Get Mystery Box with random crypto!

#የጨረታ_ማራዘሚያ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

#የጨረታ_ማራዘሚያ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጋር በመተባበር ያስገነቧቸውን  3,452 የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በሽያጭ ለማስተላለፍ የጨረታ ሰነድ በመሸጥ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ይህን ተከትሎ ከሕብረተሰቡ በመጣ ጥያቄ መነሻነት የጨረታ መክፈቻ ጊዜው ለ10 ቀናት የተራዘመ መሆኑ ታውቆ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች እስከ መጋቢት 02/2016 ዓ/ም ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ምሽቱ 1፡30 እንዲሁም እሁድ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ቀኑ 6፡00 በሁሉም ክፍለከተሞች ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት እንደሚችል እንገልፃለን፡፡


የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እና የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን