Get Mystery Box with random crypto!

ISLAMIC SCHOOL

የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL I
የቴሌግራም ቻናል አርማ islam_and_science — ISLAMIC SCHOOL
የሰርጥ አድራሻ: @islam_and_science
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 15.55K
የሰርጥ መግለጫ

✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 20

2021-10-20 19:58:21 አንጀት የሚበላ ክስተት

ትናንት ማክሰኞ አንድ ተፈናቃይ ኮምቦልቻ ታሞ ወደ ደሴ ሪፈር ተብሎ ሲመጣ ሞተ ...ጀናዛዉ መስጊድ አደረ አንድ ልጅ ብቻ ሲያለቅስ አደረ ዛሬ ተቀበረ

መፈናቀል መዉጣት ቀላል ነዉ መልሶ የኖረበት ከተማ ለመግባት ግን ከባድ ነዉ፡፡

የደሴ ከተማ የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ሀይቅ ደርሰዋል የሚባለዉ ወሸት ነዉ የኛዉ ወገን ቀይ ለባሽ ኮማንዶ ናቸዉ ፡፡ ሙስሊም ማመን ያለበት ይሄን ጦርነት ህዉሀት ሳይሆን ያመጣዉ አሏህ ነዉ ለህወል መህፉዝ ላይ የተፃፈን መቀየር አይቻልም ብቻ ዱአ ማድረግና ሰበቡን ማድረስ ነዉ፡፡

በመፈናቀል በመፍራት በመሸሽ የሚሆን ነገር የለም ማንም ሰዉ ከሞት አያመልጥምና፡፡


መቼም በየሰፈሩ የሚተኛ ወጣት የለም እንደተለመደዉ ሁሉም ነቅቶ ሰፈሩን ይጠብቅ

በአስተያየት መስጫ ለጠየቃችሁኝ ደሴ ሰላም ናት ወይ ? ላላችሁ

ሰላሟ እዉስጧ በተሰገሰገ ጁንታ በዉሸት ዜና ነዋሪዉን እያሸበሩ ነዉ እንጂ ሰላም ነን...ግን ወላሂ በጣም ዱአ ያስፈልጋል በዱአ እገዙን
6.5K viewsedited  16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-19 07:52:11 ደሴ መግባት እንደ ኪሮስ አለማየህ ዘፈን እንደመሽከርከር ቀላል አይደለም

ትናንት ሰኞ ጁንታዉ ዉጫሌን ተቆጣጠርኩ ሀይቅን ተቆጣጥሬ ደሴ ከተማና ኮምቦልቻ እገባለሁ ብሎ በተጨማሪ የሚዲያ ግብራበሮቹ ደሴ ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ሆነች እያሉ ሲያናፍሱ ...የደሴ ከተማ ነዋሪ ግን በዉሸት ወሬ ከተማየን ሸሽቼ የትም አልሄድም ብሎ የደሴ ልጆች ከተማቸዉን ጠብቀዋል፡፡

ግን በፊትም ስነፈራዉ የነበረዉ ያበላቸዉን ጣት ነካሽ የሆኑ ገና ጦርነቱ ሳይጀመር ወልደያን መርሳን ዘርፈዉ የመጡ እናት አባቱን ሚስቱን እህቱን ጥሎ ፈርጥጦ የመጣ እዚህ መጥተዉ የተፈናቃይን እርዳታ እየተቀበሉ እየሸጡ የሚቅሙ የሚያጨሱ ከጁንታዉ ለይተን የማናያቸዉ ዱርየ ወጣት ተፈናቃዮች የደሴ ከተማ ነጋዴን ንብረት ለመዝረፍ ሙከራ አድረገዉ ሀገር ወዳዱ የሚኖርበትን ከተማ ወዳዱ የደሴ ልጅ ከነዚህ የተደራጁ ሌቦች አንድ ላይ ሁኖ ይሄን የተደራጀ ሌባ እፍ አመድ ያለዛሬም አይለመድ አድርጎ አደብ አሲዟቸዋል፡፡

ግን አንዳንድ ሰዎች የደሴ መያዝ አደጋ እንዳለዉ ለመንግስት እንደሚያሰጋ አልተረዱትም...የኢትዮ ህዝብ 90% በላይ ያለዉ የአገሩን ታሪክ አያቅም ለዛ ይሆናል ትኩረት ያልሰጠዉ ...ደሴ ከተማ የፓለቲካ ቁልፍ ናት የበፊት አፄዎቹና የቅርቦቹ የሀገር መሪዎች ደሴ ከተማ የነቃ ማህበረሰብ ያለበት ስለሆነ ደሴን ያሳመነ አሸናፊ እንደሆነ ያቁታል....ከበፊት ጀምሮ ሁሉም መንግስቶች ደሴን መጀመሪያ በእጃቸዉ ማድረግ ይፈልጋሉ

