Get Mystery Box with random crypto!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ housinginaddisababa — Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች H
የቴሌግራም ቻናል አርማ housinginaddisababa — Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች
የሰርጥ አድራሻ: @housinginaddisababa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.64K
የሰርጥ መግለጫ

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 125

2022-08-26 19:29:25 ሕወሓት መቀሌ ከተማ በአየር ተደበደበች አለ
በወልቂጤ ከተማ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ በሌሎች የጉራጌ አካባቢዎችም መዛመቱ ተሰማ!
በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መጨምርም ሆነ ተከራይን የማስወጣት ክልከላው ተራዘመ።
በኢትዮጵያ ከፍተኛ የተፈጥሮ ነዳጅ ክምችት መኖሩ በዓለም አቀፍ ጥናት ተረጋገጠ!
ፖሊስ ለህወሃት ሰረጎ ገቦች ሀሰተኛ ሰነዶች የሚያዘጋጁትን ያዝኩኝ አለ!
ሩሲያ እና ህንድ በዶላር ላለመገበያየት ተስማሙ!
በአውሮፓ አስከፊ የተባለ ድርቅ መከሰቱን የአውሮፓ ሕብረት አስታወቀ!



18.6K views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 11:10:52 ህወሀት በአፋር ክልል ሽንፈት ማስተናገዱን ቀጥሏል!
የዶ/ር ደብረፅዮን ደብዳቤ እያነጋገረ ነው።
የህወሀት አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ሥር ዋለ!
የአሜሪካ ጦር ለተፈጸመበት የሮኬት ጥቃት የመልስ ምት ሰጠ!
ሩሲያ የህወሓትን የነዳጅ ዝርፊያ አወገዘች!
በለሚ ኩራ የመሬት ወረራ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች እየተለቀሙ ነው!
በጦርነቱ 20 በመቶ ግዛት ማታጣቱ ተገለጸ!
ሳማንታ ፓዎር  ህወሓትን  በፅኑ  አወገዙ!



19.6K views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 08:21:50
በአዲስአበባ የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለቀጣይ ስድስት ወራት ተራዘመ!!

የመኖርያ ቤት ኪራይ መጨመርም ይሁን ተከራይን ማስወጣት የሚከለክለው ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ጫናን ለመቀነስ በመኖርያ ቤት ተከራዮች ላይ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ እና ተከራይን ማስለቀቅን የሚከለክል ደንብ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ ይህም ደንብ በተለያየ ጊዜ እየተራዘመ ላለፈው አንድ አመት ተግባራዊ ተደርጎ ቆይቷል፡፡

ስለሆነም የከተማ አስተዳደሩ አሁን ያለውን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ እና የህብረተሰቡን የኑሮ ጫና ከግምት ባስገባ ወቅቱን በአብሮነትና በመተሳሰብ ለማለፍ ይረዳ ዘንድ ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት እንዲራዘም ወስኗል፡፡በመሆኑም ይህንን ክለከላ በመተላለፍ ተከራዮችን የሚያስወጡ እና የኪራይ ዋጋን የሚጨምሩ አካላት ላይ ማህበረሰቡ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ጥቆማውን ለከተማ አስተዳደሩ ማድረስ እንደሚችል ያስታውቃል፡፡
አጭር ቁጥር ፡- 9977

የሞባይል ስልኮች

09-00640830 / 09-00640789
20.3K views05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 06:11:49
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በህገ-ወጥ የመሬት ወረራ የመንግስትና የህዝብን ሀብት የሆነውን ንብረት በህገወጥ መንገድ ግለሰቦች ለማስተላለፍ ሲሞክሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን ለማስተካከል የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እየተወዱ መሆናቸው ይታወቃል። ይህን ተከትሎ ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ያሉ የመሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች ለጊዜው እንዲቆሙ ተደርገው የተለያዩ ማጣራቶች እየተደረጉ ይገኛሉ።

በክፍለ ከተማዉ ዋነኛዉና ወሳኝ የህዝብ ጥያቄ የሆነዉን የመሬት አገልግሎት ጥያቄዎች በህጋዊ መንገድ ለመመለስ የማስተካከያ እርምጃዎች እየተወሰዱ ባለበት በዚህ ወቅት በትናንትናው ዕለት 18/12/2014 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ስሙ ምስራቅ ሎቄ (የወረዳ መሻገሪያ) በሚባል ቦታ የየካ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ሠራተኛ የሆነች አንዲት ግለሠብ የክፍለ ከተማው ንብረት የሆነውን ጂ.ፒ.ኤስ ከአስተዳደሩ እውቅና ውጭ በመጠቀም የመንግስትና የህዝብ ንብረት የሆነውን መሬት ልኬት በመውሰድ ለግለሠብ ጥቅም ለማዋል ስትሞክር ከሦስት ባለ ጉዳዮች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ግለሰቧ በመንግስት የተሰጣቸውን ኃላፊነት እና ሙያዊ ስነ-ምግባር ወደ ኋላ በመተው እና በመጣስ እንዲሁም የለሚ ኩራ ክፍለከተማ ነባራዊ ሁኔታን ሽፋን በማድረግ ለግለሠቦች ጥቅም ሲባል የመንግስት እና የህዝብ ሀብትን ለመቀራመት እንዲሁም ላልታለመለት አላማ እና ተግባር እንዲውል በማድረግ ሙከራ ነዉ በቁጥጥር ስር የዋሉት።

