Get Mystery Box with random crypto!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ housinginaddisababa — Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች H
የቴሌግራም ቻናል አርማ housinginaddisababa — Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች
የሰርጥ አድራሻ: @housinginaddisababa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.64K
የሰርጥ መግለጫ

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2024-03-09 03:26:02
የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ክልከላ በተደረገባቸው እቃዎችና ተሽከርካሪዎች ላይ የተደረገ ማስተካከያ
14.9K views00:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-08 21:10:23
" አሸናፊዎች ባለመቅረባቸው ገንዘቡ ወደ ተቋሙ ገብቷል " - ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር

እያንዳንዳቸው 4 ሚሊዮን ብር ዕጣ ያላቸው ሁለት የሎተሪ ቲኬቶች አሸናፊዎች ባለመቅረባቸው ስምንት ሚሊዮን ብር ዛሬ የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ተመላሽ መደረጉን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታውቋል።

ተቋሙ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጠው ቃል ፤ እነዚህ ሁለት ዕጣዎች ብሔራዊ ሎተሪ ከሚያሳትማቸው ከፍተኛ ዕጣ የሆነው 20 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ቲኬቶች ናቸው ብሏል።

በእንቁጣጣሽ ሎተሪ ከቀረቡት 5 ቲኬቶች ሶስቱ ቀርበው 12 ሚሊዮን ብር ሁለት አሸናፊዎች ቢረከቡም የቀሪዎቹ ሁለት ቲኬቶች አሸናፊዎች ባለመቅረባቸው ገንዘቡ ወደ ተቋሙ ገብቷል ሲል አሳውቋል።

ጳጉሜ 2015 ዓ.ም የወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ የሁለቱ ቲኬቶች ወይም የ8 ሚሊዮን ብር አሸናፊ በቀን ስራ የሚተዳደር አንድ ግለሰብ ሲሆን ዕጣው ከወጣ ከ3 ወር በኋላም ወስዷል።

ሌላኛው አሸናፊ የቀን ሰራተኛው የሚሰራበት መኪና አሽከርካሪ የሆነ ግለሰብ ሲሆን መስከረም ወር መጨረሻ ላይ መጥቶ የ4 ሚሊዮን ብር ሽልማቱን መውሰዱን ቢቢሲ አማርኛው ክፍል የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደርን ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።
tikvahethiopi
15.8K views18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-08 21:03:54 ከመጋቢት 22፣2015 ዓ/ም በፊት የባንክ ፈቃድ የተሰጠባቸው ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቀደ።

ተሽከርካሪዎቹ እና እቃዎች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ የተፈቀደውም በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል የሚቀርቡ ሠነዶች አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎባቸው ነው ተብሏል።

ይህም የሚሆነው ለመጨረሻ ጊዜ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሸን ከፃፈው ደብዳቤ ላይ ተመልክተናል።

የውጪ ምንዛሬ ፈቃድ ክልከላ በተደረገባቸው እቃዎችና ተሽከርካሪዎች ላይ ማስተካከያ መደረጉን በመጥቀስ በሚኒስትር ድኤታው እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) የተፃፈ ደብዳቤን ሸገር ተመልክቷል።

ተሽከርካሪን ጨምሮ 28 ምርቶች ከጥቅምት 4፣2016 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የውጭ ምንዛሬ እንደይፈቀድላቸው መወሰኑ ይታወሳል።

የውጭ ምንዛሬ ክልከላ ከተደረገባቸው እቃዎች ጋር ተያይዞ በአፈጻጸም ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት ማስተካከያ ተደርጓል ተብሏል፡፡

በጥቅምት ወር በወጣው እና የውጭ ምንዛሬ የማይፈቀድላቸው 38 ዝርዝሮች ውስጥ የተካተቱ ምርቶች የሆኑ ግን ደግሞ ምርቶቹ እና ተሽከርካሪዎቹ በሕግ በተደነገገ ፍራንኮ ቫሉታ የሚገቡ ከሆነ በተደረገው ማስተካከያ ክልከላው አይመለከታቸውም ተብሏል ።

ተሽከርካሪዎች ጎረቤት አገር ወደብ ወይም ጉምሩክ ጣቢያ በደረሱበት ጊዜ በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ (ማሻሻያ) ቁጥር 1287/2015 አንቀጽ 2(24) ለአዲስ ተሽከርካሪ የተሰጠውን ትርጉም የሚያሟሉ ሆነው ነገር ግን ይህን ውሳኔ ሲጠብቁ የተሽከርካሪው እድሜ ያገለገለ ምድብ ውስጥ የገባባቸው ከሆነ በክልከላው ምክንያት በጎረቤት አገር ወደብ ወይም በጉምሩክ ጣቢያ የቆዩበት ጊዜ ሳይታሰብ እድሜው ጎረቤት አገር ወደብ ወይም የጉምሩካ ጣቢያ እስከደረሰበት ያለውን ጊዜ ድረስ ብቻ በማስላት እንዲስተናገዱ ማስተካከያ ተደርጓል።

