Get Mystery Box with random crypto!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የሰርጥ አድራሻ: @housinginaddisababa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.83K
የሰርጥ መግለጫ

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2024-02-25 09:17:35
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በመዲናዋ 4 ዋና ዋና የመንገድ ኮሪደሮች እንዲለሙ ውሳኔ አሳለፈ

ካቢኔው አዲስ አበባ የደረሰችበትን የዕድገት ደረጃ የሚመጥን የመንገድ ኮሪደሮች ልማት ለማከናወን የሚያስችል ዕቅድ ላይ ተወያይቷል።

በዚህም የከተማዋን አጠቃላይ የመንገድ ሽፋን እና ዘመናዊነት እንዲሁም የትራንስፖርት ፍሰት ወደ ላቀ ደረጃ ሊያሳድጉ የሚችሉ የመንገድ ኮሪደር እና የአካባቢ ልማቶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

በውሳኔው መሠረት የሚለሙት የመንገድ ኮሪደሮች የሚከተሉት መሆናቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፦

• ከአራት ኪሎ በመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ድልድይ (7 ኪ. ሜትር)
• ከቦሌ አየር መንገድ እስከ መገናኛ ዳያስፖራ አደባባይ (4.9 ኪ. ሜትር)
• ከመገናኛ ዳያስፖራ አደባባይ በአራት ኪሎ በኩል የዓድዋ ድል መታሰቢያ አካባቢ ድረስ (6.4 ኪ. ሜትር)
• ከፒያሳ አድዋ ድል መታሰቢያ ዙርያ በለገ-ሃር፣ ሜክሲኮ፣ ሳርቤት በኩል እስከ ወሎ ሰፈር (10 ኪ. ሜትር)

እነዚህ የመንገድ ኮሪደር ልማቶች ዘመናዊ ከመሆናቸውም በላይ ዓለም አቀፍ የስማርት ሲቲ ስታንዳርድን በማሟላት የከተማዋን ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ ናቸው ተብሏል።

የመንገድ ኮሪደር ፕሮጀክቶቹ አዋሳኝ የወንዝ ተፋሰሶችን ያቀፉ፣ ለሳይክልና ሞተር አልባ ትራንስፖርትም አገልግሎት የሚሰጡ እንደሚሆኑ ተጠቅሷል።
21.5K views06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-11 12:22:21
የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም

በአዲስ አበባ ፒያሳ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ዛሬ ይመረቃል።

በ5 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ሙዚየም የኢትዮጵያውያን ጀግኖች ለመላው ጥቁር ህዝብ ኩራት የሆነ ተጋድሏቸውን የሚዘክሩ ስራዎችን ይዟል።

በሙዚየሙ ውስጥ የዓድዋ ድል የክተት አዋጅ የታወጀበት ነጋሪት በነሐስ ተሰርቶ ይገኛሉ።

ሙዚየሙ ከምድር በታች ያለውን ሁለት ደረጃዎችን ጨምሮ 5 ወለሎች ያሉት ሲሆን፥ ከ1 ሺህ በላይ የመኪና ማቆሚያዎችን ጨምሮ በርካታ አዳራሾችንም አካቷል።
13.3K viewsedited  09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-11 01:54:44
"አድዋ-00 ሙዚየም"
15.3K views22:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-10 17:48:39
ፒያሳ
18.4K viewsedited  14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-10 14:22:22



ለፈገግታ
19.2K viewsedited  11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-10 12:46:50
18.9K views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-10 07:22:24
የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ያግዛሉ የተባሉና ሽንኩርትን ጨምሮ ሌሎችንም ምርቶች ከእርሻ በቀጥታ ወደ ገበያ የሚያቀርቡ 48 የግብርና ምርት አምራቾች በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙት 4 የገበያ ማዕከላት ሊገቡ መሆኑን ተነገረ

http://tinyurl.com/yybxybse
19.6K viewsedited  04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-10 07:18:27
የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደርጓል።

በ15 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በቀን በአማካይ እስከ 6 ሺህ ተገልጋዮችን የሚያስተናግደው መ/ቤቱ ከየካቲት 1/2016 አንስቶ የስራ ሰዓት ማሻሻያ አድርጓል።

በተደረገው የስራ ሰዓት ማሻሻያ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ፦

- ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ (በአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ) አገልግሎት ይሰጣል።

እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት የሚቆየው የስራ ሰዓት በሌሎች ቅርንጫፎችም በሂደት እንደሚጀመር ተነግሯል።

- ቅዳሜ ከጥዋት አንስቶ እስከ ቀኑ 11:30 ድረስ (በሁሉም ቅርንጫፍ) አገልግሎት ይሰጣል።

በአዲሱ የስራ ሰዓት ማሻሻያ አገልግሎቱ " ለምሳ ሰዓት " በሚል የማይቋረጥ ሲሆን በምሳ ሰዓትም አገልግሎት ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በዚህ መስሪያ ቤት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ከጥዋት 3:00 ሰዓት አንስቶ ሲሆን ለምሳ ተብሎ ደግሞ ሰራተኞቹ ወጥተው 8:00 ነበር የሚገቡት።
19.3K views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-09 05:37:23 በስደት የሚኖሩ ሀበሾች ሩም ሜት ሆነው በአንድ ቤት ውስጥ እንደሚኖሩ ይታወቃል። እዚህ አዲስ አበባ ግን ሁሉም ላጤ የቤት ኪራይ አናቱ ላይ ቢወጣበትም በብዛት ብቻውን እንጂ ደባል ሆኖ አይኖርም።

ለምን ይሆን ?

Tesfay G Neda
20.8K viewsedited  02:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-08 23:16:03
የማህበር ቤት ለመገንባት የወሰን ማስከበር ችግር የነበራባቸው መሬቶች ሙሉ በሙሉ እግዳቸው ተነሳ

የማህበር ቤት ለመገንባት የወሰን ማስከበር ችግር የነበራባቸው መሬቶች ሙሉ በሙሉ እግዳቸው መነሳቱን ክብርት ፅጌወይን ካሳ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ ኃላፊ ያሳወቁ ሲሆን ማህበራቱም ግንባታቸውን መቀጠል እንደሚችሉ ኃላፊዋ ገልፀዋል።

በ40/60 እና በ20/80 ተመዝጋቢ የነበሩ እና በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የተዘጋጁ 57 ማህበራት በወሰን ማስከበር ምክንያት የግንባታ ስራቸው ላይ እንቅፋት እንዳጋጠማቸው ከቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ በዚህ ሳምንት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቆ እንደነበር ይታወሳል።
13.1K views20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