2022-05-01 12:36:59
የ13 ዓመት ልጅ ከመደብር ዳቦ ሰረቀ ዘበኛው ይዞት ነበርና ሊያመልጥ ሲል የመደብሩ መደርደሪያ ወድቆ ተሰበረ።
ከዛ ልጁ ተይዞ እንደሌባ ተደብዶቦ ወደ ፍርድ ቤት ሄደ
ዳኛው የወንጀሉን ክስ ሰማና ልጁን እንዲህ ሲል ጠየቀው!
ዳቦ ሰርቀህ ነበር?"
ልጁ - እያፈረ "አዎን ሰርቂያለሁ"
ዳኛው - "ለምን?"
ልጁ - "አስፈልጎኝ"
ዳኛው - "መግዛት አትችልም ነበር?"
ልጁ - "ገንዘብ አልነበረኝም"
ዳኛው - "ከቤተሰብህ ለምን አትወስድም?"
ልጁ - "እናት ብቻ ናት ያለችኝ፥ እሷም በጠና ታምማ እቤት ተኝታለች"
ዳኛው - "ምንም ስራ የለህም?"
ልጁ - "መኪና እጥበት እሰራ ነበር፥ ነገር ግን እናቴን ለማስታመም አንድ ቀን ከስራ ስቀር አባረሩኝ"
ዳኛው - "ሌሎች እንዲረዱ አልጠየቅኽም?"
ልጁ - "በጧት ነው ከቤት የወጣሁ፥ እንዲረዱኝ 50 የሚሆኑ ሰዎች ጋ ሄጄ ነበር፤ አንድም የሚረዳኝ ሰው ግን አላገኘሁም፤ በቃ መጨረሻ ላይ ይህንን
መጥፎ ውሳኔ ወሰንሁ"
ጥያቄው ሲጠናቀቅ #ዳኛው ውሳኔ ማስተላለፍ ጀመረ።
እንዲህም አለ
"ዳቦ መስረቅ፥ በተለይ የተራበ ልጅ ዳቦ መስረቅ እጅግ በጣም አሳፋሪ ወንጀል ነው፤ እናም እኛ ሁላችንም የዚህ ወንጀል ተጠያቂ ነን። እኔን ጨምሮ በዚህ ቤት ውስጥ ያላችሁ በሙሉ ወንጀለኛና ተጠያቂ ነን። ስለዚህ እያንዳንዱ በዚህ ችሎት ላይ የታደመና እዚህ ቤት ውስጥ ያለ አስር (10) አስር ዶላር እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ማንም ሰው ሳይከፍል መውጣት አይችልም በማለት አስር ዶለር ከኪሱ አውጥቶ ወረቀት ላይ መመዝገብ ጀመረ።
በተጨማሪ ዳቦ ቤቱ የተራበ ልጅ ለፖሊስ አሳልፎ በመስጠቱ 1000 ዶላር እንዲከፍል ውሳኔ አስተላለፈ።
ይህ በ24 ሰአት ውስጥ ካልተፈጸመ ፍርድ ቤቱ ዳቦ መደብሩን ያሳሽጋል።
ፖሊስም የተራበ ልጅ ፍርድ ቤት በማቅረቡ 1000 ዶላር እንዲቀጣለት ወሰነ።
የተወሰነለትን ገንዘብ ለልጁ ካስረከበ በኋላ ፍርድ ቤቱ ልጁን ህዝብ ፊት ይቅርታ ጠየቀው!
የዳኛውን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ በችሎቱ ላይ የነበሩ ታዳሚዎች ሁሉ በእንባ ተራጩ።
የልጁ እጅ ላይ የነበረው ሰንሰለት ተፈታለት። ዳኛው እንባ እየተናነቀው ሲያወራ ልጁ ያይ ነበር።
በኛ ማህበረሰብ ውስጥ ያለው የፍትህ ስርዓት ግን ምን ይመስላል?
የተራበ ልጅ ዳቦ ሰርቆ ቢያዝ ወንጀሉም እፍረቱም ለህዝቡ ነው፡፡
ፅሁፉን ከዚህ ቀደም አንብባችሁት ይሆናል ነገር ግን በኢድ ቀን ብዙ የተራቡ የተቸገሩ ጎረቤቶች አሉ...ደግሞ ዘንድሮ ረመዳን የኑሮ ዉድነት ጣራ ነክቶ የተፆመ ረመዳን ስለሆነ ለኢድ በደስታ ቀን እነሱ ግን ደስታን በሌሎች ብቻ እያዩ የሚያከብሩ ስላሉ እነሱን በተቻለን አቅም መዘየር እንዳለብን እና ዘካተል ፊጥርን መስጠት እንዳንዘነጋ ፡፡
በተጨማሪ ደግሞ ብዙ ሰዉ በረመዳን ከተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ራሱን ያገላል በረመዳን ያልተጠቀመዉን ቀዷዉን ለማዉጣት ይመስል ከረመዳን ቡሀላ ማህበራዊ ሚዲያን ከልክ ባለፈ መልኩ ሲጠቀም እናያለን...መቼም ምክንያቱ ሸይጧን ተፈቷል ነዉ....