የቀረጥ ነፃ ሱቆች የሚያስመጧቸው ዕቃዎች የውጭ ምንዛሪ ክልከላው እንደማይመለከታቸው ማስተካከያውን የሚያስረዳው ደብዳቤ ላይ ተጠቅሷል።

የገንዘብ ሚኒስቴር የውጪ ምንዛሬ ክልካላው በተመለከተ በጥቅምት ወር 2015 ዓ/ም የተጻፈው ደብዳቤ እና በተለያየ ጊዜ የተሰጡ ማብራሪያዎች መሻራቸውንና በማስተካከያው መሰረት ተፈፃሚ እንዲሆን መወሰኑን ከደብዳቤው ላይ ተመልክተናል።
ንጋቱ ሙሉ
ሸገር
14.8K views18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-08 20:58:47
በአዲስ አበባ  ከየካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ የነበረው የመሬት አገልግሎት በቀጣይ ሳምንት ውስጥ እንደሚጀምር የአዲስ አበባ መሬት ልማት አስተዳደር አስታውቋል
ላለፈው አንድ ሳምንት ተቋርጦ የነበረው የመሬት አገልግሎት በመጋቢት ወር የመጀመሪያዎቹ ቀናት ላይ እንደሚጀምር የአዲስ አበባ መሬት ልማት አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወ/ሮ እመቤት ሙሉነህ ተናግረዋል፡፡

በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የማጥራት ስራዎችም ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቁመው፤ እንዲህ አይነት ስራዎች መሰራታቸው አገልግሎቱን በፍጥነት ለማሳለጥ እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡
16.3K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-01 16:12:00
እስቲ ስም አውጡለት
15.1K viewsedited  13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-01 16:06:57 የጨረታ መክፈቻ ቀን በተመለከተ 6 ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ህንፃ 12ኛ ፎቅ አዳራሽ ዉስጥ ከ03/07/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 13/07/2016 ዓ.ም ይሆናል፡፡

> በቀን 03/07/2016 ዓ.ም የሚከፈቱ የጨረታ ሳጥን ቁጥር 1 ገቢ የተደረጉ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ በቤተል ሳይት የሚገኙ ለጨረታ የቀረቡት ንግድ ቤቶች በሙሉ ይሆናሉ፡፡

➢ በቀን 04/07/2016 ዓ.ም የሚከፈቱ የጨረታ ሳጥን ቁጥር 2 ገቢ የተደረጉ በቦሌ ክ/ከተማ በሜታ ሳይት የሚገኙ ለጨረታ የቀረበ) መኖርያ ቤቶች እና በየካ ክ/ከተማ በሳህሊተ ምህረት ሳይት የሚገኙ ለጨረታ የቀረቡት ንግድ ቤቶች በሙሉ ይሆናሉ፡፡

➢ በቀን 05/07/2016 ዓ.ም የሚከፈቱ የጨረታ ሳጥን ቁጥር 3 ገቢ የተደረጉ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በአራብሳ ጃርሶ ሳይት የሚገኘ ለጨረታ የቀረቡት መኖርያ ቤቶች በሙሉ ይሆናሉ፡፡

➢ በቀን 06/07/2016 ዓ.ም የሚከፈቱ የጨረታ ሳጥን ቁጥር 4 ገቢ የተደረጉ በንፋስ ስልክ ላፍቶ በክ/ከተማ በላፍቶ ሳይት የሚገኘ ለጨረታ የቀረቡት ንግድ ቤቶች እና መኖርያ ቤቶች በሙሉ ይሆናሉ፡፡

➢ በቀን 09/07/2016 ዓ.ም የሚከፈቱ የጨረታ ሳጥን ቁጥር 5 ገቢ የተደረጉ በለሚ ኩሪ ክ/ከተማ በአራብሳ ገብርኤል ሳይት የሚገኘ ለጨረታ የቀረቡት መኖርያ ቤቶች በሙሉ ይሆናሉ፡፡

➢ በቀን 10/07/2016 ዓ.ም ዓ.ም የሚከፈቱ የጨረታ ሳጥን ቁጥር 6 ገበ, የተደረገ በለሚ ኩሪ ክ/ከተማ በሰፈራ ማርያም ሳይት

