዲስ ነገር የለም ብሎ በአዘነ አንደበቱ ነገረን በቃ ቤቱ መሸጥ እንዳለበት ተስማማንና ይሸጣል የሚል ፁህፍ የግቢዉ በር ላይ ለጠፍንበት ለአንድ ለሁለት ቀን ጠያቂ የለም በሶስተኛዉ ቀን አንዱ አኔ እገዘዋለሁ ብሎ መጣ እኛም ሊሸጥ ነዉ በሚል በደስታና በሀዘን ስንጠብቅ በዋጋ አልስማማ ብለዉ ቀረ የአማኔ መድሀኒት በሳምንት ዉስጥ መገዛት አለበት ሳምንት ሊሆን ሶስት ቀን ብቻ ነዉ የቀረን በፍጥነት መገዛት አለበት እያለ አባቢ የሚገዛ ቢጠባበቅ የሚገዛ ጠፋ በአራተኛዉ ቀን ያ ..ይወደዉ የነበረዉ የአባቢ ጓደኛ በርካሽ ዋጋ ልግዛህ አለዉ አባቢም አይቻልም በዚህ ዋጋ አልሸጥም አለ

ብድሩን የለኝም አልከፍልህም ሲል እንዳልነበር አሁን ቤት ሊገዛ ብቅ ማለቱ ገረመኝ እማየም አባቢም ሁላችንም እጃችንን ወደ ላይ ዘርግተን ያረብ ማለት ጀመርን የአማኔ መድሀኒት ለመግዛት ሁለት ቀን ብቻ ቀረን በዚህ ቀን ካልተገዛ ወደ ጤናዉ በፍጥነት እንደማይመለስ ዶክተሩ ተናግሯል ምን እናርግ ወደ አላህ ፊታችንን አዞርን በርግጥም የኛ ጌታ ዱአን ይሰማል ለምኑኝ እስጣለሁ አይደል ያለ በቃ ነገ የሚገዛ ይመጣል ስንል እርስ በርሳችን ተነጋገርን ነገር ግን በነጋታዉ ገዢ ብንጠብቅ ብንጠብቅ የለም አባቢ ተስፋ ሲቆርጥ ለጎደኛዉ ና ባልከዉ ዋጋ ግዘዉ ብሎ በኔ ስልክ ደወለለት የሱንማ ከወርቁ ጋር አብረዉ ወስደዉበታል


ጓደኛዉም ጊዜ ሳያባክን መጣና ተፈራርወዉ ቤቱን ገዛዉ እኛም እቃችንን ጠቀላለን የክራይ ቤት ማፈላለግ ጀመርን


በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

Join
t.me/Islam_and_Science
t.me/Islam_and_Science