Get Mystery Box with random crypto!

ISLAMIC SCHOOL

የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL
የሰርጥ አድራሻ: @islam_and_science
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 15.55K
የሰርጥ መግለጫ

✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 19

2022-02-04 18:00:55
አል-አኒስ የኦን ላይን ት/ት ቤት`_

በዩቲዬብ ቻናሉ የተጅዊድ ትምህርቶችን ሲያቋድሰን እና በኦን ላይን ት/ት ቁርአንን በማስቀራት የሚታወቀው ናሲህ ሚዲያ መጭው ረመዷንን አስመልክቶ አዲስ ነገር እንካችሁ እያለ ይገኛል። ይሄውም
ሙስሊሙን ማህበረሰብ በሚመቻቸው ሰአት እና ባሉበት ቦታ ሆነው ከቁርአን ጋር የሚተዋወቁበት እና የሚማሩበት *አል-አኒስ የኦን ላይን ት/ት* ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቆ በምዝገባ ላይ ይገኛል።
875 viewsedited  15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-04 11:43:48 አል-አኒስ የኦን ላይን ት/ት ቤት`_

በዩቲዬብ ቻናሉ የተጅዊድ ትምህርቶችን ሲያቋድሰን እና በኦን ላይን ት/ት ቁርአንን በማስቀራት የሚታወቀው ናሲህ ሚዲያ መጭው ረመዷንን አስመልክቶ አዲስ ነገር እንካችሁ እያለ ይገኛል። ይሄውም
ሙስሊሙን ማህበረሰብ በሚመቻቸው ሰአት እና ባሉበት ቦታ ሆነው ከቁርአን ጋር የሚተዋወቁበት እና የሚማሩበት *አል-አኒስ የኦን ላይን ት/ት* ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቆ በምዝገባ ላይ ይገኛል።

ከዚህ በፊት ያስቀራበት የነበረውን የአቀራር ስርአት በማዘመን መጭውን የተከበረ ወር ከ ቁርአን ጋር የምንከብርበት ይሁን ይለናል

ቂርአቱ የሚሰጠው በዙም አፕሊኬሽን በመሆኑ በኡስታዞች እና በተማሪወች መካከል ጥሩ በሆነ መስተጋብር የመማር ማስተማር ሂደቱ ይካሄዳል።
እንዲሁም በሌሎች አማራጮች:- ዋትሳፕ እና ኢሞ ቂርአቱ የሚካሄድ መሆኑ ለሁሉም ተደራሽ ይሆናል።
የሚሰጡ ትምህርቶች ለጀማሪ ተማሪወች ቃዒዳ
ቁርአን በነዞር
ቁርአን በተጅዊድ እና የተጅዊድ ኪታቦች
የተውሂድ እና የአቂዳ ደርሶች
የምዝገባ ጊዜ ውስን በመሆኑ ቀድመው ይመዝገቡ። 251 906443888
251 931800885
የዋትሳፕ ሊንክ......https://chat.whatsapp.com/L0udcLn0Zj4DyEc5qr5i1y
የቴሌግራም ሊንክ https://t.me/+3js98as5D2tmN2M0

ከላይ ባሉት ስልክ ቁጥሮች በቴሌግራም ዋትሳፕ እና ኢሞ መመዝገብ ይችላሉ።
_አል-አኒስ ይለያል!_
1.3K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-31 22:23:48
#Share እያደረጋቹ

#እባካቹ እህትና ወንድሞቼ ለአሏህ በሉና ሁላቹም ፕሮፋይላቹን በዚህ ምስል ቀይሩት።ለወንድሞቻችን ድምፅ እንሁን።
1.በየሚዲያው(ቴሌቭዥን እና ሬድዮ)
2.በየታዋቂ ሰዎች ፔጅ
3.በየግሩፖች
4.በየዩቱዩቦች
ድምፃችንን እናሰማ አሏህ ምንዳቹሁን ይክፈለው።

#share ባአላህ ይሁንባችሁ share #አደርጉት እኛ በነሱ #ቦታ ሆነን እናስብ እስኪ
402 views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-27 05:21:15 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ
ዉድና የተከበራችሁ የአኼራ እህት ወንድሞቼ እንዴት ናችሁ.....

