Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ  ከየካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ የነበረው የመሬት አገልግሎት በቀጣይ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

በአዲስ አበባ  ከየካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ተቋርጦ የነበረው የመሬት አገልግሎት በቀጣይ ሳምንት ውስጥ እንደሚጀምር የአዲስ አበባ መሬት ልማት አስተዳደር አስታውቋል
ላለፈው አንድ ሳምንት ተቋርጦ የነበረው የመሬት አገልግሎት በመጋቢት ወር የመጀመሪያዎቹ ቀናት ላይ እንደሚጀምር የአዲስ አበባ መሬት ልማት አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወ/ሮ እመቤት ሙሉነህ ተናግረዋል፡፡

በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የማጥራት ስራዎችም ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቁመው፤ እንዲህ አይነት ስራዎች መሰራታቸው አገልግሎቱን በፍጥነት ለማሳለጥ እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