ጁንታዉ ገና ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ደሴን በቅርቡ እያዛለሁ እያለ ሲፎክር ነበር ደሴን ከያዘ አዲስ አበባን ለመያዝ ቀላል እንደሆነ ስለሚያቁ ነዉ..ግን ደሴ ለምን የትግራይ ሰራዊት ኢላማዉ አደረገ??
☞ደሴ ከአዲስ አበባ ከተማ ቀጥሎ ከኢትዮጲያ ሁለተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ያለበት ከተማ ነዉ
☞ደሴ ከተማ ከኢትዮጲያ ሁለተኛ ደረጃ ግብር የሚሰበሰብበት ከተማ ነዉ
☞የደሴ ከተማ ህዝብ 90% በላይ ራሱን በራሱ የሚያስተዳድር ነጋዴ የሚኖርበት ከተማ ነዉ
☞ደሴ ከተማ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ብዙ ነዋሪ የያዘች ከተማ ነች፡፡ ደግሞ በሰሞኑ ችግር ከ600,000 በላይ ተፈናቃይ አቅፋ የያዘች ከተማ ነች
☞ደሴ የነጋዴ ከተማ ስለሆነ ብዙ የሚዘረፍ የሚወደም ነበር አለ ይሄ ደግሞ ኢኮኖሚዉ ሊሽመደመድ ይችላል
☞ደሴ ከተማ እምብርት ነች አራት መግቢያና ከሁሉም ከተማ የመጣ መሿለኪያ ነች


እናም ደሴ ከተማ ተያዘ ማለት ኢትዮጲያ የመኖር ያለመኖር ህልዉና ነዉ፡፡የኢትዮጲያ ህዝብ ሌላዉ ቢቀር በዱአ ሊያግዝ ይገባል፡፡

ዛሬ አዳር የከባድ መሳሪያ ድምፅ ደሴ ከተማ ሲሰማ አድሯል ..የወገን ጦር መሆኑን እንወቅ ..ወያኔ ደሴን እንዳይዝ ከባድ መሳሪያ ሊተኮስ ስለሚችል ያለን አማራጭ የከባድ መሳሪያ ድምፁን መለማመድ ነዉ፡፡ ሁላችንም ከተማችንን እንጠብቅ ሸሽተን አስጠጉን ብለን የምንሄድበት ከተማ የለንም

አሁንም የሚያሳስበን የሚቅሙ የሚያጨሱ የሚጠጡ በተፈናቃይ ስም የሚረዱ እናት አባቱን እህቱን ሚስቱን ጥሎ የመጣ ወያላ ከጁንታዉ ለይተን ስለማናያቸዉ ሁሉም እነዚህን አላማ ቢስ ወጣቶች መከታተል መቻል አለብን...በዚህ ቀን አናስወጣቸዉ ሰዉ ናቸዉ ወደዬት ይወጣሉ እነሱን በመደራጀት በመጠበቅ ከተማችንን እናድናለን

ኢንሻ አላህ ኢትዮጲያ ወሎ ደሴ እናሸንፋለን
6.4K views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-19 07:47:27
ደሴ መግባት እንደ ኪሮስ አለማየህ ዘፈን እንደመሽከርከር ቀላል አይደለም

ትናንት ሰኞ ጁንታዉ ዉጫሌን ተቆጣጠርኩ ሀይቅን ተቆጣጥሬ ደሴ ከተማና ኮምቦልቻ እገባለሁ ብሎ በተጨማሪ የሚዲያ ግብራበሮቹ ደሴ ከተማ በትግራይ ሰራዊት እጅ ሆነች እያሉ ሲያናፍሱ ...የደሴ ከተማ ነዋሪ ግን በዉሸት ወሬ ከተማየን ሸሽቼ የትም አልሄድም ብሎ የደሴ ልጆች ከተማቸዉን ጠብቀዋል፡፡

ግን በፊትም ስነፈራዉ የነበረዉ ያበላቸዉን ጣት ነካሽ የሆኑ ገና ጦርነቱ ሳይጀመር ወልደያን መርሳን ዘርፈዉ የመጡ እናት አባቱን ሚስቱን እህቱን ጥሎ ፈርጥጦ የመጣ እዚህ መጥተዉ የተፈናቃይን እርዳታ እየተቀበሉ እየሸጡ የሚቅሙ የሚያጨሱ ከጁንታዉ ለይተን የማናያቸዉ ዱርየ ወጣት ተፈናቃዮች የደሴ ከተማ ነጋዴን ንብረት ለመዝረፍ ሙከራ አድረገዉ ሀገር ወዳዱ የሚኖርበትን ከተማ ወዳዱ የደሴ ልጅ ከነዚህ የተደራጁ ሌቦች አንድ ላይ ሁኖ ይሄን የተደራጀ ሌባ እፍ አመድ ያለዛሬም አይለመድ አድርጎ አደብ አሲዟቸዋል፡፡

