Get Mystery Box with random crypto!

ISLAMIC SCHOOL

የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL
የሰርጥ አድራሻ: @islam_and_science
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 15.55K
የሰርጥ መግለጫ

✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 18

2022-04-27 23:13:35 <<የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል>>
አሚር ሰይድ

ራዕይ በተግባር የሚቀረፅ ህልም እንጂ በአእምሮ ብቻ የምናስበዉ መዳረሻ አይደለም፡፡


አንድ ልጅ እናቱ ጋር ይኖራል ከዛም እንቁላል ይሰርቃል እናቱ ዝም አለችዉ ከዛ በሂደት የሌላ ሰዉ ዶሮ ይሰርቃል ከዛም ሌባ ሲባል እናቱም ስትቆጦ
ልጁም"" እናቴ ምነዉ በእንቁላሉ በቀጣሽኝ ዶሮ ባልሰረኩ "" አላት..

ምን ለማለት ፈልጌ ነዉ ሞጣ ላይ ባደረጉት ድረጊት ስላልተቀጡ አሁንም በእነሱ አልፈረድም
የእኛ ዝምታ ጥግ ደረሰ
የእነሱ ጥጋብ ሞልቶ ፈሰሰ
ችግሩ ከራሳችን ነው ጠንካራ ሁኖ ማሳየት አቃተን ተጠራቅመን የአገሪቱ ከግማሽ በላይ ነን እያሉ ወሬ ስም ብቻ ...የአሁን ዘመን ሙስሊም እሰዉ ቤት የሄደ እንግዳ ይመስል መሽለጥለጥ ማሽቃበጥ ይወዳል፡፡ የሀይማኖት መሪ ተብየዎች በተለያየ ጊዜ ሙስሊሞች ሲገደሉ ሲፈናቀሉ ለሙስሊሙ ከመድረስ ድምፅ ከማሰማት ይልቅ ከመንግስት ሹመኛ ጋር ፎቶ መነሳት ይቀላቸዋል፡፡ጠና ቢል ቢሰሩ ሰላማዊ ሰልፍ ወይ በየመስጊዱ ተቃዉሞ ከዛ ቆፍጠን ያለ የአቋም መግለጫ አንብቦ ይበተናል ሙስሊሙ ቁጣዉን በሰልፍ በመስጊድ ባነር አሰርቶ ፎቶ ተነስቶ በሚዲያ ይለቃል ከዛ ይረሳል በዛዉ ተድበስቦሶ ያልፋል፡፡
ከመንግስት ጎን ይለጠፉና የእብድ ገላጋይ ዲንጋይ ያቀብላል ነዉና ነገሩ መንግስት የጠቀሙ መስለዉ ሙስሊሙን ግን እንዲጎዳ ያደርጋሉ፡፡


☞በሂደት የ ጎንደርን መስጅድ ለመገንባት እና ወንድሞቻችንን ለማቋቋም ተብሎ ገንዘብ ይሰበሰባል ....ዲኑን እየተጫወቱበት ያሉ የሴት ሊቀመንበር ሙነሺዶች ስለ ጎንደር ጥቃት ነሺዳ አዘጋጅተዉ ለአንድ ቀን ይለቀሳል....ከዛ በቲሸርትና በባነር የጎንደር ሙስሊሞች ህመም የኔም ህመም ነዉ ይባላል....ከዛስ .....ከዛማ ዝም ዝም ነዋ ሌላ ምን ይፈጠራል፡፡ ሙስሊሙ ልቡ በዱንያና በሴት ፍቅር ታዉሯል አዉርቶ ይቀራል ከዛ እነሱ እንደ ስለት በአመት አንዴ የሚፈልጉትን አጀንዳ ያስፈፅማሉ፡፡
☞የሚገርመዉ አሁን ድረስ ብሄርን ከእስልምና የሚያስበልጥ መኖሩ ነዉ ...የዛሬ 2 አመት በፊት በፁሁፍ ስለአማራ ክልል ሙስሊም ፅፌ የአማራ ክልል የሚኖሩ ሙስሊሞች ተችተዉኝ ከቻናል ፁሁፉን ለመሰረዝ ተገድጄ አጥፍቸዋለሁ ..የዛን ጊዜ የተናገርኩት በሁለት አመቱ በጎንደር ሙስሊሞች ላይ ደረሰ ...ምን ዋጋ አለዉ
በፊት ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ
አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ

