Get Mystery Box with random crypto!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የሰርጥ አድራሻ: @housinginaddisababa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.66K
የሰርጥ መግለጫ

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 122

2022-09-04 16:24:48 የውጭ ባንኮች የኢትዮጵያን ገበያ መቀላቀላቸውን አስመልክቶ የተለያዩ የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሐሳቦች እየተንጸባረቁ ነው። በዝርዝር ለመተቸትም ሆነ ለመደገፍ ፖሊሲዎች የአፈጻጸም መመሪያዎች እስኪወጡ መጠበቅ ተገቢ ስለሆነ፣ ለዛሬው ጥቅል ሐሳቦችንና ትኩረት የሚሹ ነጥቦች ብቻ በጨረፍታ አቀርባለሁ።

የዓለም አቀፍ ገበያ ድርጅትን (WTO) ለመቀላቀል አንዱ መስፈርት የሆነው ባንክና ቴሌን የመሳሰሉ ተቋማትን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ማድረግ ነው። በዚህ ምክንያትም የውጭ ሀገር ባንኮች የሀገራችንን የባንኪንግ ኢንደስትሪ የመቀላቀላቸው ጉዳይ የጊዜ ጉዳይ እንጂ አይቀሬ እንደነበር የሚታወቅ ነው።

አሁን ሊያወያየን የሚችለው ጉዳይ ባንኮቹ ገበያውን እንዲቀላቀሉ የተፈቀደበት ወቅት ተገቢ ነበር ወይ? የመንግስት፣ የብሔራዊ ባንክና ሀገር በቀል ባንኮች አቅምና ቅደም ዝግጅታቸውስ ምን ይመስላል? የገበያችንን ስርዓት ( Market Structure ) ምን ያህል ሕጋዊነትን የተከተለና ለወንጀልና ወንጀለኞች ያልተጋለጠ ነው። የግብር አከፋፈል፣ የመረጃ አሰባሰብና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂያችን ምን ያህል ጥብቅና ለውንብድናና ለጠለፋ ( Hacking ) ያልተጋለጡ ናቸው የሚሉትና መሰል ጉዳዮች ይሆናሉ

የውጭ ሀገር ባንኮች ወደ ሀገራችን የሚመጡት ገበያ፣ ነባርና አዲስ ደንበኛና ትርፍ ፍለጋ ስለሆነ ስለ ሀገር እድገት በተለይ የሚጨነቁና የማይጠበቡ ልማታዊ እሳቤም የሌላቸው እንደሆነ የሚታወቅ ነው። የሚቀላቀሉት ገበያ ያለበት ሀገርም ሀገራቸው ስላልሆነ ትርፍ እስካገኙ ድረስ በማንኛውም መንገድ ከማትረፍ ወደኃላ የማይሉና የሕግ አስገዳጅነት እንጂ የሞራል ጥያቄ እምብዛም የማይገዳቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ ታሳቢ መሆን አለበት። በተቃራኒው ደግሞ ሀገር በቀል ባንኮች ከትርፍ ባሻገር የሀገራቸው፣ የመንግስትና የልማታቸው አጋር ስለሆኑ ከሕግ ባሻገር በርካታ የውዴታ ግዴታና የሞራል ፈተና ስላለባቸው ውድድሩ የተለየ ጫና ሊያሳድርባቸው ይችላል።

የውጭ ሀገር ባንኮች በርካታ የውጭ ምንዛሬ ያመጣሉ የሚለውም እሳቤ የተጋነና በአብዛኛው የተሳሳተ መረጃ ነው። የውጭ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ በገፍ ይዘው መጥተው በብር የመለወጥ ፍላጎት አይኖራቸውም። በአብዛኛውም ያለችውን ገበያና የውጭ ምንዛሪ መቀራመት ላይ እንደሚያተኩሩ ከሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ይታወቃል።

ትርፋቸውንም በውጭ ምንዛሪ ከሀገር የማውጣት እድላቸው ጠባብ ስለሆነና ዋና መስርያ ቤታቸውን እንዲገነቡ ለሚሰበስቡት ብር ተመጣጣኝና ኃላፊነትና ግዴታ (Risk) እንዲወስዱ ካልተገደዱ በስተቀር ዘርፉ ቅርንጫፍ ተከራይቶ ቁሳቁስ በማሟላትና ገንዘብ በመሰብሰብ በትንሽ ኢንቨስትመንት የሚሰራ ስለሆነ ኢንቨስትመንታቸውንም ውስን በማድረግ ያለ በቂ ኃላፊነት፣ ስጋትና መተማመኛ ሊነግዱ ይችላሉ።

ሌላው ሀገር በቀል ባንኮች ከተደራሽነትና ሕዝብን ከማገልገል አኳያ ትርፍ ኖረም አልኖረ እንደ አቅማቸው ሁሉም ቦታ ቅርንጫፍ ይከፍታሉ። የውጭ ባንኮች ግን ሀብትና ኢኮኖሚያዊ አቅም በስፋት የሚታይባቸው አካባቢዎች ላይ ብቻ አትኩረው ሊሰሩ ስለሚችሉ አቅም ባለበት ቦታ ላይ ብቻ የሚኖረው ውድድሩ በሚፈጥረው ሽሚያ በሚፈጠረው አቅም መዳከም ምክንያት ቀሪው አካባቢና ማህበረሰብ የባንክ አገልግሎት ላያገኝ ይችላል።