ግን አንዳንድ ሰዎች የደሴ መያዝ አደጋ እንዳለዉ ለመንግስት እንደሚያሰጋ አልተረዱትም...የኢትዮ ህዝብ 90% በላይ ያለዉ የአገሩን ታሪክ አያቅም ለዛ ይሆናል ትኩረት ያልሰጠዉ ...ደሴ ከተማ የፓለቲካ ቁልፍ ናት የበፊት አፄዎቹና የቅርቦቹ የሀገር መሪዎች ደሴ ከተማ የነቃ ማህበረሰብ ያለበት ስለሆነ ደሴን ያሳመነ አሸናፊ እንደሆነ ያቁታል....ከበፊት ጀምሮ ሁሉም መንግስቶች ደሴን መጀመሪያ በእጃቸዉ ማድረግ ይፈልጋሉ

ጁንታዉ ገና ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ደሴን በቅርቡ እያዛለሁ እያለ ሲፎክር ነበር ደሴን ከያዘ አዲስ አበባን ለመያዝ ቀላል እንደሆነ ስለሚያቁ ነዉ..ግን ደሴ ለምን የትግራይ ሰራዊት ኢላማዉ አደረገ?? ሙሉዉን ያንብቡ
10.1K viewsedited  04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-18 14:20:03 ምንድን ነዉ ነገሩ??

አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ የተከበራችሁ የተወደዳችሁ ያቻናል ቤተቦች እንዴት ናችሁ??

ከ600,000 በላይ ተፈናቃይ እንደ ሀገራቸዉ ሳይከፋቸዉ የያዘችዉ ከተማ እናት አለም ደሴ ይሄዉ የተፈራዉ የመጣ ይመስላል፡፡ የደሴ ከተማ ነዋሪ እዉነተኛ ይሁን ሀሰተኛ መረጃ በመያዝ በከተማዉ ጭር የማለት ..አልፎ አልፎም ግሮግር ይስተዋላል...የመንግስት ነገር ምንም ሊገባን አልቻለም
ወሎ ...
ወሎ ዘር ብሄር የማይመለከት የሰዉ ልጅ ብቻ ሁነህ ስትሄድ ስቆ የሚቀበልህ ይሄዉ ሰዉ መሆንን ያለማመዱ ወሎየዎች ይሄን ያህል ግፍ ቀማሽ በየአካባቢዉ ተፈናቃይ..የሚያለቅሱ፣ የሚራቡ፣ በጦርነት የሚሰቃዩ፣መቼ ይሆን የምሞተዉ እያልን ቀን ጠባቂ ሁነናል

ወሎየ በግድ አማራ ሁኑ ተብለን ሆን የአማራ ክልል መንግስት ጀርባዉን አዞረብን ..የአማራ ክልል ታዋቂ ከተሞች በሰላም እየኖሩ የወሎ ህዝብ ተፈናቃይ ሆነ.....
የፌደራል መንግስት አብይ አህመድ እንደ ወሎ ህዝብ አጨብጭቦ መርቆ ዱአ አርጎ ነበር የተቀበለዉ..ግን ከእሱ ሳይሆን ከአመራሩ ችግር ይሁን ባይታወቅም በወሎ ሰዉ አብይ ምን አረግንህ እያሉ አልቃሹ በዝቷል

ግን የወሎ ሰዉ ጥፋቱ ምን ይሆን???
ለማንኛዉ ሙስሊም የሌላም ሀይማኖት ተከታዮች በዱአ እና በፆለት አሳታዉስን...የወሎ ሰዉ ቀኙም ግራም ገብቶት የሚሆነዉ አጥቷል...

ገና ጁንታዉ ሳይመጣ የነጋዴዉን ሱቅ ለመዝረፍ ስራ አጥ ጁንታ አሰፍስፎ ተቀምጧል፡፡


የኢትዮጲያ ህዝብ ሆይ!!!
ደሴና ኮምቦልቻ ብዙ ተፈናቃይ ያለበት ከተማ ነዉ
...ደሴ የወሎ እምብርትና ብዙ ተፈናቃይ የያዝን ነን ወደ የት እንሸሻለን እየታያዩ ማለቅ ካልሆነ በቀር
መንግስት እነዚህን ከተማ እንዳያሲዝ ድምፅ ሁኑን



ዉድ የቻናል ቤተሰቦች አሁን ላይ ወሎ ላይ ሁኖ መኖር መሞቴ አይታወቅምና እስከ ዛሬ ያስቀየምካችሁ ያስከፋሆችሁ ካለ ለአላህ ብላችሁ አዉፍ በሉኝ .....ከአሁን ቡሀላ ወሎ ሆኑ ተስፋ የለም...በዱአም እገዙን

ነገር ከጠና network ሊዘጋ ስለሚችል አደራ ወሎየዎችን እንዳረሱን ድምፅ ሁኑን

ባይሆን ድምፅ የምትሆኑን ለመንግስት ሳይሆን ለፈጣሪ ነዉ.... ለአላህ ንገሩልን ችግራችንን አስረዱልን ይሄን በላዕ ይብቃችሁ ብላችሁ ዱአ አርጉልን

አሚር ሰይድ
6.7K viewsedited  11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-13 21:53:57 ዉድና የተከበራችሁ የቻናል ቤተሰቦች