እናም እኛ ሙስሊሞች የምናየዉ የዛሬን እና የነገን ብቻ ነዉ እንጂ ከትናንት ወዳ ምን ነበር? ከነገ ወዳስ የዛሬ አመትስ ምን ይፈጠራል?ብለን ማሰብ ስለማንችል እነሱ ግን ለወደፊት 50 ወይ 60 አመት ፕላን አዉጥተዉ ሲንቀሳቀሱ በእነሱ ወጥመድ እንወድቃለን፡፡
ስለ ኢትዮጲያ የምንሰማዉ የ13 ወር ፀጋ ነገር ግን የምናየዉ የ13 ወር ለሙስሊም ጥላቻ ነዉ፡፡

☞ግን የጎንደር ሙስሊሞች በረመዳኑ በጥይት ያስፈጠሯቸዉ በአደባይይ ኢፍጣር ላይ የታቀደ ነበር ..ግን በቀብሩ ጀመሩት እንጂ ..ግን ይሄ የአደባባይ ኢፍጣር እኔ ብዙም አልተዋጠልኝ ጉዳቱ ግን አንደ ጎንደር ያሉ ሙስሊሞችን ዋጋ አስከፍሏል፡፡
እኛ ሙስሊሞች የምንዋረደዉ በሱና በኸይር ስራ መሸቀዳደም ትተን ከሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች ጋር ፉክክር ስንገባ ነዉ ዉድቀታችን መታወቅ አለበት፡፡ አሏህ በተከበረ ቅዱስ ቁርአኑ በዱንያ እነሱ እንደሚደሰቱ ግን በአኼራ እንደሚቀጡ ነግሮናል እነሱ በስኳር መንፈስ መንገዱን አደባባዩን እንደፈለጉ ሲጠቀሙበት እኛ ሙስሊሞች እነሱ ጋር ምን አፎካከረን?? የነብዩ ሱና ይበልጣል ወይስ ከአነሱ ጋር ፉክክር??
☞በደሴ በነበረዉ ኢፍጣር አይቻለሁ ሴቶች እንደ ኢድ ልብስ ለብሰዉ ተኳኩለዉ ፊታቸዉን በቡርሽ ቦርሸዉ ነበር የመጡት እናም በዛን ጊዜ ታዳ በዛ የአይን ዚና የእጅ ዚና የአፍ ዚና ወዘተ ወንጀል መሰራቱ ይቀራል ወይ?? በአደባባይ ኢፍጣር ወንድ ሴት ፊት ለፊት እየሆነ ሲያፈጥሩ አይተናል ይሄ የነብዩ ሱና ነዉ ወይ??
☞የኢፍጣሩ ብር ከተለያዩ ባንኮች እስፓንሰር ተደርጓል ..በወለድ የሚሰሩ ባንኮች ለዚህ ኢፍጣር ሰጥተዋል ...ግን ይበቃል ወይ?? ይሄ ጥያቄዉ ለአሊሞቻችን ነዉ

☞ በተለይ ሴቶች በTik tok በfb youtube ለመልቀቅ ነበር አመጣጣቸዉ...ብዙ ሰዉ የሄደዉ ማለት ይቻላል ብዙዉ ኢንተርኔት ላይ ተጥዶ tik tok እና fb ላይ ነበር
☞ ከፍጥሪያዉ ቡሀላ አንዳንድ ጀመአዎች በተለይ የአህባሽ አቂዳ የሚከተሉ ለብቻቸዉ ተገንጥለዉ ወንድ ከሴት ተቀላቅለዉ መንዙማ ከፍተዉ ሲጨፍሩ አይቻለሁ ...
ይሄ ሁሉ ማስረጃ በስልኬ video አለኝ ግን ሁሉም በሚዲያ ግልፅ ማድረግ አግባብ አይደለም፡፡
መዉሊድ የተጀመረዉ ቀስ በቀስ ነዉ ወደ ሰዉ ልብ የሰረፀዉ ..የኛም ህዝብ ይሄ የአደባባይ ኢፍጣር በአመት አንዴ በሆነ ቁጥር የሚመጣዉ ትዉልድ ሱና ነዉ ብሎ እንዳይዘዉ ያሰጋል
እናም አላህ ካደረሰኝ ለሚመጣዉ አመት ረመዳን ከአደባባይ ኢፍጣር ተብየ አዲስ የመጣ አንድነትን ለማሳየት ተብሎ ብዙ መዘዝ ይዞ ለሚመጣ እኔ አልሳተፍም...መታወቅ ያለበት ይሄ የራሴ ብቻ አመለካከት ነዉ፡፡

