Get Mystery Box with random crypto!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የሰርጥ አድራሻ: @housinginaddisababa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.66K
የሰርጥ መግለጫ

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 120

2022-09-09 19:29:31
የፀጥታው ምክር ጣልቃ ይግባ እያሉ ነው።
15.5K views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 18:52:34 የህወሃት ሀይል ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ ተሰማ!
ህወሓት በሱዳን በኩል ያደረገችው ማጥቃት ከፍተኛ ዋጋ አስከፈላት!
ኦነግ ሸኔ በወለጋ አራቱም አቅጣጫ ከበባ ማድረጉ ተሰማ
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከህወሓት ባለሥልጣናት ጋር ተነጋገሩ
ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤት መሆኗን በይፋ አወጀች
ሩሲያ የተጣሉባት ማዕቀቦች ካልተነሱ ወደ አውሮፓ ነዳጅ እንደማትልክ ገለጸች!



15.4K views15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 11:12:45 የህወሓት ሀይሎች ከመቀሌ እያመለጡ መሆኑ ተናገረ!

በማይታወቁ ድሮኖች እየተሰለልኩ እንደሆነ ደርሼበታለሁ ስትል ኢትዮጵያ አስታወቀች!

ህወሃት እየሸሹ ወደኋላ የሚመለሱ ታጣቂዎቹን እየረሸነ መሆኑ ተሰማ!

ግብጽ እና ኢትዮጵያ ኬንያ በደገሰችው ድግሥ ተጠሩ!
ምርጫ ቦርድ የእነ አቶ የሽዋስ አሰፋን የአዲስ ፓርቲ ምስረታ ጥያቄ ውድቅ አደረገ
የም/ጠቅላይ ሚንስቴሩ ረዳት የቀብር ስነስርዓት ዛሬ በሥላሴ ቤተክርስቲያን ይፈጸማል!



16.1K viewsedited  08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 22:11:58
ነገ ጷጉሜ 4 ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት በመዲናዋ ይሰጣል።

ውድ የከተማችን ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ !!!
ሁሌም ስናገለግላችሁ ክብር ይሰማናል !!!
ነገ በአገልጋይነት ቀን በትራንስፖርት አገልግሎት የሚደርስባችሁን እንግልት ለማቃለል አሥተዋፅዖ የሚያደርጉ አዳዲስ ዘመናዊ አዳዲስ አውቶቡሶችን ይዘን እንኳን አደረሣችሁ ስንል ደስታ ይሰማናል።

የአገልጋይነት ቀንን ምክንያት በማድረግ እነኚህን አዳዲስ አውቶቡሶችን ጨምሮ ፣ ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አግልግሎት ድርጅት እና አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድረስ ያለምንም ክፍያ በነፃ አገልግሎት ይሰጣሉ።

ጷጉሜን 4 የአገልጋይነት ቀን ብለን የሰየምነው ሁሉም ዜጋ የአገልጋይነት ባህልን በማዳበር ሁለንተናዊ ለውጥ ማምጣት እንድንቸል በማድረግ መነሳሳትን ለመፍጠር ነው።
መጪው ዘመን የደስታ፣ የፍስሃ እና የስኬት እንዲሆን እየተመኘ አገልግሎቱን በነፃ እንድትጠቀሙ ከተማ አስዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።
MoAA
17.2K views19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 19:22:09 በብልሹ አሰራር ምክንያት ለ3 ሳምንታት ተዘግቶ የነበረው ጽ/ ቤት ስራ ጀመረ

ጦርነቱ ተጋግሎ በሁሉም ግንባሮች የህወሓት ጦር ሽንፈት እንደገጠመው ታወቀ።
በኢትዮጵያ ጉዳይ ዛሬ ሊካሄድ የነበረው የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ በተፈጠረው አለመግባባት ለሳምንት ተራዘመ !
የኅዳሴ ግድብን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ 60 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተባለ!
ቱርክ ምዕራባውያንን ወቀሰች



16.2K views16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 13:10:57
የመሬት ልማት እና አስተዳደር ጽ/ቤት ስራ መጀመሩን አበሰረ፡፡

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ መሬት እና ልማት አሰተዳደር ጽ/ቤት ባለሙያዎች እና አመራሮች ህብረተሰቡን ጎንበስ ብለው ይቅርታ በመጠየቅ ያለምንም መማለጃ እና ጉቦ በቅንነት እና በተቀላጠፈ አሰራር ለመካስ ቃል ገብተው ዛሬ ጳጉሜ 03 ቀን አገልግሎቱን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

