2021-10-08 09:16:47
#ግድ_እስከምንታመም_አንጠብቅ
አሚር ሰይድ
28/01/2014
ቻርለስ ዳርዊንቻርለስ ዳርዊንን ምን ያህል ያቁታል??እስኪ ስለቻርልስ ዳርዊን አንዳንድ ነገር ልበላችሁ
ቻርለስ ዳርዊን 40 አመት ያህል በከባድ ህመም እየተሰቃየ በሽተኛ ሁኖ ኑሯል፡፡
እንዴት አርባ አመት ያህል ሊታመም ቻለ??ብላችሁ ልትጠይቁ ትችላላችሁ ..ግን ብቸኛ መልስ አለዉ መልሱም ድንበር ማለፍ ይሆናል፡፡
ቻርለስ ዳርዊን ህይወት ያላቸዉ ነገሮች ከዝቅተኛ ደረጃ ተነስተዉ ደረጃ በደረጃ እየተለወጡና እየተሻሻሉ በመምጣቱ ዛሬ በተለያዩ መንገድ ሄደዉ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሰዋል..በዚህ መሰረት ጦጣና ዝንጆሮ አሁን በዕድገት ሂደት ከሰዉ የተለዩ ቢሆኑም ጥንት አንድ የጋራ መነሻ ሳይኖራቸዉ አይቀርም በማለት ፈጣሪ ነዉ የፈጠራቸዉ ማለትን ትቶ ተከራክሯል፡፡
በወቅቱ በዚህ አስተሳሰብ በሰዎች መካከል ትልቅ ንትርክ ክርክርና ዉዝግብ አስከተለ ፡፡ በተማሪዎች ላይ ችግር ፈጠረ...አንዱ የሚለዉን ሌላዉ አይቀበለዉም ..ለፈተና ብለዉ የሚያጠኑት መልስ ለአካባቢዉ ህዝብ አመለካከት ተለየባቸዉና ዉዥንብር ሆነ፡፡
ይሄን የሚያከፍር አስተሳሰብ ይዞ የመጣዉን የቻርለስ ዳርዊን አመለካከት ይሄዉ ዛሬ ድረስ አለምን በዚህ አስተሳሰብ ቀርፆ ኢትዮጲያ በእስልምናም በክርስትናም ሀይማኖት ጥርት ያለ እምነት አለን ብለን የምናስብ ይሄን ከዝንጆሮ መጣችሁ እየተባልን እየተማርን አድገናል ነገ ከነገ ወዳ ልንሞት እየተዘጋጀን ነዉ ግን እስከ መቼ???
ግን ይሄን ሀሳብ ያመጣዉ ዳርዊን የአእምሮና የጤና እክል ችግር ያለበት ሰዉ ነዉ...እና እንዴት በዚህ ታማሚ የታመመ አስተሳሰብ በታመመ አመለካከት ለትዉልድን ህመሙን ማካፈል ለምን አስፈለገ???መቼ ድረስ ይቀጥል ይሆን ??? አይታወቅም
እስኪ ስለዳርዊን ሰዉ የመጣዉ ከዝንጆሮ ነዉ ብሎ የሚያከፍር ከእስልምና የሚያወጣ አመለካከት ያመጣዉን ግለሰብ አንዳንድ ነገሮች ጀባ ልበላችሁ
ዳርዊን
☞ገና የስምንት አመት ህፃን እያለ እናቱ ሞተችበት ፡፡
☞ እሱን ያሳደገችዉ ታላቅ እህቱ ነበረች..