☞ በፊት ከዛሬ 3 አመት በፊት ጀምሬ ሙነሺዶች የያዙት አቋም ከባድ ነዉ ነቢይ እያሉ ሌላ ነዉ እቅዳቸዉ እል ነበር...በዚህ የተነሳ ብዙ ሰዉ ይወቅሰኝ ነበር...ይሄዉ ዛሬ አሊም የሚሰማ ጠፍቶ ፈተዋዉም ደአዋዉም ከሙነሺዶች ሆነ ...እኔ የሚገርመኝ በተለያዩ tv ቻናሎች ስለኢስላም ሀይማኖት ሲባል እነሱ ይቀርባሉ ..ግን የክርስቲያን ዘማሪዎች ክርስትናን ወክለዉ ቀርበዉ አያቁም እነሱ አምላክ ነዉ ብለዉ ለያዙት ጥርት ያለ ስራ እየሰሩ ነዉ በtv program ወሬ የለም...የኛ ሙነሺዶች ግን በተለያየ Tv ቀርበዉ ሲበጠረቁ እያየን ነዉ ...ነሺዳና ሙዚቃ መለየት የማንችልበት ዘመን ደርሰናል...አሁንም ስለጎንደር ሙስሊሞች ነሺዳ አዉጥተዉ አንድ ደቂቃ አስለቅሰዉ ያስረሱናል፡፡

ራዕይ በተግባር የሚቀረፅ ህልም እንጂ በአእምሮ ብቻ የምናስበዉ መዳረሻ አይደለም፡፡

ብቻ ከባድ ነዉ ብዙ ማለት ይቻል ነበር መፃፍ ሳልፈልግ ጊዜ አስገድዶኝ ነዉ ..ትናንት ዛሬም ጎንደር ደዉየ ነበር የሚሰማዉ ወላሂ በጣም ከባድ የሚያስለቅስ ነዉ ...

ዛሬ የረመዳን 27 ለይል ነዉ ሌላ ማድረግ ቢያቅተን ሳንተኛ በዱአ እንገዛቸዉ ...አላህ ይሰማን ይሆናል ኢንሻ አሏህ
በዱአ የጎንደር ሙስሊሞችን እንዳንረሳ

አዉፍ በሉኝ በችኮላ በ30 ደቂቃ ዉስጥ ያለዝግጅት የተፃፈ ነዉ....አደራ አደራ ለጎንደር ሙስሊሞች ዱአ እንድናደርግ

https://t.me/IslamisUniverstiy_public_group
4.7K viewsedited  20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 06:04:24
" ንገሩ ለነዛ "
ወዲያ ወደ ጎንደር
ጥሰው ክብር ድንበር
ማን አለብኝ እብሪት
ለጫሩ እሳት ክብሪት
ንገሩ ለነዛ ..
የዝምታን ዋጋ በፍርሀት ላሰሉ
ንገሩ ለነዛ መስጊድ ላቃጠሉ

ታሪክ የማይረሳው ያፄ በደል አዝሎ
ታግሶ በኖረ ሀገር ትቁም ብሎ
ሰላም ይሻል ብሎ አንገት ስለደፋ
ተቻችሎ ሳይሆን ችሎ ቀን ቢገፋ
መስሎ ከታያችሁ ሙስሊም እንደፈሪ
መታደል ነው ለሱ ለዲን የሞት ጥሪ
ንገሩ ለነዛ .....
የዝምታን ዋጋ በፍራት ላሰሉ
ንገሩ ለነዛ ሙስሊሙን ለጠሉ

አዎ ንገሯቸው እምነት ላይ ላሴሩ
ንፁሀንን ገለው አጉል ለፎከሩ

ይሻል ተብሎ እንጂ መኖሩ ተዋዶ
ድንበር ለጣሰማ እሱው ወዶ ፈቅዶ

እንኳን ብርቱዉ አማኝ _ የኔ አይነቱም ሰነፍ
በእምነቱ ለመጣ _ ከፊት ለመሰለፍ
በጭራሽ አይሰጋም _ ከሞት ለመጋጨት
ክብሩ ነዋ ለሱ
ለስልምናው ሙቶ _ ለጀነት መታጨት
.... ንገሩ ለነዛ .....

