Get Mystery Box with random crypto!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የሰርጥ አድራሻ: @housinginaddisababa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.66K
የሰርጥ መግለጫ

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 123

2022-09-02 00:13:05
የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የአገልግሎቶቹን ክፍያ በቴሌብር በኩል መፈጸም የሚያስችል ስምምነት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ተፈራረመ

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የአገልግሎት ክፍያ ሥርዓቱን በማዘመን፤ የአገልግሎቶቹን ክፍያ በቴሌብር በኩል መፈጸም የሚያስችል ስምምነት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራርሟል።

በዚህም መሠረት የኤጀንሲው ባለጉዳዮች ያለምንም ውጣ-ውረድ እና እንግልት የመኪና ሽያጭ ውል፣ የስጦታ፣ የውክልና፣ የብድር፣ የማህበር ምስረታ እና ቃለ ጉባኤ የመሳሰሉ ከ27 በላይ አገልግሎቶቹን ክፍያ በቴሌብር መፈጸም እንዲችሉ መደረጉ ተገልጿል፡፡

ባለጉዳዮች ኤጀንሲው የሚሰጣቸውን የክፍያ ማዘዣ ቁጥር በመጠቀም፤ በቴሌብር መተግበሪያ ወይም በአጭር ቁጥር (*127#) የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀላሉ መፈጸም እንደሚችሉም ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡
_
አዲስ ማለዳ
2.3K views21:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:29:00 የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ለ5 ሺሕ ተመዝጋቢዎች ዕጣ ሊያወጣ ነው

የጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ ትሬዲንግ ከዚህ ቀደም ጳጉሜ 03 ቀን 2014 አከናውነዋለሁ ብሎት የነበረውን የዕጣ ማውጣት ሥነሥርዓት ወደ መስከረም 10 ቀን 2015 መቀየሩን በዛሬው ዕለት አስታውቋል።

በዕጣ ማውጣት ሥነ ሥርዓቱ ላይም 5 ሺሕ የአገር ውስጥ ሮስካ ተመዝጋቢዎች እንደሚሳተፉበት ገልጿል።

የጎጆ ሃውሲንግ ትሬዲንግ መሥራችና ምክትል ዳይሬክተር ናደው ጌታሁን ዕጣ የሚወጣበት ጊዜ የተራዘመበትን ምክንያት ሲያስረዱ፤ በተመዝጋቢ አባላት የይራዘምልን ጥያቄና በአባላቱን ቁጥር በመጨመር የዕጣ ብዛቱንም ከፍ ለማድረግ በመታሰቡ መሆኑን ተናግረዋል።

በዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይም የ5 ሺሕ የአገር ውስጥ ሮስካ ተመዝጋቢዎች እጣ እንደሚወጣ፣ 4 ያለቁ ሳይቶችን ካርታ ለህብረት ሥራ ማህበራት የማስረከብ፣ 4 ያለቁ ሳይቶች የግንባታ ፍቃድ ርክክብ እንዲሁም አዲስ ለተመዘገቡ 4 መቶ አባላት የሚደራጁበትን ቦታ የማሳወቅ መርሃ ግብሮች እንደሚከናወን ምክትል ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

በተጨማሪም በዕለቱ ከጤና ሚኒስቴርና ከዳሽን ባንክ ጋር ለጤና ባለሙያዎች የመኖሪያ መንደር ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት እንደሚያደርግም ተገልጿል።

ጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ የተቋቋመው የዜጎችን የቤት ችግር ለመፍታት ቤት ፈላጊዎችን በህብረት ሥራ ማህበራት አደራጅቶ የቤት ባለቤት ማድረግ ነው ያሉት የጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ የማህበራት ማደራጀት ክፍል ሀላፊ አጋ ፉፋ ሲሆኑ፤ እነዚህንም ማህበራት ጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ የራሱን የማህበራት ክፍል በማቋቋም ክትትል እና ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የህብረት ሥራ ማህበራቱ የራሳቸው የክትትል እና ቁጥጥር ኮሚቴ እንዳላቸው የገለጹት አጋ በማህበር መደራጀታቸው በህብረት ሥራ ማህበረት አዋጅ መሰረት የግንባታ ቦታን የማገኘትና የግንባታ እቃዎችን ከግብር ነፃ የማስገባትን ዕድል ይሰጣቸዋል ብለዋል።

ጎጆ ብሪጅ ሃውሲንግ እስካሁን ድረስ 4 ሳይቶች፣ 8 ማህበራት እና 1 ሺሕ 55 አባላትን ማፍራት መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፤ መስከረም 11 በሚጀመረው አዲስ ምዝገባም የተሻሻለውን የሮስካ ክፍያ እና አሠራር ለተጠቃሚ በማስተዋውቅ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት 55 ሺሕ ብር የነበረወሰ ቅድመ ክፍያ ወደ 59 ሺህ ብር እንዲሁም በየወሩ ለ10 ዓመታት ይቆጠብ የነበረው የ2 ሺሕ ብር ወርሃዊ መዋጮ ወደ 2 ሺሕ 200 ብር ማሳደጉን አስታውቋል።
_
አዲስ ማለዳ
12.1K views11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:28:56
11.2K views11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 14:20:02 ነሐሴ 26፣ 2014

በአዲስ አበባ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የድጋፍ ሰጪ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች የተሽከርካሪያቸው ወንበር ከሚይዘው አቅም በታች እንድንጭን በመመሪያ በመገደዳችን ተቸግረናል አሉ፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በበኩሉ መመሪያው አገር አቀፍ ነው ይላል፡፡

ምህረት ስዩም

#Ethiopia #ShegerWerewoch #AddisAbeba #የድጋፍ_ሰጪ_ተሽከርካሪ #የአዲስ_አበባ_ትራንስፖርት_ቢሮ

ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
11.3K views11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:26:42 ነሐሴ 26፣ 2014