ሌላው ሀገራችን ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ አስቀማጭና ተበዳሪዎች በጥቂት መቶዎች የሚቆጠሩ ሰለሆኑ እነዚህን ደንበኞችና ገበያ (Niche Market) ላይ ብቻ በማተኮር ወይም ከፍተኛ እጥረት ያለበት የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትን በማባበያነት በመጠቀም፣ የኢንዱስትሪውን አቅም ከ70 በመቶ በላይ በቀላሉ ለመቆጣጠር ይችላሉ። ይህ ደግሞ የተዛባና ወደ አንድ ጎን ያጋደለ (Economic imbalance) ፣ ኢ-ፍትሐዊ ወይም ሚዛናዊ ያልሆነ ውድድር (Unfair Competition) ሊፈጥሩ ይችላሉ።

በዚህ መንገድ ከሞላ ጎደል ገበያውን መሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ስለሚችሉም የፈለጉትን የአገልግሎት ዋጋ በመጣል፣ ወለድ በመተማንና ለፈቀዱለትና ለሚመስላቸው ዘርፍ ብቻ በማበደር ኢኮኖሚውን ወደ ፈለጉበት በመጠምዘዝ ልማታዊ እድሎችን እስከማደናቀፍ ሊደርሱ ይችላሉ። የውጭ ምንዛሪ ሲፈቅዱ የሀገራቸው ምርት ብቻ እንዲገባ በማድረግም ሀገሪቱን የሸቀጥ ማራገፊያ ( Damping ground) ሊያደርገት ይችላሉ። እንደዚህ ዓይነት አካሄዶች በማደግ ላይ ባሉ በርካታ ሀገራት ላይ ያጋጠመ ፈተናና ችግር ነው። በአንዳድ ሀገራትም አንዴ ባንኮቹ ጡንቻ ካፈረጠሙ በኃላ ለተለያዮ ኃይሎች የፖለቲካ መሳርያ በመሆን የመንግስትን እጅ እስከ መጠምዘዝ የደረሱበት ሁኔታም ታይቷል።

የውጭ ባንኮች ወድ ሀገር ውስጥ መግባታቸው በጠንካራ ጎንነት ሊወሳ የሚችለው የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ዘመናዊ የባንክ ሙያና እውቀት ስርጸት፣ አዳዲስ የማኔጅመንትና የአመራር ጥበብ ሽግግር የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። ከዚህም በላይ ለነባርና ብቃት ላላቸው የባንክ ሰራተኞችን ጨምሮ ለአዳዲስ ስራተኞችም የስራ እድል ይፈጥራል።

የውጭ ባንኮቹ ሀገር ውስጥ መኖራቸው በወጭና በገቢ ንግድ ላይ የነበረውን የተንዛዛ አሰራርና ተደራራቢ የክፍያ ስርዓት ሊቀንስ ይችላል። ኢንደስትሪው በስርዓትና በሕግ ከተመራም የዘመነና ጤናማ ውድድርን ሊያስከትል ይችላል። በአጠቃላይ ዘመናዊ አሰራር በማስተዋወቅ አዲስ ሃብት ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ በማሸጋገርና በማበልጸግ የተቀማጭም ሆነ የውጭ ምንዛሪ ይበልጥ እንዲሳለጥና Economics of Scale ከፍ እንዲል ሊያግዝ ይችላል።
Mushe Semu
3.3K viewsedited  13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 16:24:34
3.3K views13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 14:08:18
የካርቱም አየር ማረፊያ በጎርፍ መጥለቅለቁ ታውቋል።
6.6K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 13:36:38
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ በቀረበ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሳኔዎች

የባንክ ዘርፍን ለውጭ ኢንቨስተሮች ከፍት ማድረግ የዘርፉን አገልግሎቶች በእውቀት እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ፤ የአገራችን ኢኮኖሚ ከአለም አቀፍ ገበያ ጋር ያለውን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፣ የፋይናንስ ዘርፉን ተወዳዳሪነት፣ ውጤታማነትና ቀልጣፋነት በመጨመር በቂ የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር እና የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት እንዲሳለጥ፤ የሚፈጠረው የስራ እድል እንዲጎለብት እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ውጤታማነትን እና አለምአቀፍ ተወዳዳሪትን በማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድግት ለማረጋገጥ የሚያስችል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

#PMOEthiopia
9.5K views10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 13:15:09
የኢትዮጵያ ቴሌኮም ለኢንተርኔት በ10 ብር ፓኬጅ ለ አንድ ሰአት ያለገደብ unlimitedly ያስጠቅማችኃል።