ዛሬ አንደኛ የወጣችዉ የ50 ብር ካርድ ተሸላሚ

ከ10/10 በማምጣት
ሀያት ሙራድ ከአዳማ ሲሆን

ሁለተኛ ደግሞ 8/10 በማምጣት☞ ኢክራም ከጂማ የ25 ብር ካርድ

ሶስተኛ ደግሞ የወጣችዉ☞ መርየም ከማል ከአዲስ አበባ 8/10 በማምጣት የ15 ብር ካርድ ተልኮላታል


መልሰ

/ የጀነት በራፍ 8 ናቸው፦ እነሱም

1. ባቡ ሰላህ:- ሰላትን አዘውትረው ለሚስግዱ ሚገቡበት በር
2. ባቡ ጂሀድ:- ጂሀድ ለሚወጡ ሰዎች ሚገቡበት በር
3. ባቡ ሰደቃህ:- ሰደቃህ ለሚያወጡ ሰዎች ሚገቡበት በር
4. ባቡ ረያን:- የፆመኞች በር
5.ባቡ ሀጅ:- በየአመቱ ሀጅ ለሚያደርጉ ሰዎች
6.ባቡ ቃዲሚን:- ለታጋሾች እና ይቅርታ አድራጊዎች
7.ባቡ ኢማን:- ለደግ ሰዎች እና እምነታቸውን በደግነት ለሚጠብቁ
8.ባቡ ዚክር:- አላህን በብዛት ለሚያወሱ


/የጀሀነም በራፍ 7 ናቸው፦እነሱም

1.ጀሂም:- በአላህ እና በመልክተኛው አምነው ትእዛዝ ያልጠበቁ ሰዎች ሚገቡበት በር ነው
2.ጀሀነም:- ትልቁ በር ሲሆን ጣኦት አምላኪ ሚገቡበት ነው
3.ሰኢር:- እሳትን ሚያመልኩ ሚገቡበት ነው
4.ሰቀር:- በአላህ የማያምኑ ሚገቡበት ነው
5.ለዛ:- ሙሳን አምላክ ነው ያሉ ሚገቡበት ነው
6.ኸዊያህ:- ኢሳን አምላክ ነው ያሉት ሚገቡበት ነው
7.ኩታማህ:- በአስከፊነቱ ከጀሀነም የላቀ ሲሆን ለአጋሪዎች ተደግሳለች


/ ለ20 ግዜ ተጠቅሷል

/ለ16 ግዜ ተጠቅሷል

/ለ17 ግዜ ተጠቅሷል

/ ለ27 ግዜ ተጠቅሷል

/ ለ7 ግዜ ተጠቅሷል

/ ለ5 ግዚ ተጠቅሷል

𝕤𝕦𝕣𝕒𝕥𝕦𝕝_𝕙𝕦𝕕 ¶ 11፣23!

/ 𝕤𝕦𝕣𝕒𝕥𝕦 𝕒𝕟-𝕟𝕒𝕞𝕝 § 27፣50!

𝕓𝕠𝕟𝕖𝕤......


~የነቢያቶች ሀገር

1.. አደም (ዐ.ሰ) = ስሪላንካ (Sirilanka)
2.. ኑህ (ዐ.ሰ) = ጆርዳን (Jordan)
3.. ሹዓይብ (ዐ.ሰ) = ሶሪያ (Soria)
4.. ኢብራሂም (ዐ.ሰ) = ፍልስጤም (Palistain)
5.. ኢስማኤል (ዐ.ሰ) = ሳኡዲ (Saudi)
6.. ያእቆብ (ዐ.ሰ) = ፍልስጤም (Palistain)
7.. ያህያ (ዐ.ሰ) = ፍልስጤም (Palistain)
8.. ዘከሪያ (ዐ.ሰ) = ፍልስጤም (Palistain)
9.. ኢስሃቅ (ዐ.ሰ) = ፍልስጤም (Palistain)
10.. የሱፍ (ዐ.ሰ) = ፍልስጤም (Palistain)
11.. ሉጥ (ዐ.ሰ) = ኢራቅ (Iraq)
12.. ኢዩብ (ዐ.ሰ) = ጆርዳን (Jordan)
13.. ሁድ (ዐ.ሰ) = የመን (Yemen)
14.. ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) = ሳኡዲ (Saudi) ( ከሁሉም በተለየ መልኩ የተላኩት ለአለም ህዝቦች ነው )
15.. ሙሳ (ዐ.ሰ) = ግብፅ (Egypt)
16.. ሀሩን(ዐ.ሰ) = ግብፅ (Egypt)
17.. ሷሊህ (ዐ.ሰ) = የመን (Yemen)
18.. ሱለይማን (ዐ.ሰ) = ግብፅ (Egypt)
19.. ኢሊያስ (ዐ.ሰ) = ጀሩሳሌም (ፍልስጤም)
20.. ዳውድ (ዐ.ሰ) = ኢራን (Iran)
21.. ኢሳ (ዐ.ሰ) = ጀሩሳሌም (ፍልስጤም)
22.. ኢድሪስ (ዐ.ሰ) = ኦማን (Oman)
23.. ዩኑስ (ዐ.ሰ) = ኢራን (Iran)
24.. ዙልኪፍል (ዐ.ሰ) = ጆርዳን ( Jordan )
25.. አልየስእ (ዐ.ሰ) = ሶሪያ ( Soria)

የአሏህ እዝነት እና ሰላም በሁሉም ላይ ይስፈን!


