2024-02-25 21:50:58
የቤቶች ልማትን በተመለከተ በግማሽ ዓመቱ የተከናወኑ ሪፖርት
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቤቶች ልማት አንጻር በበጀት ዓመቱ ግንባታቸውን ለማስጀመር ከታቀደው 120 ሺህ ቤቶች መካከል 99 ሺህ 113 ቤቶች ማልማትጠመቻሉን ገልፀዋል፡፡
ከተማ አስተዳደር ከቤቶች ልማት አንጻር በአቃቂ ክፍለ ከተማ 60,185፣ በቦሌ 14 ሺህ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ 10 ሺህ፣ በልደታ 8,600፣ በቂርቆስ 6,156፣ በጉለሌ 172 በድምሩ 99 ሺህ 113 ቤቶች ማልማት መቻሉን ከንቲባ አዳነች በሪፖርታቸው ገልፀዋል።
ከተማ አሰተዳደሩ በዘንድሮ በጀት ዓመት የ111 ሺህ ቤቶች መገንባት የሚያስችል የአጋርነት ውል እና የመሬት ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪ በመንግት በጀት የተገነቡ 4200፣ በበጐ አድራጎት የተሰሩ 5023 ፣ በግለሰብ እና በሪልስቴት ከ10,000 አጠቃላይ 19,223 ቤቶች ተገንብቶዋል ብለዋል፡፡
ከቤቶች ግንባታ በተጨማሪ በመንግስትና በግል አጋርነት ፕሮግራም እየተገነባ የሚገኘው ለሚ ፓርክ ግንባታው 60 በመቶ ደርሷል ሲሉም ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም ከቤቶች ልማት አኳያ 149,892 የመንግስት ቤቶች እና 126,734 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መረጃን በዘመናዊ ሶፍትዌር ማደራጀት ተችሏል፣
125ሺህ 764 የቤት ፈላጊዎችን መረጃ እና 307 ሺህ 726 የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚዎች መረጃ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተደራጅቷል ሲሉ ከንቲባዋ ገልፀዋል፡፡
21.2K views18:50