Get Mystery Box with random crypto!

' አሸናፊዎች ባለመቅረባቸው ገንዘቡ ወደ ተቋሙ ገብቷል ' - ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር እያንዳንዳ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

" አሸናፊዎች ባለመቅረባቸው ገንዘቡ ወደ ተቋሙ ገብቷል " - ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር

እያንዳንዳቸው 4 ሚሊዮን ብር ዕጣ ያላቸው ሁለት የሎተሪ ቲኬቶች አሸናፊዎች ባለመቅረባቸው ስምንት ሚሊዮን ብር ዛሬ የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ተመላሽ መደረጉን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታውቋል።

ተቋሙ ለቢቢሲ አማርኛው ክፍል በሰጠው ቃል ፤ እነዚህ ሁለት ዕጣዎች ብሔራዊ ሎተሪ ከሚያሳትማቸው ከፍተኛ ዕጣ የሆነው 20 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ቲኬቶች ናቸው ብሏል።

በእንቁጣጣሽ ሎተሪ ከቀረቡት 5 ቲኬቶች ሶስቱ ቀርበው 12 ሚሊዮን ብር ሁለት አሸናፊዎች ቢረከቡም የቀሪዎቹ ሁለት ቲኬቶች አሸናፊዎች ባለመቅረባቸው ገንዘቡ ወደ ተቋሙ ገብቷል ሲል አሳውቋል።

ጳጉሜ 2015 ዓ.ም የወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ የሁለቱ ቲኬቶች ወይም የ8 ሚሊዮን ብር አሸናፊ በቀን ስራ የሚተዳደር አንድ ግለሰብ ሲሆን ዕጣው ከወጣ ከ3 ወር በኋላም ወስዷል።

ሌላኛው አሸናፊ የቀን ሰራተኛው የሚሰራበት መኪና አሽከርካሪ የሆነ ግለሰብ ሲሆን መስከረም ወር መጨረሻ ላይ መጥቶ የ4 ሚሊዮን ብር ሽልማቱን መውሰዱን ቢቢሲ አማርኛው ክፍል የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደርን ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።
tikvahethiopi