በረመዳን ላይ አንድ በሚዲያ ፍቅር ተብየ ሞንጨር ያደረገዉ...ሸህየዉን የሚያስቅ ፈትዋ ይጠይቃቸዋል....
ሼኺ በጣም ጥርጣሬ ዉስጥ እገኛለሁ..አንድ የማፈቅራት ልጅ ነበረች እሷም በርግጥ ታፈቅረኛለች የተዋወቅነዉ በFacebook ነዉ በአካል አንተዋወቅም፡፡ ፍቅር ከመሰረትን ለአመት 3 ወር ይጎለዋል ..ረመዳን ከመግባቱ በፊት በጣም እናወራ ነበር፡፡ነገር ግን ረመዳን ሊገባ አንድ ለሊት ከቀረዉ ለት ጀምሮ በፍፁም ሚዲያ ላይ በfacebook በtelegram በimo. የለችም ...ስደዉልም ቁጥሯ አይሰራም ከኢንተርኔት offline ነች
...እናም እኔም ጥርጣሬ የሆነብኝ ነገር እሷን እያሰብኩ በዉስጤ ሰዉ አይደለችም ሸይጧን ነበር ሲጀነጅንህ የነበረዉ እና ልጂቱ ታስራ ይሆናል በማለት ዉዝግብ ላይ ነኝ ሼይህ ሲል
ሼይሁ በሳቅ ....
እናም በሚዲያ ወሬ ብዙዉ በረመዳን ይቀንሳል የሚያቆምም አለ ...በዛዉ ሚዲያን ለመራቅ መሞከር እንጂ ረመዳን ተፈታ ተብሎ በረመዳን ያቆምንበትን የሚዲያ ቀዷን ከማዉጣት እንቆጠብ
ዉድ የቻናል ቤተሰቦች መልካም ኢድ አልፈጥር በአል ተመኘሁ፡፡ ለተጨቆኑ በግፍ የተገደሉ የጎንደር ሙስሊሞችን እንዳንረሳ የሶስት ቀን ሀዘን ብቻ ሆኖ እንዳይቀር....በተጨማሪ የደባርቅ ሙስሊሞች እና
በትግራይ ክልል የሚኖሩ የሁሉም እምነት ተከታዮችን በማስታወስ እናሳልፍ ..ደግሞ በትግራይ ክልል ያለዉን አስባችሁታል?? ከሁለት አመት በላይ በጦርነት ላይ ናቸዉ የኑሮ ዉድነት አሁን ባለንበት እያየን ነዉ..ትግራይ ክልል እንዴት ፁመዉ እንዴት ኢድን ያከብሩ ይሆን??
በትግራይ ክልል ያሉ ሚስኪኖች እንዴት ይሆን በአልን የሚያከብሩት?? ይሄንን በማሰብ በአልን ብናከብር ኸይር ነዉ...ለምን አይታወቅም ነግ በኔ ነዉ ዱንያ በደስታና ሀዘን ሀዲድ የምትረማመድ ነች ..ነገ ፈጣሪ የኛን በምን እንደፃፈዉ አናቅም...የጦርነትን ክፋት ችግር ጭንቀትና ስነልቦና ጉዳት እንዴት እንደሚያደርስ
የሚያቀዉ ጦርነትን ያየ ብቻ ነዉ...ጦርነት የከባድ መሳሪያ ድምፅን ያልሰማ ያላየ ከአየዉ ጋር በጭራሽ ሊረዳ አይችልም ...በዛ ሰዉ ጫማ እስካልተራመድክ ድረስ የዛን ሰዉ ህመም ችግር መረዳት ይከብዳል፡፡
ትግራይ ወራሪ ሀይል መጥፎ ጎናቸዉ ቢበዛም ግን እንደሰበአዊነት እኛስ አላህ ዘራችንን ትግሬ አርጎት ቢሆንስ? አሁን በዚህ ሰአት እኛ ትግራይ ክልል ሁነን በነበረን ምን ይገጥመን ይሆን ?? ብለን ማሰብ መቻል አለብን...ኢትዮጲያ ዉስጥ ለፓለቲካ ጥቅም ተብሎ በዘር በሀይማኖት ዉስጥ ተሰግስገዉ ምንም የማያቀዉን የደሀ ልጅ ሞት አላህ በቃችሁ ይበለን...
አላህ ችግርና መከራን አንስቶ በደለኛን የሚቀጣበት ፣ሰላምና ፍትህን የሚያሰፍንበት ኢድ እንዲሆንል እመኛለሁ!
ሙስሊሞችን የበደሉ የጨቆኑ የገደሉትን አላህ ሂድያ ሰጥቶ ኢስላምን ይወፍቃቸዉ ካልሆነ አላህ በዱንያ የሚታይ የማያዳግም ቅጣት ያስጣቸዉ ያረብ
መልካም የኢድ አልፈጥር በአል ተመኘሁ ..ፁመዉ ተራቡት ከሚባሉት ባርያዎቹ ሳይሆን ለፆመኞች በተዘጋጀዉ በር ከሚገቡት ባርያዎቹ ያድርገን
ኢድ ሙባረክ!!!
https://t.me/IslamisUniverstiy_public_group
3.2K viewsedited 09:36