Get Mystery Box with random crypto!

#AddisAbaba በአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ድንጋይ እና አፈር ተደርምሶ የ7 ሰዎች ሕይወት | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ ድንጋይ እና አፈር ተደርምሶ የ7 ሰዎች ሕይወት አፏል።

አደጋው የደረሰው በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ወረዳ 12 " ጠሮ መስጂድ " አካባቢ ነው።

ለሊት 11 ሰዓት ገደማ ለቤት ግንባታ የተከመረ ድንጋይ እና አፈር ከላይ ወደ ታች (ወደ ቤቱ) ተንዶ 3 ክፍል ያለው ቤት ላይ አደጋ ደርሷል።

በዚህም ቤት ውስጥ ተኝተው የነበሩ 7 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

ሟቾቹ ፦
የ4 ዓመት ህጻን ፣
ሶስት የ11 እና የ12 ዓመት ታዳጊዎች 
ከ25 እስከ 30 ዓመት ያሉ 3 ወጣቶች ናቸው።

ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች የሁለት ቤተሰብ አባላት እንደሆኑ ታውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ አደጋው የደረሰበት ምክንያት ምን እንደሆነ ለማወቅ ምርመራ ላይ ነው።

መረጃው የአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ነው።
@tikvahethiopia