#ሼን
https://t.me/IslamisUniverstiy_public_group
3.6K views03:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 22:33:01
#Stop_Muslim_Genocide_in_Gondar
በሚዲያ profile በማድረግ ሌላ ማድረግ ባንችል በፆመኛ አንጀታቸዉ ለሚሰቃዩ የጎንደር ሙስሊሞች ድምፅ እንሁናቸዉ
3.1K views19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 22:32:49
======
የቤተ ክህነቷ ሰዎች እነ ዲያቆን አባይነህ ካሴ በዛሬው ዕለት በጎንደር ሙስሊሞች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የሽብር ጥቃት እንዲካሄድ ያደረጉት የጎንደር ሙስሊሞች ጎዳና ላይ እናፈጥራለን ብለው ዝግጅት መጀመራቸውን ተከትሎ ቀድሞ ለማክሸፍ መሆኑን በግልፅ አሳውቀዋል።

የሽብር ጥቃቱ አቀናባሪዎች ለኛ ባይጠፉንም በግልፅ «እኛ ነን!» ብለው መምጣታቸው መልካም ነው።

ለመሆኑ ቢታወቁስ የሚያግዛቸው እንጂ የሚቀጣቸው መንግስት መች አገኙና!
3.0K views19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 22:21:26 #Stop_Muslim_Genocide_in_Gondar
3.2K views19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 22:16:08 አስቸኳይ መልዕክት ነው። ሼር አድርጉት

በጎንደሩ ጥቃት ሌሎች አከባቢዎች ያሉ ክርስትያን ወንድሞቻችን ተጠያቂ አይደሉም፣ ልንጠብቃቸው ይገባል!

ጎንደር ለተፈጸመው ድርጊት ተጠያቂው ጥቂት የጎንደር አክራሪ እንጂ በሌሎች አከባቢ ያሉ ክርስትያን ወንድም እህቶቻችን አይደሉም።

ስለዚህም በየትኛውም ቦታ የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታይ ወንድም እህቶቻችን፣ ወገኖቻችንን ምንም አይነት ጥቃትም ይሁን ሌሎች ነገሮች እንዳይደርስባቸው ጥበቃ ልናደርግ ይገባል።

አንዳንድ አካላት ኃይማኖታዊ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ እየሰሩ በመሆኑ እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ ሙስሊም ለሀገር ሠላምና መረጋጋት ሲል የራሱን ደህንነት እንዲጠበቅ፣ ሁከትና ብጥብጥ ከሚፈጥሩ ጉዳዮች እንዲርቅ፣ ከሌሎች ኃይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ አጥፊዎችን እንዲያወግዝና መንግስት ጥፋተኞች ለሕግ እንዲያቀርብ በሰከነ ሁኔታ እንዲያግዝ አበክረን እንጠይቃለን።

ኃይማኖታችን አንዱ ባጠፋው ሌላውን የሚቀጣና እርምጃ የሚወስድ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ባለመሆኑ ሁላችንም ሙስሊሞች እንድንረጋጋ በአሏህ ስም እንጠይቃለን።

በጎንደር በአክራሪዎች ሕይወታቸው ለተቀጠፉ ሙስሊም ወንድሞቻችን አሏህ(ሱ.ወ) ማረፊያቸውን ጀነተልፊርዶውስ እንዲሰጣቸው እንለምነዋለን። አሏህ ሆይ! ማራቸው፤ ማረን

ሠላም፣ ፍቅር ፣ አንድነት ...ለሁላችንም!
3.3K views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 22:06:20
አቃጠሉት!

#update ጎንደር
~ እስካሁን በተገኘው መረጃ፣ አስራ-አንድ(11) ሠዎች ለህልፈት በቅተዋል።
~ አሁንም ድረስ ወደ ሆስፒታል እየገቡ ያልሉ ቁስለኞች መኖራቸው ታውቋል።
~ የተኩስ ድምፅ ረግቧል። የቃጠሎ ምልክቶች አሁንም ድረስ ይታያሉ።