በሚቀጥለዉ እሮብ ለስድስተኛዉ ዙር እንገናኝ ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ
6.5K viewsedited  18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-13 20:10:31

አስላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ!

እንዴት ናችሁ ዛሬ የአምስተኛዉ ዙር ጥያቄና መልስ ዉድድር ተጀምሯል

ዛሬ ሶስት ሰዉ ይሸለማል
☞በፍጥነት አንደኛ የመለሰ የ50 ብር ካርድ
☞ ሁለተኛ የወጣ የ25 ብር ካርድ
☞ ሶስተኛ ለወጣ የ15 ብር ካርድ ተዘጋጅቷል፡፡
ተስፋ ሳቆርጡ ተሳተፉ አንደኛ ሁሉንም መመለስ ቢያቅት የተወሰነዉን መልሶ ካርዱን ያሸንፉ፡፡


የጥያቄና መልስ ዉድድራችን አሁን ጀምሯል ዉድድሩ የሚያልቅበት ሰአት 3:30 መሆኑን እንዳትዘንጉ፡፡ በተጨማሪ ስም ከምትኖሩበት ከተማ አትዘንጉ፡፡

መልሳችሁንም በተከታታይ መላክ ከዉድድር ዉጭ ያደርጋል
ስማችሁን የምትኖሩበትን ከተማ መልሱን በአንድ ላይ ትልካላችሁ መልካም ዉድድር



የጀነት በራፍ ስንት ናቸው ከነ ስማቸው እና ማብራሪያው

የጀሀነም በራፍ ስንት ናቸው ከነ ስማቸው እና ማብራሪያ

ሀሩን(ዐለይሂ ሰላም)፡- በቁርኣን ውስጥ ስንት ጊዜ ተጠቅሷል፡

ዳዉድ(ዐለይሂ ሰላም)፡- በቁርአን ውሰጥ ስንት ጊዜ ተጠቅሷል

ሱለይማን(ዐለይሂ ሰላም)፡- በቁርኣን ውስጥ ስንት ጊዜ ተጠቅሷል፡፡


ዩሱፍ(ዐለይሂ ሰላም)፡- በቁርኣን ውስጥ ስንት ጊዜ ተጠቅሷል፡፡

ዘከሪያ(ዐለይሂ ሰላም)፡- በቁርኣን ውስጥ ስንት ጊዜ ተጠቅሷል

የሕያ(ዐለይሂ ሰላም)፡- በቁርአን ውሰጥ ስንት ግዜ ተጠቅሷል

እነዚያ ያመኑትና በጎ ሥራዎችን የሠሩት ወደ ጌታቸውም የተዋረዱት እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፡፡ እነሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
የትኛው ሱራ ውሰጥ ይገኛል ከነ አንቀጱ

ተንኮልንም መከሩ፡፡ እነርሱም የማያወቁ ሲኾኑ በተንኮላቸው አጠፋናቸው፡፡ የትኛው ሱራ ውሰጥ ይገኛል ከነ አንቀጱ

BONES.......


የ25ቱ ነብያቶች ሀገር ፃፉ የዚህ መልስ ነው ትልቅ ነጥብ ያለው

መልሱን በዚህ bot አሁኑኑ ይላኩ
t.me/Meh_Ani_bot t.me/Meh_Ani_bot
t.me/Meh_Ani_bot t.me/Meh_Ani_bot
5.3K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-13 09:47:11 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካተሁ
እንዴት ናችሁ፡፡ ዛሬ ከምሽቱ 2:15 ላይ ኛዉ ዙር የጥያቄና መልስ ዉድድር ይኖረናል፡፡

ቀድሞ ለመለሰ የ50 ብር የሞባይል ካርድ
➋ኛ የወጣ የ25 ብር ካርድ
➌ኛ የወጣ የ 15 ብር ካርድ ሽልማት ተዘጋጅቷል


ለመወዳደር ዝግጁ ናችሁ??



መስማማታችሁንና ለመወዳደር ማታ 2:15 ለመግባት ሀሳብ ያላችሁ Like በማድረግ ይግለፁ

መልካም እድል
4.3K views06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-11 19:45:44 ╔═══════════════╗
ማጄላንና ታላቁ ሙጃሂድ ላቡ ላቡ
╚═══════════════╝