አልሀምዱሊላህ!!
አልሀምዱሊላህ!!
አልሀምዱሊላህ!!

በህይወት ተርፈናል፡፡ መቼም የጠፋሁት ደሴም በወገኖቻችን ቀኝ ግዛት ተይዘን ነበር...አላህ በሰጠዉ ፈጣን እርዳታ አሁን የሰላም አየር እየተነፈስን ነዉ፡፡

☞ደሴ ከዛ ከጨለማ ህይወት ተገላግለን ኔት ወርክ እና መብራት ቢመጣም Data ግን ገና አልተለቀቀም፡፡
ዛሬ ከወራቶች ቆይታ ቡሀላ በአስተያየት መስጫ bot ስገባ ስለኔ ህይወት ተጨንቃችሁ አሚር አለህ ወይ? ዱአ እያረግን ነዉ መኖርህን አመላክተን ላላችሁ...

በMessage መብዛት ለየብቻችሁ ለመመለስ ጊዜ አላገኘሁም አዉፍ በሉኝ....ግን ሀቂቃ የእናተ ዱአ ተጨምሮ ይሆናል በህይወት የተረፍኩት እንጂ በጣም ከባድ ጊዜ አሳልፈናል ...አላህ ለወደፊት ከጦርነት ይጠብቀን

ዛሬ ከጁንታዉ ተርፈን ዘመድ ለመዘየር አዲስ አበባ ስለመጣሁ ነዉ፡፡ Data ደግሞ አዲስ አበባ ስለሚሰራ ይሄዉ በህይወት መኖሬን መልዕክት አስቀምጫለሁ...በቅርቡ ወደ ደሴ ተመላሽ ነኝ....ከሚዲያ እርቃለሁ

ግን ሰዉ በአማን ቀን ማንኛዉም ሰዉ ነዉ!!!
ግን ጦርነትን ወይም ክፉ ቀን ጠብቆ የሚከዳ በቁም ከሚገል ከክፉ ባልንጀራ አላህ ይጠብቃችሁ
መሞታችንን ሲጠባበቁ ግን በህይወት እንድኖር ዱአ ስታደርጉ ለነበራችሁ ወዳጆቼ ይድረስ

በህይወቴ በዚህ ጦርነት ሳልሞት የገደለኝ ሰዉ ግን ለወደፊት እንዴት መኖር እንዳለብኝ አስተምሮኛል...

Data ደሴ ሲለቀቅ ኢንሻ አላህ ወደ በፊቱ አስተሳሰቤ ከተመለስኩ እንገናኝ ይሆናል..በዚህ ጦርነት ብተርፍም ብዙ የልብ ቁስል እና የአስተሳሰብ ቢዥታ አስቀምጦ እንደሚሄድ አትዘንጉ...ያሳለፍነዉ ድሮን ከባድ መሳሪያ ድምፅ እና አለኝ በምለዉ ሰዉ ክህደት ስለነበር ድንጋጤዉ እና የልብ ስብራት መች ይለቃል ...

ግን ብቻ አልሀምዱሊላህ ደሴ ላይ ብዙም የሞተ የለም ከነቤተሰቦቼ ከነጓደኞቼ ደህና ነን


ያረህማን እዝነት ከተጨመረ እና ደሴ data ከሰራ ወደ ፊት በሰፊዉ እንገናኝ ይሆናል...
ዛሬ አለን ለማለት ነዉ ለኔ ስትጨነቁ ስታስቡ ዱአ ስታደርጉ የነበራችሁ ለወደፊትም ዱንያ ነዉ እና አይሞላም ግን ብዙ በደል ሳይደርስባችሁ ብዙ ክህደት ሳይደርስባችሁ ብዙ ችግር ሳይፈትናችሁ አላህ የምትኖሩ ያድርጋችሁ...አላህ ቀን መርጦ ከሚጥል ባልጀራ ወዳጅ ይጠብቃችሁ ....ያመናችሁት አይክዳችሁ ....ከልባችሁ አሚን በሉ.......

