Get Mystery Box with random crypto!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ housinginaddisababa — Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች H
የቴሌግራም ቻናል አርማ housinginaddisababa — Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች
የሰርጥ አድራሻ: @housinginaddisababa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.64K
የሰርጥ መግለጫ

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2024-03-29 22:43:59
በቀደም የአዲስ አበባ ከተማ አመራሮች ስለ ፒያሳና ሌሎች ፕሮጀክታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት ሲያቀርቡ እየሰማሁ ነበር፡፡ፒያሳ ስለነበሩባት ችግሮች ብዛት አብራርተው ሲጨርሱ አሁን የፒያሳ ነዋሪዎች በተላኩበት ቦታ ሽንት ቤት እንዳገኙ ፥ እንቅልፍ ተኝተው እያደሩም እንደሆነ ወዘተ ተነተኑ፡፡ብዙዎች ጥያቄ እንተወውና እንደው ግን የፒያሳ ልማት ለፒያሳ ህዝብ ጥቅም ከሆነ ጠቅላላ የፒያሳን ህዝብ በታትኖ ከማስወገድ እዚያው ፒያሳ ላይ ማስተካከል ይቻል ነበር፡፡ለምሳሌ ዶሮ ማነቂያን ብቻ ማንሳት ቢቻል እና እዚያ ቦታ የመኖሪያ ህንጻዎችን መገንባት ቢቻል የሚገነቡት የመኖሪያ ህንጻዎች የዶሮ ማነቂያን ህዝብ ብቻ ሳይሆን የጣልያን ሰፈርን እና የገዳም ሰፈርን ህዝብ መያዝ ይችሉ ነበር፡፡ከዚያም ገዳም ሰፈር እና ጣልያን ሰፈርን አልምቶ የእሪ በከንቱ እና ሌሎች ነዋሪዎችን ማኖር ይቻል ነበር፡፡ይሄ ብዙ ውስብስብ የሚባል እቅድ አልነበረም፡፡

የደጃች ውቤ ሰፈር ያኔ በኢህአዴግ ዘመን ከፈረሰ በኋላ ህይወታቸው የተመሳቀለ ፥ በድብርት ምክንያት የተጎዱ አረጋውያን ፥ ማህበራዊ መዋቅራቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች እስካሁን ድረስ አላገገሙም፡፡የአሁኑም ቢብስ እንጂ አያንስም፡፡

ማንኛውም ልማት የህዝብን ሁለገብ ጥቅም ታሳቢ ካላረገ ልማት ሊባል አይችልም፡፡

AB Bella
15.4K views19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-29 16:33:35
ዛሬ በሚጠናቀቀው የአክሲዎን ሽያጭ አማራ ባንክ በሰነደ መዋእለ ንዋይ ገበያ (Securities Exchange) ላይ ከግል ኢንቨስተሮች ከፍተኛ ባለድርሻ የሚያረገውን አክሲዎን ገዛ።

አማራ ባንክ ከፍተኛውን መዋዕለ ነዋይ በመመደብ የ 10 በመቶ የአክሲዮን ድርሻ መግዛቱን ገልጿል።

ባንኩ የሰነደ መዋዕለ ገበያን ላይ በ 90.6 ሚሊዮን ብር ከፍተኛዉን ድርሻ የገዛ የግል ኩባንያ መሆን ችሏል። ይህን ተከትሎ የአክሲዮን ግዢን የመፈፀመ አምስተኛዉ ባንክ ሆኗል።

ካፒታል ገበያን በኢትዮጵያ ለማቋቋም ድርሻ ከገዙት ባንኮች ዉስጥ እስካሁን 308.1 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል ።
ካፒታል
18.1K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 22:22:17 "ምሳ ከፍለን ብንበላም ውሃ በነፃ ነበር" ብለን ብንነግራቸው፣ ልጆቻችን እንዴት ያምኑናል?!

ድሮ ድሮ ምግብ ቤት ገብተን ሽሮ፣ በያይነቱ፣ ፓስታ በእንጀራ አሊያም ድንች በስጋ እናዝዝ ነበር። እና ውሃ በነፃ መሆኑ ግልጽ ነው። በጭራሽ ጥያቄም አይደለም። ምግብህን ከፍለህ ትበላና አንድ ጆግ ውሃ በነፃ ትጠጣለህ።

ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አስተናጋጆች አንድ ጥያቄ ይጠይቁ ጀመር፣ "የብርጭቆ ውሃ ወይንስ የታሸገ?!"። ምርጫህ የብርጭቆ ውሃ ከሆነ ምንም ንትርክ የለውም፤ ውሃ በጆግ ይመጣል። አንዳንድ ቦታ ጭራሽ በታጠነ ጆግ ነው የሚቀርብልህ።