~ አንድ ሚኒስተር፣ በቅርበት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛል።
~ የፀጥታ አካላት መሀል-ከተማ እና መስመር(መንገድ) አካባቢ በውስንነት ተሰማርተዋል።
~ ነጃሺ መስጅድ አካባቢ፣ ክርስቲያን ወጣቶች የማረጋጋት ሥራ እየሰሩ መሆኑ ተሰምቷል።
~ ገብርኤል መስጅድ ለከፍተኛ ቃጠሎ ተቃጥቷል።
~ አሁን ከመሼ ሠዎች እየተገደሉ መሆኑም ተነግሯል(ቀበሌ 06 አካባቢ/ቅዳሜገበያ አካባቢ)።
~ ሁሉም እንቅስቃሴ ተገትቷል።
....
Kedir taju

#Stop_Muslim_Genocide_in_Gondar
3.4K viewsedited  19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 22:00:42
ጎንደር ፒያሳ የሚገኘው እርግብ በር መስጅድ
||

ፍትሕ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ታፍነው የሽብር ጥቃት እየተፈጸመባቸው ለሚገኙት የጎንደር ሙስሊሞች


ሀገር አጥፊ የአክራሪዎች ትሩፋት!
እኛ ስናውቀው፣ አባ-ሼህ ከማል የክርስቲያኑም አባት ነበሩ። እርሳቸውን <አናስቀብርም> ያሉ አክራሪ ክርስቲያኖች ግና - ከሀጅ ኢልያስ መካነ-ቀብር ድረስ ተሰልፈው አይናችን እያየ በድንጋይ ጀምረው፣ ቦምብ ወረወሩ። መትረየስ ተኮሱ። የተደራጁ ሀይሎች መሣሪያ ታጥቀው ቀባሪውን ወገን ማጥቃት ጀመሩ። ከ10 ሠዎች በላይ ተመትተዋል። የሞቱም አልሉ። መስጅዶች እየተደበደቡ ነው። የሙስሊሞች ቤት፣ ሱቅ፣ ተንቀሳቃሽ መኪና በአሰሳ እና በጥናት እየተጠቁ ነው። ከተማው መንግሥት ያለው አይመስልም። በፍፁም ሀላፊነታቸውን እየተወጡ አይደሉም! የተቋማት አመራሮችን እንኳን ለማግኘት አልፈቀዱም። የሆነው ይኸው ነው። ስለሚሆነው ደግሞ እንመክራለን። ኢንሻአላህ ፅንፈኛን ሁሉ እንቃወማለን! በቆምንበት ለማለፍ አናመነታም!!!
Kedir taju

https://t.me/IslamisUniverstiy_public_group
4.0K viewsedited  19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 22:24:05 አለማችን ላይ ካሉ ቢሊየነሮች መካከል አንዱ አንድቀን በሚዲያ ቀርቦ ጋዜጠኛዋ "እስኪ ስለስኬትህ ምንጭ ንገረን" ትለዋለች። ቢሊየነሩም ከኪሱ ባዶ ቼክ አውጥቶ ቀን ፅፎ ይፈርምና የምትፈልጊውን የገንዘብ መጠን ፃፊ ይላታል። ጋዜጠኛዋ ኮስተር ብላ "እኔ ስራ አለኝ ደሞዝ አለኝ ጥሩ ኑሮ አለኝ። ልለምን አይደለም ብላ ቼኩን ትመልስለታለች። እሱም "የስኬቴን ምንጭ አይደል የጠየቅሽኝ" አላት። አዎ አለች። ባለሀብቱም "አየሽ እኔ ያገኘሁትን እድልና አጋጣሚ ሁሉ ሀላል እስከሆነ ድረስ አላባክንም እጠቀማለሁ አንቺ ቼኩን ተቀብለሽ ቢሊየን ፅፈሽ ቢሆን ከቢሊየነሮች አንዷ ትሆኚ ነበር አላት

ረመዳን የለውጥ ቼክ ነው። ለምሳሌ ሱና የፈርድ ያህል ይመዘገብልሀል። ፈርዱ ደግሞ በሰባ ይባዛልሀል። ስለዚህ ህይወትህ ላይ የምትፈልገውን ፅፈህ የመለወጥ እድሉን ፈጣሪ ሰቶሀል።

ፈጣሪ ዱአቸውን ከወደደላቸው ከተቀበላቸው ያድርገን ...ፁመዉ ተራቡት ከተባሉ ሚስኪን ባርያዎቹ ሳይሆን ለፆመኞች ለብቻ ለተዘጋጀዉ የጀነት በር የምንገባ ያድርገን
...ሴቱንም በረመዷን የምግብ ሙያ መለማማጃ ከማያደርጉት ያርጋችሁ

