Get Mystery Box with random crypto!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በዲቦራ ፋውንዴሽን የተገነባውን መዋዕለ ህጻናት መረቁ በለገጣፎ ለገዳዲ ከተ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በዲቦራ ፋውንዴሽን የተገነባውን መዋዕለ ህጻናት መረቁ

በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የተገነባው መዋዕለ ህጻናቱ፥ ዘጠኝ የመማሪያ ክፍሎች እና ሌሎች የአስተዳደር ቢሮዎች ያሉት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በምርቃ መርሐ ግብሩ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ም/ሃላፊ ወ/ሮ መገርቱ መሃመድ፣ የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ በሪሶ ተመስገን እና የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራችና የቦርድ ሊቀ መንበር አቶ አባዱላ ገመዳ ተገኝተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ህጻናት የቤተሰብና የሀገር ተስፋ በመሆናቸው ህጻናቱ የትምህርትና የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ሁሉም ድጋፍ ሊያደርግላቸው ይገባል ብለዋል፡፡
FBC