ልጅ ሳለን ስለማጄላን ጥሩ ጥሩው ተነግሮናል። በየትምህርት ቤታችን አስተማሪዎቻችን ስለእርሱ መልካም መልካሙን አውግተውናል። ዓለምን የዞረ የጂኦግራፊ ሊቅ ተብሎ የሚወሳው ማጄላን ማን ነው? እውነተኛ ታሪኩን ላውጋችሁ።
ሙስሊሞች የፊሊፒንን ደሴቶች ማሃራጅ ብለው ይጠሯቸዋል። ከቻይና እና ከሱማትራ በመጡ ነጋዴዎችና ዳዒዎች እስልምና በአካባቢው ተስፋፍቷል። ለ“ማኒላ” ድንበር ነዋሪዎች በሙስሊም ነጋዴዎች አማካኝነት የኢስላም ጥሪ ደርሷቸዋል። የእስልምና ብርሃን ከ7000 በላይ ነዋሪዎች ዘንድም ፈንጥቋል። ይህ የእግር እሳት የሆነበት ማጄላን ሙስሊሞች እንዳይስፋፉ እስልምናን ማምከን ይቻለው ዘንድ ከፖርቹጋል ተነስቶ ምስራቅ አፍሪካን እስከ ህንድ አዳርሶ ሙስሊሞችን በገፍ ብትሩ ቀጥቷል።
ሙስሊሞችን በእጅጉ ይጠላል። በ1502 ለሐጅ ጉዞ 700 ሙስሊሞችን ጭኖ የሚጓዝ መርከብን አገተ። መንገደኞቹ ወዴት እንደሚሄዱም ጠየቀ። የአላህን ቤት ለመጎብኘት ወደ መካ እየተጓዙ መሆኑ ሲነገረው ለግብረ አበር ወታደሮቹ ትዕዛዝን አስተላለፈ። ንብረታቸውን ከተዘረፉ በኋላ በመርከቡ ላይ ሰብስበው ከነህይወታቸው አቃጠሏቸው። በዘመታቸው የመስቀል ጦርነቶች ከ300 በላይ መስጂዶችን አፍርሷል።
ሙስሊሞችን ማርኮ አፍንጫቸውንና ጆሮዎቻቸውን ቆራርጧል። ጥርሶቻቸውን እየሰበረ በድዳቸው አስቀርቷቸዋል። እጅና እግራቸው ተጠፍሮ በክፍል ውስጥ ታጭቀው ከነህይወታቸው በእሳት ነደዋል።
ማጄላን የምድር አሳሽ አለምን የዞረ ጆግራፊስት መሆኑን አስተምረውናል። ግና ለሙስሊሞች የነበረውን ጥላቻ ያደረሰባቸውን ግፍና መከራ አልነገሩንም።
እ.ኤ.አ. በ1521 በ“ፈርዲናንድ ማጂላን” የሚመራው የስፔን ጦር ፊሊፒን ደረሰ። የጎረቤት ደሴቶች በስፔን አክሊል ሥር እንዲተዳደሩና ክርስትናን የበላይ ለማድረግ በሚል ስምምነት ላይ ተደረሰ። አመጣጡም የእስልምናን መስፋፋት ለመግታትና ሙስሊሞችን አይቅጡ ቅጣት ለመቅጣት የታሰበበት ነበር።
በመስቀል ዘመቻው “ማክታን” የተሰኘች አንዲት ትንሽዬ ደሴትን ለመቆጣጠር ጉዞ ጀመረ። በወቅቱ ደሴቷ “ላቡ ላቡ” በሚባል ሙስሊም ሡልጣን ትተዳደር ነበር። በማጄላን የሚመሩት የስፔን ወታደሮች ከደሴቷ ጠረፍ መሽገው ከነዋሪዎቿ ምግብ እየነጠቁና ሐብት ንብረታቸውን እየዘረፉ ሲያስቸግሩ ሕዝቡ ተቃውሞውን አሰማ። ላቡ ላቡ እጅግ ጠንካራ ሙጃሂድ ነበርና ለማጄላን ወረራ እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማጄላን የአጎራባች ደሴት ነዋሪዎችን አነሳሳበት። ጥንካሬውን እና ዘመናዊ መሣሪያዎቹን ለማሳየት እድሉን ስላገኘ ደብዳቤ አስይዞ ወደ ላቡ ላቡ መልዕክተኛን ላከ።
"ከማጄላን ለማክታን ደሴት ገዢ ላቡ ላቡ በእየሱስ ስም እጀምራለሁ እኛ የነጭ ዘሮች የስልጣኔ ቀዳሚዎች ይህንን ሀገር የመግዛት ስልጣን ከእናንተ የበለጠ ይገባናልና ስልጣንህን አስረክብ"
ላቡ ላቡ ደብዳቤውን አንብቦ እንዳበቃ በግልባጩ አጭር ምላሽን ፅፎ ሰደደ "ኃይማኖት የአላህ ነው። የምናመልከው አምላክ ቀለማቸው ምንም ይሁን ምን የሰው ልጆች ሁሉ አምላክ ነው" ሲል መለሰ።
በዕለቱ ፀሐይ በሰማይ መሃል አናት ላይ ነበረች። የማጄላን መርከቦች በፊሊፒን ከሚገኙት የሙስሊም ደሴቶች በአንዱ ላቡ ላቡ በሚያስተዳድረው የማክታን ደሴት ዳርቻ እየተቃረቡ ነው። ዓመቱ 1521 ነው። ፊሊፒናዊያን በወጣት መሪያቸው “ላቡ ላቡ” መሪነት ተሰብስበው ለጂሃድ ተዘጋጅተዋል። ትናንሽ ጀልባዎች ላይ አድፍጠው የወቅቱን ዘመናዊ መሳርያ ታጥቀዋል። የራስ ቁር በአናታቸው አጥልቀው ሰይፍና ጋሻን ይዘዋል። በተንጣለለው ደሴት ላይ ከቀርከሃ በተሠሩ ቀስቶችንና አጫጭር ሰይፎችን ሸክፈዋል። የማጄላን ወታደሮች ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሲጠጉ ካደፈጡት ሙጃሂዶች ጥቃት ተሰነዘረባቸው። ሁለቱ ጭፍሮች ተገናኙ። የማጄላን ወታደሮች እንደለመዱት የሙስሊሞች አንገት ከራሳቸው ሊያበሩ ተዘጋጁ። በሹል ሰይፎቻቸው ሰውነቶችን ሊቀዳድዱ ቋመጡ። ግና ስላደፈጡት ሙጃሂዶችና ስለቀርከሃ ቀስቶች መረጃው አልነበራቸውም። የራስ ቁር እና ጋሻ ይዘው ያፌዙባቸው ጀመር። ጎራዴ ከጎራዴ ጋር ተፋጨ። ​ በ“ላቡ ላቡ” እና “ማጄላን” መካከል እጅግ ጠንካራ ፍልሚያ ተደረገ።
የብረት ጡሩር ደረቱ ላይ ያጠለቀው ማጄላን በባዶ ራቁቱ በሚዋጋው ሙጃሂድ በላቡ ላቡ ሠይፍ ተመቶ ወደቀ። ጉዳቱ ለሞት የሚዳርግ አልነበረም። ወጣት መሪ ላቡ ላቡ ለሁለተኛ ጊዜ የማጄላን አንገት ላይ ሰነዘረ። የማጄላን ጭንቅላት በደም ተጨማለቀ። የመሪያቸውን መገደል ያዩት ወታደሮች ከመሸሽ በቀር ሌላ አማራጭ አልነበራቸውምና አስክሬኑን ጥለው ወደ መርከባቸው መፈርጠጥ ጀመሩ።
ፊሊፒናዉ ሙስሊም ጀግና የተዋጣለት ተዋጊ ሙጃሂድ ‹ላቡ ላቡ› ማጄላን በሙስሊሞች ላይ የሰራውን ግፍና እየፈፀመ የነበረውን ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ሰምቶ በእጅጉ ተቆጥቶ ነበርና እነሆ ዛሬ እስከወዲያኛውም ወደ ቀብር ሸኘው።
ፊሊፒናውያን አሁንም ላቡ-ላቡን ብሔራዊ ጀግናቸው አድርገው ይመለከቱታል።
እንደ አለመታደል ሆኖ የእስልምና ጠላቶች የማጄላንን የሐሰት ታሪክ አስውበው ፃፉልን። እኛም በምዕራባውያን መስቀለኞች ዓይን እንድናነበው ተደረግን። በልባችን ውስጥ እንደጀግናና ተአምረኛም ይዘከር ይዟል።