የማገኙ ለጨረታ የቀረቡት መኖርያ ቤቶች በሙሉ ይሆናሉ፡፡ ➢ በቀን 11/07/2016 ዓ.ም የሚከፈቱ የጨረታ ሳጥን ቁጥር 7 ገቢ የተደረጉ የካ ክ/ከተማ ጉራራ ሳይት የሚገኙ ለጨረታ የቀረቡት

ንግድ ቤቶች እና መኖሪያ ቤቶች በሙሉ ይሆናሉ፡፡

+ 12/07/2016 3. የሚከፈቱ የጨረታ ሳጥን ቁጥር 8 ገቢ የተደረጉ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ገላን ጉራ · ሳይት የሚገኘ ለጨረታ የቀረቡት ንግድ ቤቶች እና መኖርያ ቤቶች በሙሉ ይሆናሉ፡፡

➢ በቀን 13/07/2016 ዓ.ም የሚከፈቱ የጨረታ ሳጥን ቁጥር 9 ገቢ የተደረጉ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወርቁ ሰፈር ሳይት የሚገኘ * ለጨረታ የቀረቡት ንግድ ቤቶች እና መኖርያ ቤቶች በሙሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
15.0K views13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-01 15:30:35

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ ለተጫራቾች በሙሉ

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ቀን የተራዘመ መሆኑን ስለማሳወቅ

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖራሽን በመንግስት በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው የተጠናቀቁ የመኖሪያ እና ንግድ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ለማስተላለፍ በወጣው ግልጽ ጨረታ መሰረት ከጥር 27/2016ዓ.ም ጀምሮ እየተሽጠ መሆኑ እና የካቲት 20/2016 ዓ.ም ላይ የሚጠናቀቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ሰነድ ፍላጎት ከፍተኛ ስለሆነ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ታሳቢ በማድረግ ቅዳሜን እና እሁድን ጨምሮ እስከ መጋቢት 02/2016 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ ሲሆን የመጨረሻው ቀን በ02/07/2016 ዓ.ም እስከ ቀነ· 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ እንደሚከናወን እና በዚሁ እለት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የሰነድ ማስገቢያ ሰዓት መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
14.5K views12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-01 13:19:44
የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ለሽያጭ ያቀረባቸውን ቤቶች ጨረታ ማራዘሙን አስታውቋል

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጋር በመተባበር ያስገነቧቸውን 3 ሺህ 452 የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በሽያጭ ለማስተላለፍ የጨረታ ሰነድ በመሸጥ ላይ ይገኛል።

ይኽን ተከትሎ “ከሕብረተሰቡ በመጣ ጥያቄ መነሻነት” በማለት የጨረታ መዝጊያ ጊዜው ለ10 ቀናት የተራዘመ መሆኑን ገልጿል።

ኮርፖሬሽኑ ጥር 27 ቀን 2016  ጀምሮ ይፋ ባደረገው ማስታወቂያ፣ አጋጠመኝ ያለውን የፋይናንስ አቅም ችግር ለመፍታትና ተጨማሪ ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ለመገንባት በማለት፣  የመኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ሱቆችን በጨረታ ለመሸጥ የጨረታ ሰነዶችን ሽያጭ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት እንደሚያካሂድ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በዚህም የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ በኃላ ለበርካታ ዓመታት ኮንደሚኒየም ቤት ለማግኘት የቆጠቡ እና እየቆጠቡ የሚገኙ ነዋሪዎችን ያስቆጣ ሲሆን የጨረታ ሂደቱ እንዲቆም ቋሚ ኮሚቴ በማቋቋም መጠየቃቸውም ይታወሳል።

በወቅቱ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የ1997 ተመዝጋቢዎች እና ቆጣቢዎች “ደሃው ህብረተሰብ ለዓመታት ከልጆቹ ጉሮሮ ነጥቆ እየቆጠበ መንግስት ቤቶችን ለጨረታ ማቅረቡ ያሳዝናል” ሲሉም ገልጸዋል።

አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የተለያዩ ግለሰቦች ለበርካታ ዓመታት የቆጠቡ እንዲሁም ሙሉ ክፍያውን የፈጸሙ ሲሆኑ አሁን መንግስት እያደረገ ያለው ነገር ለረጅም ዓመታት ተስፋ ያደረጉበትን መኖሪያ ቤት “ማግኘት የማይቻል ነው” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸው ነበር።

የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን በወቅቱ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ያልሰጠበት ቢሆንም፤ በድጋሚ “ከሕብረተሰቡ በመጣ ጥያቄ መነሻነት” በማለት የጨረታ መዝጊያ ጊዜው ማራዘሙን አስታውቋል።