የኢትዮጵያ ቴሌኮም ለአንድ ደቂቃ ደቂቃ ድምፅ ከ ፒክ ሰዓት ውጪ 35 ሳንቲም ይጠይቃችኃል በጥድፍያ ሰዓት ደግሞ 50 ሳንቲም የአገልግሎት ክፍያ ይጠይቃል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደግሞ ለአንዲቷ ደቂቃ ድምፅ 50 ሳንቲም ይጠይቃል።

ሳፋሪኮም በ ኢትዮጵያ ፓኬጅ ልክ እንደ ኢትዮጵያ ቴሌኮም አማራጮች ባያበዛም ጀምሯል።

የኢትዮጵያ ቴሌኮም ለኢንተርኔት በ10 ብር ፓኬጅ ለ አንድ ሰአት ያለገደብ unlimitedly ያስጠቅማችኃል።

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለ 120 ሜጋ ባይት ፓኬጅ 10 ብር ይጠይቃችኃል።

ይህ ማለት እንደምትመለከቱት HD ወይም high definition standard pixels ይወሰናል ማለት ነው።

ኢትዮ ቴሌኮም በ 60 ብር 1.1gb ይጠይቃችኃል

1.1gb ማለት 1100mb ማለት ነው (1*10 z power of 9)

በሌላ ቋንቋ ኢትዮ ቴሌኮም ለ አንዲቷ ቢት or mb 0.055 ሳንቲም ይጠይቃችኃል ማለት ነው።

ሳፋሪኮም በ 50 ብር 900mb ይሸጥላችኃል ( 1*10 z power of six)

በሌላ ቋንቋ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለ አንዲቷ ቢት or mb በተመሳሳይ 0.055 ሳንቲም ይጠይቃችኃል ማለት ነው።

እዚህ ላይ የገንዘብ ለውጥ ያለው ቢመስልም ለአንድ ቢት mb ክፍያው 0.055 ሳንቲም ነው።

የኢትዮጵያ ቴሌኮም በ 105 ብር 2.2gb ይሸጥላችኃል።

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለ 2gb 100 ብር ክፈሉኝ ይላችኃል ማለት ነው።

@tenbusha
9.2K views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 13:01:50
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በዲቦራ ፋውንዴሽን የተገነባውን መዋዕለ ህጻናት መረቁ

በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የተገነባው መዋዕለ ህጻናቱ፥ ዘጠኝ የመማሪያ ክፍሎች እና ሌሎች የአስተዳደር ቢሮዎች ያሉት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በምርቃ መርሐ ግብሩ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ም/ሃላፊ ወ/ሮ መገርቱ መሃመድ፣ የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በሪሶ ተመስገን እና የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራችና የቦርድ ሊቀ መንበር አቶ አባዱላ ገመዳ ተገኝተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ህጻናት የቤተሰብና የሀገር ተስፋ በመሆናቸው ህጻናቱ የትምህርትና የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ሁሉም ድጋፍ ሊያደርግላቸው ይገባል ብለዋል፡፡
FBC
8.8K views10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 12:45:02
የ ቃሊቲ መንገድ
9.5K views09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 18:46:19 አምባሳደር ስለሺ በቀለ ብፁዓን ጳጳሳትን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ!
የኢትዮጵያን ወርቅ ሲሰርቁ የነበሩ የውጪ ዜጎች ተያዙ
መከላከያ በወልቃይት ግንባር ድል ቀንቶኛል አለ
በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያለአግባብ ስሜ ተነስቷል ላለችው ሱዳን ምላሽ ሰጠ!
በአሰቃቂ ሁኔታ ለተገደሉት ህፃናት አስቸኳይ ፍትህ እንዲሰጥ ተጠየቀ!
የወልዲያ ከተማ አስተዳደር ነጋዴና አገልግሎት ሰጭዎችን አስጠነቀቀ
ባይደን የትራምፕ ደጋፊዎች ለአሜሪካ ዴሞክራሲ ‘ስጋት’ ናቸው አሉ



10.2K views15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 15:30:40
በልደታ ክፍለ ከተማ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች መካከል 3 ባለ 11 ወለል የሆኑ ህንፃዎችን የያዘ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ተጠናቋል። ይህ የመኖሪያ ቤት ፕሮጀክት ከ150 በላይ የሚሆኑ እማውራና አባውራዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

MoAA
12.4K views12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 09:40:31 የሕውሓት ኃይሎች ከአማራ ክልል አካባቢዎች እንዲወጡ ብሪታንያ  ጠየቀች!
የቤት ሠራተኛዋ ሁለት ህፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ገደለች!
ለውጭ ማስታወቂያ የሚሆን መሬት በጨረታ ሊቀርብ ነው!
ከንቲባው ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸው ተሰማ!
የእሳት አደጋ ሰራተኞች በእሳት ተበሉ!
የፖለቲካ ልዩነት የአገርን ጠላት በጋራ ከመመከት አይገታንም ሲሉ ሚኒስትሩ ተናገሩ!
ታይዋን የመጀመሪያውን ተኩስ ቻይና ተኮሰች



7.5K views06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