በጊዜ ሂደት አስተናጋጆች ሌላ ጨዋታ ጀመሩ፤ "ይቅርታ የብርጭቆ ውሃ የለንም"። ንትርክ ተጀመረ ማለት ነው። ትንሽ ትነጫነጭና የታሸገ ውሃ ታዛለህ። ቢሆንም የውሃ ዋጋ አነስተኛ ነበር።

በመጨረሻ፣ የብርጭቆ ውሃ የሚባል ታሪክ ሆኖ አረፈ። አሁን ምግብ ቤት ገብተህ "የብርጭቆ ውሃ ይሁንልኝ" ማለት ነውር ነው፤ መሳቂያ መሆን ነው። ያለማጋነን የምግብ እና የውሃ ዋጋ መሳ ለመሳ ነው።

እና "ምሳ ከፍለን ብንበላም ውሃ በነፃ ነበር" ብለን ለልጆቻችን ብንነግራቸው ያምኑናል ወይ?!
Lami S
20.2K views19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 19:27:12 "አፍሮ ባሮ ሜት" የተሰኘው የጥናትና ምርምር ተቋም፣ በፈረንጆች 2023 ከ10 ኢትዮጵያዊያን ስድስቱ በከፋ ወይም በመካከለኛ ድህነት ውስጥ ማለፋቸውን በጥናት ማረጋገጡን ገልጧል። ተቋሙ ከበፈረንጆች 2020 ጋር ሲነጻጸር፣ በከፋ ወይም መጠነኛ ድህነት ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር በ7 በመቶ መጨመሩን አስታውቋል።በጥናቱ መሠረት፣ በ2023 የምጣኔ ሃብት ኹኔታው "በጣም መጥፎ" ወይም "መጥፎ" መኾኑን ለጥናቱ የገለጡ ኢትዮጵያዊያን 65 በመቶ ሲኾኑ፣ በ2020 ግን ቁጥሩ 45 በመቶ ብቻ እንደነበር ተገልጧል። ጥናቱ፣ 18 በመቶ ያህሉ ኢትዮጵያዊያን ዓመቱን በከፋ የምግብ ዕጦት እንዳሳለፉና 42 በመቶዎቹ የሚኾኑት ደሞ አልፎ አልፎ ወይም ብዙ ጊዜ የምግብ እጥረት እንደገጠማቸው ማመልከቱንም ተቋሙ ጠቅሷል።
12.6K views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 11:09:33
የተሳሳተ መረጃ ስለማረም

ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ በተለይም በቲክቶክ በተለቀቀ የተሳሳተ መረጃ የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝግባችሁ እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ ብቁ መሆን አለመሆናችሁን ባምቢስ በሚገኘው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ 5ኛ ፎቅ መታችሁ እንድታዩ በሚል የተለቀቀው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን  እየገለፅን ተመዝግባችሁ እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ ላተፈለገ እንግልት እንዳትዳረጉ የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ይገልፃል፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እና ኮርፖሬሽኑ ነዋሪውን በተለይም ተመዝግቦ የሚጠባበቀውን የቤት ባለቤት ለማድረግ የተለያዩ የቤት ልማት አማራጮችን ተግባራዊ በማድረግ ከምንጊዜውም  በተሻለ መልኩ እየሰሩ እንደሚገኝ እየገለፅን ተመዝጋቢዎችም ሆነ ሌሎች ነዋሪዎች የተቋሙ ባልሆኑ ማህበራዊ ሚዲያዎችም ሆነ ግለሰቦች በሚያናፍሱት ወሬ እንዳትታለሉ እያስገነዘብን ትክክለኛውን የቤት መረጃ ለማግኘት ከታች ያሉትን የማህበራዊ ሚዲያ ሊንኮች ብቻ እንድትጠቀሙ እናሳስባለን፡፡ 

የአ/አ/ል/ አስተዳደር ቢሮ
16.7K views08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-27 20:42:37
ምንም አይነት የኮንደሚኒየን የምዝገባ ማስታወቂያ አልወጣም

