Get Mystery Box with random crypto!

በዒድ ሰላት ወቅት የተከሰተው ክስተት በክርስቲያኑና በሙስሊሙም መካከል የተፈጠረ አይደለም። አንዳ | ISLAMIC SCHOOL

በዒድ ሰላት ወቅት የተከሰተው ክስተት በክርስቲያኑና በሙስሊሙም መካከል የተፈጠረ አይደለም።

አንዳንድ አካላት ችግሩን ከመንግስት ጋር ለመሰያያዝ መሞከራቸውም የተሳሰተ መሆኑን አረጋግጠናል።

በዒድ ሰላት ወቅት የተፈጠረው ችግር ምን እንደሆነ በስፍራው ከነበሩ በጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎቻችን ደርሶናል። በአንድ ፌደራል ፓሊስ ድንገት (ባርቆብኝ ነው ብሏል) በተተኮሰ አስለቃሽ ጭስ ምክንያት የተፈጠረ ግርግር ነበር።የአስለቃሽ ጭሱ እንደተተኮሰ በቦታው የነበሩ የበአሉ ታዳሚዎች በከፍተኛ ደረጃ ተደናግጠዋል።ወደ ፌደራል ፓሊሱ በማቅናት ይዘውታል።ፓሊሱም ድንገት ባርቆበት እንደሆነ ተናግሯል ሆኖም ህዝቡ ከፍተኛ የሆነ መረበሽ ውስጥ ስለገባ ለመግባባት አልተቻለም።

በመጨረሻም የፌደራል ፓሊሱ በኤግዢቢሽን አካባቢ ወደ ሚገኘው የፌደራል ፓሊስ ካምፕ እዲገባ ተደርጎል።ይህን ተከትሎ ሌሎች ፓሊሶች ከካምፑ ሲወጡ ተኩሱ የፈጠረው ግርግር ባለመረጋጋቱ ችግሩ ሊባባስ ችሏል።

ከዚህ በተረፈ ከስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ኦርቶዶክስ እምነት ተለታዮች ጋር ችግሩን የሚያያይዘው ነገር አለመሆኑ ተረጋግጧል።በመንግስት በኩልም ሆነ ተብሎ የተፈጠረ ችግር አለመኖሩን አረጋግጠናል።በመሆኑም ህዝቡ እንዲረጋ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

የአዲስአበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት


ይሄን video ይመልከቱ አስለቃስ ጭሱን ሲተኩሱ አንስቶ ወደ እነሱ
ወላሂ ጀግና ነዉ