Get Mystery Box with random crypto!

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ ለተጫራቾች በሙሉ የጨረታ ሰነድ መሸጫ ቀን የተራዘመ መሆኑን ስለማሳወቅ የአዲ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች


ማ ስ ታ ወ ቂ ያ ለተጫራቾች በሙሉ

የጨረታ ሰነድ መሸጫ ቀን የተራዘመ መሆኑን ስለማሳወቅ

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖራሽን በመንግስት በጀት በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተገንብተው የተጠናቀቁ የመኖሪያ እና ንግድ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ለማስተላለፍ በወጣው ግልጽ ጨረታ መሰረት ከጥር 27/2016ዓ.ም ጀምሮ እየተሽጠ መሆኑ እና የካቲት 20/2016 ዓ.ም ላይ የሚጠናቀቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ሰነድ ፍላጎት ከፍተኛ ስለሆነ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ታሳቢ በማድረግ ቅዳሜን እና እሁድን ጨምሮ እስከ መጋቢት 02/2016 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ ሲሆን የመጨረሻው ቀን በ02/07/2016 ዓ.ም እስከ ቀነ· 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ እንደሚከናወን እና በዚሁ እለት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የሰነድ ማስገቢያ ሰዓት መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