የክ/ከተማ አስተዳደሩም በህግ ጥላ ስር የዋሉት ግለሠቦችን የፍርድ ሂደት ተከታትሎ ውጤቱን ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
MoAA
18.3K views03:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 21:58:49
የዕጣ ማውጣት ሂደቱ ላይ በተደረገው ኦዲት በተገኘው ግኝት ዕጣው እንዲሰረዝ መደረጉ ለአመታት ቆጥቦ ባለ እድል ለመሆን እየጠበቀ በነበረው ተመዝጋቢ ላይ ሊደርስ የነበረውን ጉዳትና ኢፍትሃዊነት በማስቀረቱ የከተማ አስተዳደሩ ውሳኔ ትክክለኛ ነው::

ለተፈጠረው ችግር በቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮና በራሴ ስም ይቅርታ እየጠየቅኩ የማጣራቱ ስራ ያልተጠናቀቀ ሲሆን በቀጣይ ከከተማ አስተዳደሩ በሚሰጡ አቅጣጫዎች የምንወሰ‍ዳቸውን እርምጃዎችና ቀጣይ ስራዎች ለመፈፀም የምንተጋ መሆኑን እገልፃለሁ::

ክብርት ያስሚን ወሃብረቢ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
5.5K views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 19:13:31
80 የጋራ መኖርያ ቤቶች ለነዋሪዎች ተሰጡ

በዛሬው እለት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የልቤ ፋና ትምህርት ቤት ሲገነቡ የቆዩትን ሁለት ህንፃ ጨምሮ በአጠቃላይ አራት ህንፃዎችና 80 የጋራ መኖርያ ቤቶች ተጠናቀው ተመርቁ።

ህንፃዎቹ በተገነቡበት ቦታ ላይ ለነበሩት ነዋሪዎችም እንደ ነበራቸው መኖሪያ ስፋትና መጠን በቤቶቹ በይፋ እጣ በማውጣት አስተላልፈዋል፡፡

እነዚህ ቤቶች ግንባታቸው ከተጀመረ በኋላ መሬቱን በሚፈልጉ ግለሰቦች ለ9 ወራት ያህል በፍርድ ቤት እግድ አስቁመው የነበረ ሲሆን፣ መስተዳድሩ በአጭር ጊዜ ቤቶቹን ገንብቶ በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ መተላፍ ችሏል፡፡

ቤቶቹን በተመጣጣን ዋጋ ገንብቶ ያጠናቀቀው ደግሞ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ምስጋና አቅርበዋል ፡፡
12.7K views16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 19:03:44 ከንቲባዋ 80 ቤቶችን አደሉ!
ኦነግ ሸኔ ከኢትዮጵያ በመሸሽ ጎረቤት ሀገራት መደበቁን መንግስት አሳወቀ!
ጥይት በጤፍ ቀላቅለው ወደአዲስ አበባ ሊያስገቡ የነበሩ ተያዙ!



12.6K views16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 11:17:21 የቤት እጣ አወጣጡ ሂደት እንዴት እንደተጭበረበረ ይፋ ሆነ!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት 2.6 ቢሊዮን ከሰረ!
የሳሙና ዋጋ እንደ ነዳጅ እንዳይሆን ተሰግቷል!



18.7K views08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 07:29:18 በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ ነው [አበይት ዜና]


20.1K views04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 19:52:30 ከ14ኛ ዙር የ20/80 እና ከ40/60 3ኛ ዙር እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮና የቤቶች ቢሮ የተለያየ እርምጃ የተወሰደባቸው አመራሮችና ባለሙያዎችን ስም ዝርዝር ይፋ ተደረገ።

በዚህም መሰረት፦

1ኛ. ዶ/ር ሙሉቀን ሃብቱ ቢሮ ሃላፊ ከሃላፊነታቸው የተነሱ

በቁጥጥር ስር የዋሉ፡-

1ኛ. አብርሀም ሰርሞሎ የዘርፉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ

2 ኛ . መብራቱ ወልደኪዳን፦ ዳይሬክተር

3ኛ. ሀብታሙ ከበደ፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

4ኛ. ዬሴፍ ሙላት፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

5ኛ. ጌታቸው በሪሁን፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

6ኛ. ቃሲም ከድር፦ ሶፍትዌር ባለሙያ

7ኛ. ስጦታው ግዛቸው፦ ሶፍትዌሩን ያለማ

8.ኛ. ባየልኝ ረታ፦ ሶፍትዌር ተቆጣጣሪ

9ኛ. ሚኪያስ ቶሌራ ፦ የቤቶች ኢንፎሜሽንና ቴክኖሎጂ ባለሙያ

10ኛ .ኩምሳ ቶላ፦ የቤቶች ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳሬክተር
26.6K views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