☞የዳርዊን አባት በፀባዩ ሰዎችን የመጫን ባህሪ የነበረዉ በጣም አስቸጋሪ ሀይለኛና ግዙፍ 150 ኪግ የሚመዝን ሰዉ ነበር፡፡ በአባቱ ባህሪ ዳርዊን ይበሳጭ ይናደድ ነበር፡፡
☞ ዳርዊን በትምህርት በኩል አልተሳካለትም ስለህክምና እንዲያጠና ወደ አንድ ዩኒቨርስቲ ቢላክም ከዚያ ወድቆ ተባረረ፡፡ ከዚያም ወደ ዝነኛዉ ኬምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ተልኮ ስለመንፈሳዊ ትምህርት እንዲከታተል ተደረገ በዚህም ቢሆን አልተሳካም፡፡
የዳርዊን ዝንባሌ ሁልጊዜም ፈረስ መጋለብ ተራራ መዉጣትና ወዘተ እርባና ቢስ ነገሮች ላይ ስለነበር አባትየዉ ይበሳጭበት ነበር፡፡ቤተሰብ አሰዳቢ ከንቱ ልጅ እያለ ይሰድበዉ ነበር ...በትምህርቱ ሰነፍ ስለሆነ አልሳካለት ሲል አንድ መርከብ ላይ ተቀጥሮ ሊሄድ ወሰነ...ይህም የመርከብ ጉዞ ዓለምን በከፊል እንዲዞር ያስቻለዉ ነዉ፡፡
ከመርከብ ጉዞዉ ሲመለስ ሰዉ በዝግመተ ለዉጥ ከጦጣና ዝንጆሮ ነዉ የመጣዉ ማለት ጀመረ
ዳርዊን በሀይማኖት በኩል ለሚሰነዘርበት ነቀፋ የራሱ ጥርጣሬ ነበረዉ፡፡
#ለምሳሌ እግዚአብሄር እዉነት ደግና ኑህሩህ ከሆነ ጌታ ሰዉ ባህሪዉን እየገረፈ ሲገዛ ወይም ሚስኪን እንስሳትን እንደዚያ ሲያሰቃይ ወይም ተዉሳክ የሰዉን ልጅ በተለይም የታዳጊ አገሮችን ህፃናትን እንደዚያ እያሰቃየ ሲፈጅና ሲያረግፍ እያየ እንዴት አስችሎት ዝም ይላል??ወዘተ እያለ በማሰብ ግራ ይጋባ እንደነበር ተመዝግቧል፡፡
በዳርዊን አስተሳሰብ ነገሮች በሳይንሳዊ መረጃዎች እየታዩ መጠናት አለባቸዉ የሚል ነዉ፡፡ ሆኖም ዳርዊን ይሄን አመለካከት ለሰዎች ማስረፅ ሲጀምር ህይወቱን በሰላምና በጤንነት እንዲመራ አልታደለም ከባድ የጤና ጉድለት ነበረበት፡፡
የዳርዊን ህመምና የመጨረሻ ዘመን ታሪኩ የሚያስገርምና ዛሬም ትምህርት ሰጪ ነዉ፡፡ይላሉ ሳይንቲስቶች
ዳርዊን ከአምስት አመት የባህር ጉዞዉ ሲመለስ በአመቱ ጤናዉ መታወክ ጀመረ ..ይህ በሽታ ለአርባ አመት ያህል አሰቃይቶት ኖረ ፡፡ ለመሆኑ የታመመዉ በሽታ ምን አይነት ነዉ??ስም ለመስጠት የሚከብድ በሽታ ነበር
#ለምሳሌ:- ሆዱን ይቆርጠዋል፣አንጀቱን ክፉኛ ያመዋል፣ጋዝ ያበዛበታል፣ያስታዉከዋል፣አልፎ አልፎም ልቡ እጅግ በጥድፊያ ይመታል፣ ድካምና አቅመቢስነት ይሰማዋል ፣አንዳንዴም እንደማንቀጥቀጥ ይለዋል ..በአጭሩ ህመሙ ይሄ ይሄ ነዉ ማለት አይቻልም ሁሉም አይነት ህመም ያሰቃየዉ ነበር ፡፡
ህመሙ በጣም ሲጠናበት ከከተማ ወጥቶ ወደ ሀገር ቤት ገጠር ገብቶ መኖር ጀመረ...