ኢንሻ አላህ ለወደፊት እንገናኝ ይሆናል.....
አሚር ሰይድ
ታህሳስ 17/04/2014
1.1K viewsedited  02:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-07 19:36:02 እንተዋወሰ ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ሌሎችን ያሰተውሰ። ኢንሻ አሏህ

አሏህ ሀገራችን ሰላም ያደርግልን አብሽሩ
6.1K views16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-25 14:19:49 አረቦች አልሰባህ ረባህ (ከንጋት ትርፍ አለዉ) ይላሉ

ከትናንትናዉ እልህ አስጨራሽ ጦርነት ዛሬ ትንሽ የደሴ ከተማ ህዝብ እፎይ ብሏል
ነብዩ ሰዐወ ጦርነትን በጭራሽ አትመኙ ብለዋል ሀቢቡና ሙሀመድ ሰዐወ ከ1400 አመት በፊት የነገሩንን ከሁሉም ያለዉ ወገን ቢሰማ ይሄ ሁሉ ጉድ ባልመጣብን

ዉድና የተከበራችሁ የቻናሌ ቤተሰቦች ጭንቀታችን አሳስቧችሁ የጠየቃችሁኝ ደሴ እንዴት ሆነ ?? ላላችሁ
አልሀምዱሊላህ ሰላም ነን ትናንት የህዝብ መንጋ ሁነዉ መጥተዉ ነበር ግን እስከ አሁን አልገቡም
በጀግኖቻችን መከላከያዉ የአማራ ልዩ ሀይል ፋኖዉ የደሴ ከተማ ወጣት ስንቅ ዉሀ በማቀበል በአንድ ላይ በመተባበር እየመከተ ይገኛል...ጥላትም አፈግፍጓል ግን ገና ይቀራል

የአይጥ እድሜዋ ስንት ነዉ?ተብሎ ቢጠየቅ እንደ ድመቱ ጥንካሬ ይወሰናል አለዉ ይባላል
እናም የወሎ ህዝብ ሆይ እንተባበር!!!
አንዳንድ አክቲቪስቶች እንደ Esat ጋዘጠኛ
ሲሳይ አጌና በወሎ ህዝብ የሚቀልዱ አይነት የተለያዩ ማህበረሰቦች የደሴ ህዝብ እየሸሸ ነዉ ብለዉ ወሬ ሲያናፍሱ እያየን ነዉ
☞በመጀመሪያ መከላከያ ሰራዊት ከመቀሌ ጀምሮ ስንት ከተማ እየሸሸ መጥቶ አይደል እንዴ ደሴ የደረሱት እናም ሴቶችና ህፃናትን ወደ አዲስ አበባ ማሸሹ ይደንቃል ወይ??
☞የደሴ ልጅ ስናድግ መሳሪያን የምናዉ ከፓሊስና ከወታደር እንጂ በእጃችን ይዘን ተኩሰን አላደግንም ጦርነትም ሰምተን አናቅም እና ይሄ ሁሉ ጦርነት ሲሆን ቢሸሽን የሚተችበት ሞራል አለ??ለምን በፊት ጀምረን አስታጥቁን ብንል የሚሰማን የለም ነበር እና በአማራ ክልል ወሎን ባለማስታጠቅ ዋጋ እያስከፈለን ባለ ጦርነት የደሴ ልጅ መወቀስ አይችልም
ሲጀመር የደሴ ከተማ ወጣት 100% የትም አልሄደም
☞የደሴ ልጅና የደሴ ነዋሪ ለይቷል የደሴ ነዋሪ የነበረ ንበረቱን ይዞ ደሴን ክዶ ወደ ተወለደበት ሀገር ሂዷል እስኪ መጀመሪያ ይረጋጋና የምናያቸዉ ይሆናል፡፡ ግን ወላሂ ብየ ልንገራችሁ የደሴ ተወላጆች የምናቃቸዉ ከአዲስ አበባ ከተለያየ ከተማ መጥተዋል..ከዉጭ ሀገር ከአሜሪካ ድረስ መጥተዉ ህዝቡ ጋር መከላከያዉ ጋር ከጎኑ ሁነዋል
☞ለምሳሌ እኔ ዘመዶቼን ሴቶችና ህፃናትን ወደ አዲስ አበባ ልከናል ለምን በዚህ ጦርነት የከባድ መሳሪያ የመድፍ የዲሽቃ ድምፅ በብዛት ስለሚሰማ ሴቶችና ህፃናት ይረበሻሉ ..ህፃናት ሴቶች ሲረበሹ ሲጨነቁ ከማየት ሴትና ህፃናትን ልከን ወንዱ ግን ጦር ግንባር ድረስ እየሄድን ነዉ