የገበያ ቅኝታችን

የ2015 የት/ት ዘመን እየተቃረበ ነውና የትምህርት ቁሶች ዋጋ ምን ይመስላል፡፡

ሐና ፍሰሐ

#Ethiopia #ShegerWerewoch #የገበያ_ቅኝት #የትምህርት_ቁሶች

ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
12.4K views08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 10:22:46 ግብፅ የኢትዮጵያን ድርድር አልቀበልም አለች
ፖለቲከኛው ከሀገር እንዳይወጡ መታገዳቸው እና መኖሪያ ቤታቸው መታሸጉ ተሰማ!
በመቶ የሚቆጠሩ ሰራተኞች ከአንድ የአዲስ አበባ ተቋም ወደ እስር ቤት ተጋዙ!
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲያቆም ጥሪ አቀረበ!
25 ሺህ ህፃናት በጦርነትና በመሳሰሉት ጠፍተዋል ተባለ!
በጦርነቱ በአፋር ክልል ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ!
ቻይና ሀያል የሆነችበት ሚስጥር ተገለጸ!
ሩሲያ ወደ አውሮፓ የሚሄደውን የጋዝ ማስተላለፊያ መሥመር ዘጋች!



12.9K views07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 22:42:37
የአደስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲያስገነባው የቆየው ባለ17 ብሎክ ዘመናዊው የልደታ ወጣት ጥፋተኞች ማቆያ ማእከል ፕሮጀክት ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡

ይህ አለም አቀፍ የጥፋተኞች አያያዝ መስፈርትን ያሟላና ወጣቶች ስራ ወዳድነትን እንዲሁም የስፖርትና የመዝናኛ ለወጣቶቹ ሁለንተናዊ ግንባታ የሚያግዙ ጉዳዮች የተካተቱበት ማእከል ግንባታ ከተማ አስተዳደሩ በፍጥነት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለፍሬ በቅቷል፡፡

20,186.42 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ አርፏል

6,000 ካሬ ሜትር ቦታ በአረንጓዴ ቦታ ተሸፍኗል

2,892 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የከተማ ግብርና ስራ ተሰርቶበታል

4364.53 ካሬ ሜትር ቦታ በውስጥ ለውስጥ የኮብልስቶን ንጣፍ ተሸፍኗል

በአጠቃላይ 1,213.38 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፉ 2 የወንዶችና የሴቶች ስፖርት ሜዳዎች ተሰርተውለታል

ፕሮጀክቱ አጠቃላይ 17 ብሎኮች ሲኖሩት የአስተዳደር ህንፃ፣የመማሪያ ክፍሎች፣ቤተ መፅሐፍት፣መመገቢና ማብሰያ ክፍሎች፣ክሊኒክና የምክር አገልግሎት መስጫ ክፍል፣ዎርክሾፕ፣የጠያዎች ማረፊያ፣3 የወንዶችና 2 የሴቶች ዶርሚተሪ፣ ላውንደሪ፣ ሁለገብ አዳራሽ እና ሌሎችም መሰረተ ልማቶች ተሟልተውለታል፡፡

MoAA
5.3K views19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 22:41:58
ሳፋሪኮም ኩባንያ በድሬዳዋ ለጀመረው የሞባይል አገልግሎት ለድምጽ በደቂቃ 50 ሳንቲም እንደሚያስከፍል ለአል ዓይን ኔትዎርክ በሰጠው ቃል ተናግሯል። የኢንተርኔት አገልግሎት ደሞ 120 ሜጋ ባይት በ10 ብር፣ 900 ሜጋ ባይት በ50 ብር እና ሁለት ጌጋ ባይት በ100 ብር ለደንበኞቹ እየሸጠ እንደሚገኝ ኩባንያው ገልጧል። ኩባንያው እስከ ቀጣዩ ዓመት ሚያዝያ ወር ድረስ የቴሌኮም አገልግሎቱን በ25 ከተሞች እጀምራለሁ ብሏል።

ዋዜማ
5.1K views19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 19:08:17
የመስከረም ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ያለምንም ለውጥ ይቀጥላል።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል።

ከነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረገው የነዳጅ ምርቶች ዋጋ የአውሮፕላን ነዳጅን ጨምሮ በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ ያለምንም ለውጥ ይቀጥላል።

ከሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የታለመት የነዳጅ ድጎማ አሠራር በተመሳሳይ በመስከረም ወር 2015 ዓ.ም እንደሚቀጥል ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
10.4K views16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 17:45:07 በመቀለው የአየር ጥቃት ሆስፒታል ኢላማ ተደርጓል ሲሉ የትግራይ ኃይሎች ከሰሱ
ህወሓት በወልቃይትና በዋግ ግንባር ጦርነት መጀመሩን መንግስት ገለጸ!
ከወለጋው ጭፍጨፋ የተረፉ ነዋሪዎች ጥበቃ እየተደረገላቸው አይደለም ተባለ፡፡
ጫማውን ከወራጅ ውሃ ለማውጣት የሞከረው የ8 ዓመት ታዳጊ በጎርፍ ተወስዶ ህይወቱ አለፈ
ሱዳን በካርቱም የሚገኙትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠየቀች።
ዩኒሴፍ "በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ግጭት የህፃናትን ህይወት ቀጥፏል" አለ
በቻይና የጥቃት ስጋት ውስጥ ያለችው ታይዋን "ለመልሶ ማጥቃት" ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች
ህንድ ህገ ወጥ ናቸው ያለቻቸውን ሁለት ሰማይ ጠቀስ መንትያ ህንጻዎች አፈረሰች!



11.4K views14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