የአዲስ  አበባ ቤቶች ሄዳችዉ online መሆናችዉ አረጋግጡ የሚባለዉ ወሬ ተሰራጭቷል።

ስለዚህ ለ "Online ምዝገባ ለማረጋገጥ አዲስ አበባ ቤቶች ቢሮ እንድትሄድ" እየተባለ የተሰራጨው ወሬ ሀሰተኛ ነው።
17.4K viewsedited  17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-27 20:04:58
መንግሥት በዋና ከተማ አዲስ አበባ የሚከናወኑ የቤት ፈረሳዎች ከተማዋን ለማዘመንና ለነዋሪዎቿም ምቹ ለማድረግ የታሰበ የልማት እቅድ መሆኑን ይገልጻል። መኖሪያ ቤታቸው ለፈረሰባቸው ወገኖችም ምትክ ቦታ እንደሚሰጥም እንዲሁ። በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ሥራ ሂደት መገምገሙንም ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በማኅበራዊ መገናኛ ገጻቸው አመልክተዋል። በዚህም ቀዳሚ ዓላማቸው አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ የተመቸች ሳቢ ከተማ ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳካት መሆኑንም ገልጸዋል። «የማልማት ሥራ ሂደቱ በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚና በመንግሥት ብሎም አነስተኛ ገቢ ባላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች እና የተለያዩ አካላት የተያዙና የተከራዩ ንብረቶችን የነካ ሊሆን ቢችልም ይህ ለረዥም ጊዜ ፋይዳ ትልም ይዞ የተነሳ ሥራ ሲጠናቀቅ ለሁሉም ባለድርሻ አካል ብሎም ለሰፊው ሕዝብ የሚሰጠው ጥቅም ትልቅ ነው»ም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ከተማን ለማዘመን በማሰብ የነባር ቤቶች እና መንደሮች መፍረስ አስቀድሞ ከሌሎች ሃገራት ተሞክሮ ቢወሰድበት መልካም እንደነበር የሚጠቁሙ በበኩላቸው ለታሪካዊ ሕንጻዎችና ቅርሶች ተገቢና ሞያዊ ጥንቃቄ እያሳሰቡ ነው። ከበቂ መተላለፊ መንገድ አንስቶ የመጸዳጃ ቤቶች እና የፍሳሽ ማውረጃ መስመሮች ጉድለት የሚታይባቸው ጭርንቁስ መንደሮችን የዋና ከተማዋን ደረጃ በጠበቀ መልኩ ማሻሻል እንደሚያስፈልግ የሚገልጹ ወገኖች ጥንታዊ የከተማ ገጽታዎችን ጠብቆ ማቆየት በሌሎች ሃገራት ለቱሪዝም መስህብነት አይነተኛ ሚና እንዳለውም ያነሳሉ።
DW
16.8K views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-27 19:43:25
ፒያሳ ዛሬ
16.1K views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-27 19:39:39
ቦሌ ቡልቡላ 5 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ግንባታ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 12 በሚገኘው ቡልቡላ 5 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ እያካሄደ ይገኛል፡፡

የመንገዱን ግንባታ እያከናወነው የሚገኘው ሶፍ ዑመር ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የተባለ ሀገር በቀል ድርጅት ሲሆን.፣ የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ጎጎት ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ ይከታተለዋል፡፡

ይህ የመንገድ ግንባታ በአጠቃላይ 2 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን፣ 1 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትሩ በአስፋልት እንዲሁም ቀሪው 1ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍነው የመንገዱ ክፍል ደግሞ በኮብል ደረጃ የሚገነባ ነው፡፡

ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ 390 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበለት ሲሆን፣ አሁን ላይ የአፈር ቆረጣና ሙሌት ፣ የቱቦ ቀበራ እና ተያያዥ ስራዎች በመከናነወን ላይ ናቸው፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመንገዱ ወሰን ውስጥ የሚገኙ ቀሪ የወሰን ማስከበር ስራዎችን በማጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
17.0K views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-27 12:58:57
#CBE

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀሪ ገንዘብ ያልመለሱ ገንዘቡን እንዲመልሱ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

ቀሪ ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ስም ዝርዝርም ይፋ አድርጓል።

ባንኩ ችግር ገጥሞት በነበረበት ወቅት በህገወጥ መንገድ ገንዘብ የወሰዱ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ተመላሽ እንዲያደርጉ አሳስቦ ነበር።

በዚህ መሰረት 9281 የሚሆኑ ግለሰቦች በተሰጠው ጊዜ ገደብ ተጠቅመው የወሰዱትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ መልሰዋል ብሏል።

5166 ግለሰቦች ባንኩ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም ያላግባብ ከወሰቡትን ገንዘብ በከፊል ተመላሽ ያደረጉ ቢሆንም እስከ ዛሬ ድረስ ቀሪውን ገንዘብ አልመለሱም ሲል ገልጿል።

ባንኩ ወደ ቀጣዩ #ሕጋዊ እርምጃ ከማለፉ በፊት ቀሪውን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ድረስ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ገንዘቡን የማይመልሱ ከሆነ በባንኩ በኩል ቀጣይ ሕጋዊ እርምጃ እንደማይኖር አረጋግጧል።

እስከተጠቀሰው ቀን ገንዘቡን #የማይመልሱ ካሉ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘዴዎችን በመጠቀም ፦
- ሙሉ ስማቸው
- ፎቷቸው
- በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ በመውሰድ ወንጀል መጠርጠራቸውን በመግለፅ ለሚመለከታቸው የሕግ አካላትና ተቋማት ይገለጻል ለሕዝብም ይፋ ይደረጋል ብሏል።

ከሕግ አካላት እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር ቀጣይ #የወንጀል፣ የፍትሐ ብሔር እና የአስተዳደር ሕጋዊ እርምጃዎችም እንደሚወሰዱ በጥብቅ አስጠንቅቋል።
17.8K views09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