Get Mystery Box with random crypto!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የሰርጥ አድራሻ: @housinginaddisababa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.66K
የሰርጥ መግለጫ

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 119

2022-09-21 22:20:03
በአዲስ አበባ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ዙሪያ ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ አልተወጡም በሚል የመንግሥትን ስራ በማይመች አኳኋን በመምራት በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ እና 11 ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው።
14.5K viewsedited  19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 19:11:53 ዘመነ ካሴ በፖሊስ ተያዘ

የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር መነጋገራቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር መጠነ ሰፊ ውጊያ መጀመሩ ተዘገበ

እናትና ልጅ በደራሽ ውሐ ተወሰዱ!
በድብቅ የተከማቸ ከ25 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ተያዘ።

በአዲስ አበባ ከተማ የጦር መሳሪያዎች ከተጠርጣሪዎች ጋር ተያዙ!
ከ8ሺህ በላይ ታራሚዎች በይቅርታ ተለቀቁ
ከ54 ሺህ በላይ ሰዎች ለረሀብ እንደተጋለጡ ተገለጸ።



15.5K views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 18:12:51
በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ዙሪያ በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ እና 11 ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው

በአዲስ አበባ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ዙሪያ ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ አልተወጡም በሚል የመንግሥትን ስራ በማይመች አኳኋን በመምራት በከባድ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ እና 11 ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው።

የአዲስ አበባ የቴክኒክ ሙያ ስልጠናና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱን ጨምሮ 11 ግለሰቦች የመንግሥትን ስራ በማይመች አኳኋን በመምራት ከባድ የሙስና ወንጀል ነው የተከሰሱት።

ከተከሳሾቹ መካከል ዶ/ር ሙሉቀን ይመሩት ከነበረው መስሪያ ቤት አብርሃም ሴርሜሎ፣ ኩምሳ ቶላ እና መብራቱ ኪዳነማሪያም እንዲሁም ከቤቶች አስተዳደር ባዩልኝ ረታ፣ ሚኪያስ ቶሌራ እና ዮናስ ወ/ጊዮርጊስ ይገኙበታል።

አቢሲ እንደዘገበውጨበግለሰቦቹ ላይ የተመሰረቱት ክሶችም የመንግሥትን ስራ በማይመች አኳኋን መምራትና በስልጣን ያለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል እንዲሁም በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ የማቅረብ ናቸው።
15.2K views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 16:05:30 እየተለመደ ያለው ሕገወጥነት...

ይህ በቀጭን መመሪያ በስራ ላይ ያለ ሕግን መጋድ እየተለመደ የመጣ ሕገወጥነት ነው። እኔ እስከማውቀው በፊንፊኔ ዙርያ ሰበታ ከተማ የቤት ስም ዝውውር ከቆማ ወራቶች ተቆጥሯል። የአዲስ አበባ አሰተዳደርም ይህንን ተግባር በተደጋገም ይፈጽማል። በቃ በአንድ ሌሊት የግቢይት እንቅስቃሴ ይታገዳል። ለምን ስባል ሕገወጥነትን ለመከላከል ይላሉ። ሕገወጥነትን መከላከል የሚቻለው መብትን በመደፍጠጥ ሳይሆን ጠንካራ ተቋሚ በመገንባት ነው። አንድ ሰው የእራሱን ንብረት መሸጥ መለወጥ ካልቻለ literally የዛ ንብረት ባለቤት አይደለም። ይህን መሸጥ መለወጥ ሲያከናውን በስሙ ወይንም በተወካዩ በኩል ማከናወን እንደሚችል ሕግ ለግለሰቦች የሰጠው መብት ነው። ይህ አካሄድ ትክክል ካልሆነ ሕጉን ወደ ፓርላማ ወስዶ ማሻሻል እንጅ የግለሰቦችን መብት በመመሪያ ማገድ ሕገወጥነት ነው።
መሀሙድ ዴኮ
15.5K views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 11:35:33
በርካታ ፈተናዎችን በድል አድራጊነት ወደ ተሽጋገርንበት የ2015 አዲስ አመት እንኳን አደረሰን፡-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

በርካታ ፈተናዎችን በድል አድራጊነት ወደ ተሽጋገርንበት የ2015 አዲስ አመት እንኳን አደረሰን፤ አደረሳችሁ ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለፁ፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ በጦር ሃይሎች ጠቅላይ መምሪያ በየሶስት ወሩ እየታተመ በሚወጣው ‘መከታ’ መጽሔት ላይ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ለአዲሱ ዓመት የ’እንኳን አደረሳችሁ’ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም “የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም የጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን አመራሮችና አባላት በርካታ ፈተናዎችን በድል አድራጊነት ወደ ተሽጋገርንበት የ2015 አዲስ አመት እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ” ብለዋል።

ከቀደመው 2013 የተሻገረውን ጨምሮ 2014 ዓ.ም ሀገራችን በርካታ ፈተናዎችንና የሕልውና አደጋዎችን የተጋፈጠችበት ጊዜ ነበር ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ በሕዝባችን፣ በመሪዎቻችን፣ በመከላከያና በፀጥታ ሃይሎች የተቀናጀ ትግል ፈተናዎቹን በፅናት ያለፍንበትና ዓመቱን በድል አድራጊነት የተሽጋገርንበት ወቅት ነው ብለዋል።

“እኛ ወታደሮች ብንሆንም የሰላምን አማራጭ እናስቀድማለን ፤ሰላም ለሀገር ዕድገትና ለሕዝባችን ሕይወት መለወጥ አስፈላጊ መሆኑን ስለምናምን ጦርነት ካልተከፈተብን በስተቀር ወደ ጦርነት አንገባም” በማለት ተናግረዋል።

የሀገራችንን ሕልውና አደጋ ላይ ለመጣልና ሕዝባችንን ለማጎሳቆል ያለመ ኃይል ከየትኛውም አቅጣጫ ውጊያ ከከፈተብን ግን በአጭር ጊዜና በአነስተኛ ኪሣራ መመከት የሚያስችል ቁመናና ዝግጁነት ላይ እንደምንገኝ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማረጋገጥ እወዳለሁ ሲሉም ገልጸዋል፡፡
8.1K views08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 11:35:06
7.8K views08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 19:38:11 የሕወሓት አባላት ከእስር ቤት በምህረት ሊለቀቁ ነው ተባለ !
አዲስ አበባ ከሽብር አደጋ ለጥቂት ተረፈች!
አሜሪካ ሕወሓትን ለማስወገድ ተስማማች!
የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮዽያ የውስጥ ጉዳይ ገብቶ የመፈትፈት መብት የለውም ስትል ሩሲያ ገለጸች!
ከጋምቤላ ህዝብ ግማሹ መፈናቀሉን ክልሉ አስታወቀ !
ቻይና እና አሜሪካ በቀጣዩ ዓመት ጦርነት እንደሚጀምሩ ተተነበየ!
ፕሬዝዳንት ፑቲን ለተቸገሩ ሀገራት ስንዴ ሊልኩ ነው!



12.5K views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 19:32:12
12.0K views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 04:39:15
እያንዳንዱ ኢንቺ የኢትዮጵያ መሬት የትግራይ ህዝብ ነው:: ኢትዮጵያውያንም በትግራይ ክልል ካለው እያንዳንዱ ኢንች መሬት ባለቤት ናቸው:: ትግራይ ከእንግዲህ የሽብርተኛውና የወንጀለኛው ህወሓት መሸሸጊያ እትሆንም::
14.7K views01:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