የሸገር ሰዉ ሆይ ባይሆን እናንተ መጥታችህ ወሎን ማገዛችህ ቢቀር የወሎ ሴትን ለዘር ጥሩ ነዉ ብላችሁ እንዳታስቀሩብን አደራ
☞ዛሬ በተደረገዉ ስብሰባ ማንኛዉም ነዋሪ በደሴ ዙሪያ ጫካ ቢገኝ ያዉ ወደ አኼራ ይሸኛል ለምን በጫካ እየሄዱ መረጃ የሚሰጡ ሰርጎ ገቦች እየተያዙ ስለሆነ
☞በከተማዉ ዉስጥ አልፎ አልፎ ተኩስ ይሰማል ይሄ ደግሞ ትናንት በኩታበር በተደረገዉ እልክ አስጨራሽ ጦርነት ዉስጥ ብዙ የተደመሰሱ ሲሆን ግን ሰርጎ ገቦች ደሴ ስለገቡ እነሱ እየተገኙ እርምጃ እየተወሰደባቸዉ መሆኑን እወቁ



ግን ብዙ ሰዉ በተለይ ከወሎ ዉጭ ያለ ነዋሪ ያልተረዳዉ ነገር አለ እንዴት አድርጌ እንደማስረዳ አላዉቅም ደሴ ከተያዘ ኢትዮጲያ መንግስት የመቀጠል ያለመቀጠል ጉዳይ ነዉ፡፡
ጦርነቱን እኛ ፈልገነዉ አልመጣም..መጡብን እንጂ ወላሂ የወሎ ህዝብ ከትግሬ ሳይቀር ተዋልደናል ነገር ግን ይሄዉ መጡብን ጥላቻም ሳይሆን ይሄ ራስን ቤተሰብን ከተማን የመከላከል ህልዉና ነዉ ፡፡

ከወል ዉጭ ያላችሁ ወላሂ ብየ ልንገራችሁ እነሱ የመጡት እንዴት አድርጌ ላስረዳችሁ አዲስ አበባ ሰልፍ ወይም ድጋፍ ሲኖር መስቀል አደባባይ የሚሰበሰበዉ ህዝብ አለ አይደል..እነሱም የመጡት መስቀል አደባባይ እንየሚሰበሰብ ህዝብ ሁነዉ እየዘረፉ እያሳደዱ ነዉ ታዳ ይሄን እንደ ህዝብ የመጣ ደሴ ላይ ካልተመከተ ነገ ከነገ ወዳ አዲስ አበባ እንደማይገቡ ምን ማረጋገጫ አለ


ለማንኛዉም የደሴ የኮምቦልቻ ወጣት ሆይ !!!!
ወደ ጦር ግንባር በመሄድ ዉሀ ስንቅ ማቀበል አንዘንጋ...ወላሂ የሚዋጉትን ወታደሮች በጣም ነዉ የሚያሳዝኑት ..ወራሪዉ ሀይል እየዘረፈ የተለያዩ እንስሶችን እየበሉ ሲዋጉ የኛ የወገን ጦር ግን በኮቾሮ ብስኩት እየበላ ነዉ የሚዋጋዉ....የጦር ግንባር ሂደን ስቃያቸዉን አይተን እንምጣ ፡፡ ዛሬ በተለያዩ ግንቦሮች ለመከላከያ ሰራዊት ዉሀና ምግብ እያቀበልን ነዉ...የሚዲያ ወሬና ተግባር ይለያያል የወሎ ህዝብ ሆይ የተግባር ሰዉ እንሁን!!
ሆዳችን ብዙ እሳት ተቀጣጥሏል ይሄን ጦርነት ካሸነፍን ቡሀላ በወሎ የተሰራዉን ቁማር አሻጥር በወሎየዎች በመተባበር ይፈታል ለታሪክ ይነገራል
እንተጋገዝ እናሸንፋለን