═════════════════
ምንጭ:-
كتاب قبسات من نور
5.5K viewsedited  16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-08 09:16:51 መሪ የሌለዉን መኪና እየሄደ ንብረት ህይወት እንዳያጠፋ መላ እንበል የሚል መጥፋቱ አሳዛኝ ነዉ፡፡

ምን ለማለት ነዉ ቻርለስ ዳርዊን በቀጥታ ፀቡ ከአላህ ጋር በይፋ ነበር ፈጣሪ የፈጠረዉን ከዝንጅሮ ነዉ የሰዉ ልጅ የመጣዉ ብሎ አርባ አመት ያህል ታሞ አሟሟቱ አስጠልቷል....


ዛሬ ደግሞ መዉሊድ አንድ ሰዉ በጀመረዉ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ በቅብብሎሽ መጥቷል፡፡ እኛ ልጅ እንደነብርን መዉሊድ ሲከበር ዳቦዉ ሰደቃዉ ለሚስኪኖች ይደርስ ነበር...የመዉሊድ ዝግጅቱ ደግሞ ጥሩ የሚያስተምሩ ከቢድአ የፀዱ ነበሩ፡፡


ነገር ግን አሁን ላይ መሪዉ አሊም ሳይሆን ወጣት ሙነሺዶች ሁነዋል .... በመዉሊድ ስም አጂ ነብይ ሴቶች ጋር ፊት ለፊት እየተያያችሁ ደግሞ ምርቃናዉ ሲጨምር ደግሞ አንድ ላይ የምጨፍሩ...አላማ በሌላቸዉ ለሴት የማሻ አላህ ድምፅህ ያምራል comment ተጠባባቂ ከሆኑ ሙነሺዶች ነሺዳ እናዳምጣለን እያላችሁ የምታሳልፉ
በመዉሊድ ስም ወደ ሌላ ሀገር እየሄደ ዚና የምሰሩ ...በአጠቃላይ በቢድአ ተጨማልቃችሁ መዉሊድ የምታከብሩ ሆይ!!!