(አዲስ ማለዳ)
15.0K views10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-01 13:15:01
#የጨረታ_ማራዘሚያ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጋር በመተባበር ያስገነቧቸውን  3,452 የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በሽያጭ ለማስተላለፍ የጨረታ ሰነድ በመሸጥ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ይህን ተከትሎ ከሕብረተሰቡ በመጣ ጥያቄ መነሻነት የጨረታ መክፈቻ ጊዜው ለ10 ቀናት የተራዘመ መሆኑ ታውቆ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች እስከ መጋቢት 02/2016 ዓ/ም ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ምሽቱ 1፡30 እንዲሁም እሁድ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ቀኑ 6፡00 በሁሉም ክፍለከተሞች ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት እንደሚችል እንገልፃለን፡፡


የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
14.8K views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-29 12:49:47 #ፒያሳ

በአዲስ አበባ ፤ ፒያሳ አካባቢ በተለምዶ " ዶሮ ማነቂያ " ተብሎ በሚጠራው ቦታ የሚገኙ ነዋሪዎች፤ በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ ከስፍራው እንዲነሱ ቀነ ገደብ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ምትክ የመኖሪያ እና የንግድ ቦታ ሳያዘጋጅላቸው፤ ከስፍራው " በአጭር ጊዜ ውስጥ " ተነሱ ማለቱ በነዋሪዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ አስነስቷል።

የፒያሳና 4 ኪሎ አካባቢ መልሶ የማልማት ፕሮጀክትን በተመለከተ ትላንት በወረዳ ደረጃ የተደረጉ ውይይቶች " በአለመግባባት " እና " በረብሻ " መበተናቸውን ተከትሎ ዛሬ ከአዲስ አበባ አስተዳደር እና ከአራዳ ክ/ከተማ የስራ ኃላፊዎች ጋር ነዋሪዎች ውይይት አድርገው ነበር።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

° በፒያሳ አካባቢ በአክሲዮን የተደራጁ ነዋሪዎች ማህበርን በሰብሳቢነት የሚመሩ ግለሰብ ፦

" ቤት ለመቀባት እንኳ 3 ቀናት ይበቃል ወይ? ትላንት በነበሩ ውይይቶች ይህንን ውሳኔ የሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ለሊቱን ሙሉ ሳይተኙ አድረዋል።አሁንም በስጋት ላይ ናቸው። "

° 5 አባላት ያሉት ቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን የገለጹ እናት ፦

" አብዛኞቹ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደ እኔ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ናቸው። በስፍራው የታቀደው የመልሶ ማልማት ነዋሪዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ እና ምትክ የመኖሪያ ስፍራ ያዘጋጀ ሊሆን ይገባዋል። "

° ሌላኛዋ የአካባቢው ነዋሪ ፦

" ለልማት ተነሺዎች የሚያዘጋጀው አማራጭ የስፍራውን ማህበራዊ ትስስር በማይበጥስ መልኩ ሊደርግ ይገባል። በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያለን የአካባቢው ነዋሪዎች እርስ በእርስ ተደጋግፈን የምንኖር በመሆናችን ምትክ የኮንዶሚኒየም ቤት የሚሰጠን ከሆነ በአንድ ቦታ ላይ የምንሰፍርበት ሁኔታ ይመቻች ። "

ከባለስልጣናት ምን ምላሽ ተሰጠ ?

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽህፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጥላሁን ፤ ነዋሪዎቹን ከቦታው ለማንሳት ያቀደው በዘጠና ቀናት ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል።

አስተዳደሩ ለነዋሪዎች  ምትክ የኮንዶሚኒየም፣ የቀበሌ እና የኪራይ ቤቶች እንደሚያዘጋጅ ቃል ገብተዋል። 

የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አበበ ተቀባ ፤ አስተዳደሩ " ቅደመ ሁኔታ ሳያሟላ አንድም ሰው አይነቃነቅም " ብለዋል።

የከተማው አስተዳደር " ቅደመ ሁኔታውን ካሟላ " ነዋሪዎች በ3 ቀን ቢነሱ ችግር እንደማይፈጥርም ጠቁመዋል።

" ይህ ፕሮጀክት እንዳያልቅ የሚያንጓትት ካለ ኃላፊነቱን ራሱ ነው የሚወስደው " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በዛሬው ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ በመልሶ ማልማቱ የልማት ተነሺዎቹን ሂደት የሚከታተል ኮሚቴ አባላት ምርጫ ተከናውኗል።

በመልሶ ማልማት እቅዱ የተካተተውን የፒያሳ አካባቢን በ6 በመክፈል፤ ከእያንዳንዱ ስፍራ 6 ሰዎች በህዝብ ተመርጠዋል። 

(ከላይ በፒያሳ ስለሚካሄደው መልሶ ማልማት ስራ ማብራሪያ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ የ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " መሆኑን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
18.6K views09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