አረ ደሴ ደሴ ፣ ገራዶ ገራዶ
ገደል ገባ ጁንታ ፣ ተንዶ ተንዶ
ሞቱን አፋጠነ ፣ የደሴን መሬት ወዶ
ነደደ ወያኔ ፣ ወሎ እሳት ወልዶ

አሁን ደሴ ላይ ያለ ተፈናቃይ ብቻ ከአንድ ሚሊየን ይበልጣል እነሱ ወደ ደሴ መጡ እኛ ግን ሲመጡ ጥለን የምንሄድበት ከተማ የለንም

መቼም ቢሆን ደሴን ጥለን የምንሸሽበት የምንጠጋበት ከተማ የለንም አብሽሩ አላህ ከእዉነት ጋር ነዉ
ድል ለኢትዮጲያ ወሎ ደሴ ኮምቦልቻ
9.7K viewsedited  11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-24 08:00:18
ተተኮሳ ብየ ዲሽቃና መትረይስ
ወሬ ሰማሁ ብየ የጥላትን መድረስ
አንቺን ጥየ ብሄድ ፈርቼ ለነፍሴ
ይቅር አትበይኝ ተቀየሚኝ ደሴ


ሲጓጉ ነው እንጂ ፣ ምኞት ሲቋምጡ
በጀግናው ሰራዊት፣ በፋኖው በምርጡ
በወጣት ሚኒሻው፣ አፈር እየጋጡ
እንደምን አርገው ነው ደሴን የሚረግጡ
ሼን


የሚያስዝነዉ ግን የትግራይ ህዝብ ለወደፊት ዘራቸዉን የሚተኩበት ወንድ መጨረሳቸዉ ነዉ...ደሴ ለመግባት ቋምጠዉ የተረፈረፈ የትግራይ ልጆች ለመቅበር ለራሱ ብዙ ቀን ይፈጃል....ግን ትግሬ ሁኖ አይበጅም የሚል ጠፍቶ ይሆን ወይስ እነሱ አዲስ አበባ ዉጭ ሀገር በብር ሰክረዉ ደሀዉ የትግሬ ህዝብ ይለቅ ብለዉ ፈርደዉ ይሆን???
እንደ ዱሮዉ በቦሩ ሜዳ መጥተዉ ነበር ..ዛሬ ግን ቦሩ ሜዳ የወሎ መቀበሪያ ሳይሆን የጥላት መቀበሪያ ሁኖ ታሪክ ቀዷዉን አዉጥቷል፡፡


ለማንኛዉም ምንም ማድረግ አይቻልም ጦርነት ፊት ለፊት መጥቷል.....ደሴ ኮምቦልቻ ያለን ወጣቶች ሆይ ወደ ጦር ግንባር ደጀን እንሁን ለመከላከያ ለፋኖዉ ስንቅ እናቀብል፡፡
በተረፈ ደሴ ሰላም ነዉ ላላችሁ ...ለጊዜዉ ሰላም ነን ጠላት በሁሉም አቅጣጫ ከቦን እኛም ሳንደናገጥ ከተማችንን ሸሽተን ሳንሄድ የመድፉ የከባድ መሳሪያዉ ድምፅ ሳይበግረን እናት አለም ደሴን በቀን በለሊት እየጠበቅን ነዉ፡፡
ከእናንተ የምንፈልገዉ ወንድ የሆነ ብቻ ፆታዉ ወንድ የሆነ ሳይሆን ልቡ በወንድ የታተመ ወሎ መጥቶ እንዲረዳን ሴቶች ደግሞ ዱአ እንድታደርጉ ብቻ ነዉ

ወሎ የልጅ እያሱ ልጆች ሆይ አብሽሩ ቀን አለ!!!

አሁን የወሬ የቀልድ ጊዜ ወሎ ላይ የለም የመሞት ወይ የመሰንበት የሞት ሽረት ትግል ነዉ፡፡ ወሎ ደሴን ማዳን ኢትዮጲያን ማዳን ነዉ 100% እርግጥ ነዉ ደሴ ከተያዘ ሁሉም ኢትዮጲያዊ ማወቅ ያለበት ነገሮች ሁሉ እንደሚበላሹ ነዉ ...

ትኩረት ወሎ ደሴ ኮምቦልቻ
7.1K viewsedited  05:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