ማንኛዉም ከሀዲስ ከቁርአን ዉጭ የሆነ ነገር ፈጠራ ነዉ ፈጠራ ደግሞ ጥመት ነዉ...ጥመት ደግሞ ወደ ጀሀነም እሳት ነዉ ግድ እንደ ቻርለስ ዳርዊን 40 አመት እስከምትታመሙ አትጠብቁ..የዱንያ ፈተና የሚበዛዉ ያሰብካቸዉ የማይሳኩት በዚህ ሊሆን ይችላልና፡፡

ነብዩ ሰዐወ ለአንድ ቀን ብቻ የሚወደዱ አይደሉም..
ነብዩን ከወደድን ሱናቸዉን እንከተል...ፀጉር አበላልጦ ተቆርጦ ነሺዳ ከማለት ዱቤ ከመቆርቆር...የቱርክ ልብስ ለብሰሽ ፊትሽን በድል ቀለም ሳምፕል አስመስሎ ከንፈርሽን ትኩስ የበግ ሳንባ አስመስለሽ ነቢይ ናፈኩኝ መዉሊድ መዉሊድ ከማለት
ሰኞና ሀሙስ መፆም
ለተለያየ ሰዉ ሰራሽ ዉበት የምትጠቀሚበትን አሁን ላይ ተፈናቅለዉ ስንት የሚያለቅሱ ልብሳቸዉን መቀየር ያቃታቸዉ እህቶችሽ አድርጊ
ቁርአን መቅራት አንዴ ቢከተም 4,307,400 ሀሰናት መሸመት
አጂ ነብይ ጋር የምትደባለቂበትን አድበሽ እቤትሽ ብትቀመጭ ..ነገ ባልሽ ድንግል ነሽ ?ሲልሽ አይንሽ 360 ዲግሪ ከሚዞር ይሄን ጊዜ እግርሽ የሚሽከረከርበትን ቢድአ ቦታ የመሄድ ቀንሺ
የማይጠቅሙ ግን የሚጎዱ ሙነሺዶች ስታዳምጭ ጆሮሽ የደነቆረዉና ተሰምቶሽ በነሺዳ የምታለቅሺ ከሆነ ...ለቅሶ ለሴት ልጅ እንደሳቋ ቀላል ነዉ የሞኝ ለቅሶ ትተሽ በነሺዳ የደነቆረ ጆሮሽን በቁርአን በአዲስ መልክ አደራጂዉ ..የነሺዳ ፍቅር ልብሽ ገብቶ ለማልቀስ የገፋፋሽን በዚክር አርጥቢዉ ..ይሄ ነዉ ነብዩን መዉደድ

#ወንድሜ_ሆይ!!! ነብዩን መዉደድህ በመዉሊድ ከሆነ ተሸዉደሀል
ጫት እየቃምክ ..የጎመን ወጥ ብረድስት ከመምሰል እንደ ሰለሀዲን አዩብ ጀግና ሁን ..ጫት ቅሞ አይደለም እየሩስ አሌምን ነፃ ያወጣዉ ተዉሂድን ይዞ እንጂ
መዉሊድ ላክብር አላክብር እያልክ ከመጨቃጨቅ ስንት ሙስሊም እህቶችህ በካፊሮች ወጥመድ ገብተዉ ሀይማኖታቸዉን ከሚቀይሩ ..እንደ ወንድ ቆላ ደጋ በሰሜን ወይ በደቡብ ተንቀሳቅሰህ አግብተህ ዘርህን ተካ ...አየህ አንተ መዉሊድ እያልክ ሌላ ሀገር ሂደህ ጫት ከምትቅም አገር ቀይረህ ስራ ብትሰራ አላህ ያግዘሀል አንድ እህትህን ሀይማኖቷን ከመቀየር ከተከላከልክ ..አየህ እስልምና የሰዉ ልጅ ወደ መጥፎ እንዳይሄድ መከላከል ስለሆነ የአንተ ማግባት ብዙ ለዉጥ እንዳለዉ ተረዳ...ለምን አሁን ላይ ወንዱ ማስተዳደር አቅቶት ለወደፊት ሴቶች እንዳያስተዳድሩ እየተፈራ ስለሆነ ወንድ ሁነህ ለሴት ብቃትህን አሳይ


እናም ወገን ሆይ !!!! በግርግር በአጣልፍኝ ወቅት መጨፈር የሚወድ..ቡና መጠጣት ጫት መቃም ስጋ መብላት አጂ ነብይ ጋር መጨፈር የሚወድ መዉሊድ መዉሊድ ከሚል ሰዉ እራስን ማግለል ጥቅሙ ለራስ ነዉ ...ግድ እንደቻርልስ ዳርዊን 40 አመት እስከምንታመም አንጠብቅ ...

ኸይር ተናግሬ ከሆነ ከአላህ ነዉ...ስህተት ከሆነ ከሸይጧን ነዉ አላህ ይቅር ይበለኝ
ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሁ ወበረካትሁ

Join
@IslamisUniverstiy_public_group
5.8K viewsedited  06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