☞ አንዳንድ ሀኪሞች እንደተናገሩት በሰዉነቱ ዉስጥ ምንም በሽታ ስላላገኙበት የዳርዊን ችግር የራሱ የመንፈስ ጭንቀት ወይም የአእምሮ ድክመት ያስከተለበት ቀዉስ መሆኑ ያስታዉቃል ይሄ ደግሞ ህመሙ አካላዊ በሽታ ሳይሆን ህሊናዊ ነዉ፡፡
በዘራቸዉ ለራሱ የዳርዊን እናትና አባት ወገን አልፎ አልፎ የአእምሮ መታወክ የነበረባቸዉ ሰዎች እንደነበሩ የዳርዊንም ችግር የዚሁ የዘር ችግር ሊሆን ይችላል
ብዙዎች የዳርዊን የመታመም ምክንያት በፈጣሪ ስራ ገብቶ የሰዉ ልጅ ከዝንጆሮ ነዉ የመጣዉ ማለቱ ይህ ከአንድ ሀይማኖት አለዉ ተብሎ የማይጠበቅ ስለሆነ ፈጣሪ ለሰዉ ማስተማሪያ በህመም እንዲኖር አድርጎት ነዉ ይላሉ
በዚሁ በሽታ ቀን ማታ ለአርባ አመት ያህል እንደተሰቃየ በሞት ተለይቷል...ታዳ አርባ አመት ታሞ መሞቱ የፈጣሪ ቁጣ አይደል??
በአጠቃላይ በአላህ ህግ ላይ ጭማሪ የሚጨምር እንደ ቻርለስ ዳርዊን አይነት ህይወት ለመኖር ሊገደድ ይችላል...አሁን ዘመን ላይ ስንት ከዲን ያፈነገጠ አስተሳሰብ እየሰማን ነዉ፡፡
ዛሬ ዘመን ላይ ተራዉ ጃሂል ብድግ ብሎ ያልበላዉን እያከከ በማያገባዉ ፈትዋ ሲሰጥ ይታያል...ለምሳሌ ሙስሊሞች ብዙ ስራ መስራት ሲጠበቅባቸዉ መዉሊድ እናክብር ፣ አረ በጭራሽ አታክብር፣ አያገባህም እኔ ላክብር እየተባባሉ በሚዲያ የስድብ ናዳ ከአንዱ ወገን ወደአንዱ ወገን ሲንከባለል እያየን ነዉ... አንዱ ሙነሺድ ተብየ በFb page >>> መዉሊድ የሚያከብርን ሰዉ አታክብር አይባልም፣የማያከብርን ሰዉ በግድ አክብር አይባልም፣የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን መዉሊድን ለማክበር ከአላህ መመረጥን ይጠይቃል፡፡<<<
ብሎ ሲለጥፍ ገረመኝ....
☞ዛሬ ደግሞ እኔዉ የማቀዉ የሰፈሬ ልጅ አብሮ አደጌ አጂ ነብይ ሴት ጋር ሲያወራ ሲጋተት ሌላም ሲሰራ የነበረ በሙዚቃ መሳሪያ የተቀናበረ ነሺዳ አዉጥቶ ክሊፑን ሳይ አይኔን ማመን አቅቶት በጣም ገረመኝ ....ቆይ ግን ሙነሺዶች የሚሰሩት ስራ ምንድን ነዉ ?? ነብይን እወዳለሁ እያሉ በTv መስኮት ለኒሳዖች እኛን የሚወደን ማን ነዉ የሚሉ አይመስሉም?? ነሺዳ ሲመረቅ የሚገቡት ሴቶችስ ግን ለምን ይሆን ገብተዉ ሙነሺዶችን ልባቸዉ ፍስስ እስከሚል ድረስ የሚመለከቷቸዉ???
አሊሞች ግን ለምን በዚህ ዙሪያ ፈትዋ ለመስጠት ፈሩ??? አሁን ላይ እኮ ፈትዋ በራስ ዝንባሌና በሞቀ ስሜት ዝና በሚፈልጉ አስመሳይ ዲን ጠቃሚ መስለዉ ሌላ አላማ ባላቸዉ ሙነሺዶች ፈትዋ እደተሰጠ ዲነል ኢስላም ያለመሪ መኪና እየተሾፈረ አሊም ደግሞ ያንን መሪ የሌለዉ መኪና ከሆላ ሁነዉ በሄደበት ሲገፉ እየተመለከትን ነዉ፡፡
ሌላዉ አልበቃ ብሎ የወንድ ሙነሺዶች ሲገርመኝ ደግሞ ሴት ነሺዳ አዉጥታለች ሲሉኝ አላመንኩም ...እኔ ለማመን ግድ መስማት አለብኝ ብየ ሴት ሙነሺድ መምጣቷን አረጋገጥኩ...ምን ይባላል አሊም ተብየዎች መሪ የሌለዉን መኪና ከሆላ እየተከተሉ በሄደበት እየገፉ እንጂ ....
4.9K viewsedited 06:16