Get Mystery Box with random crypto!

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደርጓል።

በ15 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በቀን በአማካይ እስከ 6 ሺህ ተገልጋዮችን የሚያስተናግደው መ/ቤቱ ከየካቲት 1/2016 አንስቶ የስራ ሰዓት ማሻሻያ አድርጓል።

በተደረገው የስራ ሰዓት ማሻሻያ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ፦

- ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ (በአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ) አገልግሎት ይሰጣል።

እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት የሚቆየው የስራ ሰዓት በሌሎች ቅርንጫፎችም በሂደት እንደሚጀመር ተነግሯል።

- ቅዳሜ ከጥዋት አንስቶ እስከ ቀኑ 11:30 ድረስ (በሁሉም ቅርንጫፍ) አገልግሎት ይሰጣል።

በአዲሱ የስራ ሰዓት ማሻሻያ አገልግሎቱ " ለምሳ ሰዓት " በሚል የማይቋረጥ ሲሆን በምሳ ሰዓትም አገልግሎት ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በዚህ መስሪያ ቤት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ከጥዋት 3:00 ሰዓት አንስቶ ሲሆን ለምሳ ተብሎ ደግሞ ሰራተኞቹ ወጥተው 8:00 ነበር የሚገቡት።