ወደ ከፍታ፣ ወደ ለውጥ ጎዳና፣ ወደ ክቡር ሰብዓዊነት፣ ወደ በረካ፣ ወደ እዝነት፣ ወደ ነፍስን መግርያ፣ ወደ እርቅ ማዕድ፣ ወደ ሰላም፣ ወደ ስክነት፣ ወደ አብሮነት፣ ወደ ተወዳጁና ተናፋቂው፣ የኸይር ወር ወደ ሆነው፣ የማይጠገበው ውድ የሆነው የረመዳን ፆም በአላህ ፍቃድ እንኳን አደረሰን።
መልካም ስራቸው ከሚበዛላቸው፣ ጊዜያቸውን ከሚጠቀሙት፣ በኸይር ከሚያሳልፉት፣ ለወንጀላቸው መሀርታን ከሚያገኙት፣ በጀነት ከሚበሰሩት ሰዎች መሀል አላህ እንዲያደርገን ዱዓዬ ነው።




ረመዳን ሙባረክ!!!


https://t.me/IslamisUniverstiy_public_group
8.6K viewsedited  19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-20 04:28:01 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ
ዉድና የተከበራችሁ የቻናል ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ ፡፡


በአስተያየት መስጫ ምነዉ ጠፋህ በሰላም ነዉ.. መቼ ነዉ ፁሁፍ ማቅረብ የምጀምረዉ የሚል በተያለያዩ ቀናቶች በብዙ የቻናል ቤተሰቦች አስተያየት እያየሁ ነዉ፡፡የተለያዩ ፁሁፎች ማቅረብ ስላቆምኩ ብዙ ተከታታዮች ከቻናል Leave እያሉ እንደሆነም ነግረዉኛል፡፡

ምንም ማድረግ አልችልም ከጁንታዉ ጊዜ ቡሀላ ብዙ ነገሮች ተቀያይረዋል፡፡ ያን የጁንታ ጊዜ ደሴ ከተማ ላይ ስናሳልፍ የአስተሳሰብ ቢዥታ ፈጥሮብኝ አልፏል....

#ለምሳሌ በፊት ያነበብኳቸዉ መፅሀፎች ሳይቀር ከአእምሮየ 99% ተሰርዟል...የጁንታዉ ዘመን የተፈጠረብን ስነ ልቦና የጦርነትን ሁኔታ የከባድ መሳሪያ የድሮን ድምፅ ..የጁንታዉ በወገኖች የሚያደርጉት ስቃይ ዘረፋ የሴቶች እንግልት የመኖር ዋስትና ሳይኖረን ለመሞት ተዘጋጅተን ስለተረፍን ጦርነት ምን አይነት እንደሆነ ያላዩት ጋር በጭራሽ መግባባት አንችልም


ወደ በፊቱ አቋሜ ለመመለስ በጣጣጣም ከባድ ነዉ፡፡ የጁንታዉን ዘመን ያየና ያላየ በጭራሽ በሀሳብ ለራሱ መግባባት አንችልም....እንደበፊቱ ፁሁፍ እዉነተኛ ታሪክ አዘጋጅቼ ለእናንተ ማቅረብ የማልችልበት አቋም ላይ ነዉ ያለሁት...

እንደበፊቱ ለሌላ ሰዉ መትረፍ አልችልም ለኔም ስነልቦና ሀኪም ያስፈልገኛል

የሚሻለዉ መፍትሄ አንድና አንድ ብቻ ነዉ ይሄ ቻናል Admin ቢኖሩም ግን የሚመጥን ፁሁፍ ብዙዎች ማቅረብ አልቻሉም ፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ተከታታይ ከቻናል እየተሰናበቱ ነዉ፡፡
የፁሁፍ ሙያ ያለዉ ያናግረኝና ሙሉ በሙሉ ቻናሉን ለመስጠት ወስኛለሁ እኔ ፁሁፍ አዘጋጅቶ እንደበፊቱ ለማስተማር አይሆንልኝም ብቻ ዱአ አርጉልኝ ፡፡ በፊት በተለያዩ ሀሳብ አጋጣሚዎች ያስቀየሞኳችሁ ካላችሁ አዉፍ በሉኝ
አሚር ሰይድ


ለአስተያየት እና ቻናሉን ፁሁፍ አዘጋጅቼ ማስተማር እችላለሁ የሚል ካለ በዚህ bot ያናግረኝ
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

5 views01:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