Get Mystery Box with random crypto!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የሰርጥ አድራሻ: @housinginaddisababa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.66K
የሰርጥ መግለጫ

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2024-02-10 17:48:39
ፒያሳ
18.4K viewsedited  14:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-10 14:22:22



ለፈገግታ
19.2K viewsedited  11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-10 12:46:50
18.9K views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-10 07:22:24
የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ያግዛሉ የተባሉና ሽንኩርትን ጨምሮ ሌሎችንም ምርቶች ከእርሻ በቀጥታ ወደ ገበያ የሚያቀርቡ 48 የግብርና ምርት አምራቾች በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙት 4 የገበያ ማዕከላት ሊገቡ መሆኑን ተነገረ

http://tinyurl.com/yybxybse
19.6K viewsedited  04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-10 07:18:27
የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደርጓል።

በ15 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በቀን በአማካይ እስከ 6 ሺህ ተገልጋዮችን የሚያስተናግደው መ/ቤቱ ከየካቲት 1/2016 አንስቶ የስራ ሰዓት ማሻሻያ አድርጓል።

በተደረገው የስራ ሰዓት ማሻሻያ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ፦

- ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ (በአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ) አገልግሎት ይሰጣል።

እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት የሚቆየው የስራ ሰዓት በሌሎች ቅርንጫፎችም በሂደት እንደሚጀመር ተነግሯል።

- ቅዳሜ ከጥዋት አንስቶ እስከ ቀኑ 11:30 ድረስ (በሁሉም ቅርንጫፍ) አገልግሎት ይሰጣል።

በአዲሱ የስራ ሰዓት ማሻሻያ አገልግሎቱ " ለምሳ ሰዓት " በሚል የማይቋረጥ ሲሆን በምሳ ሰዓትም አገልግሎት ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በዚህ መስሪያ ቤት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ከጥዋት 3:00 ሰዓት አንስቶ ሲሆን ለምሳ ተብሎ ደግሞ ሰራተኞቹ ወጥተው 8:00 ነበር የሚገቡት።
19.3K views04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-09 05:37:23 በስደት የሚኖሩ ሀበሾች ሩም ሜት ሆነው በአንድ ቤት ውስጥ እንደሚኖሩ ይታወቃል። እዚህ አዲስ አበባ ግን ሁሉም ላጤ የቤት ኪራይ አናቱ ላይ ቢወጣበትም በብዛት ብቻውን እንጂ ደባል ሆኖ አይኖርም።

ለምን ይሆን ?

Tesfay G Neda
20.8K viewsedited  02:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-08 23:16:03
የማህበር ቤት ለመገንባት የወሰን ማስከበር ችግር የነበራባቸው መሬቶች ሙሉ በሙሉ እግዳቸው ተነሳ

የማህበር ቤት ለመገንባት የወሰን ማስከበር ችግር የነበራባቸው መሬቶች ሙሉ በሙሉ እግዳቸው መነሳቱን ክብርት ፅጌወይን ካሳ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ ኃላፊ ያሳወቁ ሲሆን ማህበራቱም ግንባታቸውን መቀጠል እንደሚችሉ ኃላፊዋ ገልፀዋል።

በ40/60 እና በ20/80 ተመዝጋቢ የነበሩ እና በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የተዘጋጁ 57 ማህበራት በወሰን ማስከበር ምክንያት የግንባታ ስራቸው ላይ እንቅፋት እንዳጋጠማቸው ከቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ በዚህ ሳምንት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቆ እንደነበር ይታወሳል።
13.1K views20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-08 22:22:24
አራዳ
13.4K views19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-07 19:56:26
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ለገበያው ደላሎች፣ ለኢንቨስትመንት አማካሪዎችና ባንኮች ፍቃድ መስጠት እጀምራለሁ አለ።

የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ሥራውን ከመጀመሩ በፊት ያለጥድፊያና በጥንቃቄ ሲሰራ መቆየቱን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ ተናግዋል።

ከየካቲት 4 ጀምሮ  ስቶክ ብሮከሮች፣ አማካሪዎችና የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ የሚሰጣቸው አሁን ለመጀመርያ ግዜ ወደ ሥራ ለመግባት የሚያስችል ማዕቀፍ የሚያሟሉ ሲሆን ነው ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በኢኮኖሚ ውስጥ እጅግ አጓጊና የማይመስል የአክስዮን ሽያጭና ግዢ፤ ሥርዓት እንዲይዝ የህግ ማዕቀፍ እየተሰናዳ መሆኑን ባለስልጣኑ ዛሬ ጋዜጠኞችን ጠርቶ ሲናገር ሰምተናል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የዳሬክተሮች ቦርድ ገበያውን ለመመስረት የሚያስፈልገውን 25 በመቶ ለመጋበዝ መተማመኛም ለመስጠት ወስኖ በኢትዮጵያ ንግድ ህግ መሰረት የተቀመጠውን የአምስት መስራቾች ቁጥር ለማሟላት ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር ያሉት 4 የልማት ድርጅቶች የኢትዮጵያ የሰነድ ነዋይ ገበያ አክሲዮን መስራች አባል ሆነው የኢትዮጵያ ሰነድ መዋለ ነዋይ ገበያ መቀላቀላቸው ይታወሳል።

ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ጋር በጋራ በመመስረቻው ስምምነት ላይ የፈረሙት ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ፣ የኢትዮጵያ መድህን ድርጅትና የብርሀንና ሰላም ማተሚያ ድርጅቶች ናቸው፡፡

ማንኛውም የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ኢንቨስትመንት ባንኮችን ለማቋቋም የሚፈልጉ ሁሉ የሚጠበቅባቸውንና ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት እስካሟሉ ድረስ ለምን ያህል ይሰጥ የሚለው በገደብ የተቀመጠ እንዳልሆነ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ሸገር
19.1K viewsedited  16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-07 19:21:41
በማህበር የተደራጁ የጋራ መኖሪያ ቤት ፈላጊዎች  በወሰን ማስከበር  ምክንያት እንቅፋት  ስላጋጠማቸው ግንባታቸው  መጓተቱ ተገለፀ

ከዚህ ቀደም በ40/60 እና በ20/80 ተመዝጋቢ የነበሩ እና በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የተዘጋጁ 57 ማህበራት በወሰን ማስከበር ምክንያት የግንባታ ስራቸው ላይ እንቅፋት እንዳጋጠማቸው ዛሬ በቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ማወቅ ተችሏል።

መግለጫውን የቢሮ ኃላፊዋ ክብርት ፅጌወይን ካሳ የሰጡ ሲሆን የተወሰኑ ሳይቶች ላይ ችግሮቹ ቢፈቱም አሁንም ግን አብዛኞቹ ሳይቶች  የወሰን ማስከበር ችግር እንዳለባቸው ገልፀዋል። 

በፍርድ ቤት የተያዙ ውሳኔዎችም እልባት  ሲያገኙ የሚታየው መዘግየት ተቀርፎ ማህበራቱ ወደ ግንባታ የሚገቡ ይሆናል ብለዋል።

የማህበራቱ ተወካዮችም በመግለጫው የተሳተፉ ሲሆን በአፋጣኝ ወደስራ ባለመግባታቸው በየጊዜው ለሚታየው  ለግንባታ ዋጋ ንረት መዳረጋቸውን ገልፀዋል።
17.8K views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