በእለቱ የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን ሮባ፣የመሬትልማትና አስተደደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገረመው ወርቁ፣የጽ/ቤቱ ምክትል አስተዳደር አቶ ሀብታሙ ዋናያ እንዲሁም የጽ/ቤቱ ባለሙያዎች ተገኝተው ስራ መጀመሩን አብስረዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ጥላሁን ለደንበኞች በተደረገው አቀባበል ወቅት ባደረጉት ንግግር ያሉትን በርካታ ችግሮች ለማስተካከል ብለን አገልግሎቱን በመዝጋታችን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ አሁን በተቻለ ፍጥነት የአመራር ለውጥ አድርገናል፡፡ተጠያቂ መሆን ያለበትን አካል ተጠያቂ እንዲሆን እያደረግንም እንገኛለን፡፡

ይሁን እንጂ እኛ አመራር ስለቀየርን ብቻ ለውጥ ይመጣል ብለን አናስብም፡፡ነገር ግን ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት ለመስራት ቆርጠን ተነስተናል፡፡ የተበደለውን አርሶ አደር እና ነዋሪ በሚገባ እንክሳለን፡፡ያን ማድረግ ካልቻልንም ተሸንፈናል ብለን በራሳችን እንለቃለን እንጂ እኛ እዚህ ቦታ እያለን ማንም ሊንገላታ አይገባም ብለዋል፡፡

ተገልጋዮችም አመራሩ በቁርጠኝነትና በቅንነት የሚሰራ ከሆነ በጋራ ለመስራት እና ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ክ/ከተማዋንም የለማች እና ሞደል ክፍለ ከተማ ለማድረግ የበኩላቸውን አስታዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ተናግረዋል፡፡

ለሚ ኩራ ኮሚዩኒኬሽን
ጳጉሜ 03/2014 ዓ.ም
16.9K views10:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 09:57:23 ሕዝባዊ ማዕበልን በሕዝባዊ ማዕበል ለመመከት ውሳኔ ተላለፈ!

ህፃኑን በእሳት ያቃጠሉት በእስራት ተቀጡ!

አዲስ በተቀሰቀሰው ግጭት የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ 70 ሺህ ተሻገረ!

ከጦርነት ሀገር የተገዛው የእርዳታ እህል  ጦርነት በምታካሂደው ኢትዮጵያ ገባ!
"ግጭቱ በጦርነት አይፈታም" ስትል አሜሪካ አሳሰበች
ጋዜጠኛዋ ለሦስተኛ ጊዜ ታፍና እንደተወሰደች ተሰማ!
ፑቲን "የዩክሬኑ ጦርነት ሩሲያን እያጠናከራት ነው" አሉ!



1.6K views06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 02:32:31 የለሚ ኩራ ክ/ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ስራ ሊጀምር መሆኑን ይፋ አደረገ፡፡

ጽ/ቤቱ በሚሰጠው አገልግሎት ህብረተሰቡን ለእንግልትና ለምሬት ዳርጓል፡፡ተገልጋዩም ማግኘት ያለበትን ህጋዊ አገልግሎት ማግኘት ባለመቻሉ መማለጃን እየተጠየቀ ለብዝበዛ ተጋልጧል በማለት ህብረሰቡ በተደጋጋሚ ቅሬታን ማንሳቱን ተከትሎ ላለፉት ሶስት ሳምንታት ተቋርጦ የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ አስፈላጊውን ውይይት እና ማጣራት አካሂዶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መግባባት ላይ በመድረሱ ስራውን ነገ ጳጉሜ 03 ቀን በይፋ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

አዲሱ የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ገረመው ወርቁ እንደገለጹት በአንድም ሆነ በሌላ ምክኒያት ህዝባችን መንገላታቱን መንግስትም መጎዳቱን ተነጋግረን ከመግባባት ላይ ደርሰናል፡፡ምንም እንኳን ከመቅጣት ማስተማር ላይ ብናተኩርም በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ህዝብን የጎዱ አካላት በህግ ይጠየቃሉ፡፡እየተጠየቁም ነው፡፡ በመሆኑም ነገ አገልግሎቱን ስንጀምር የበደልነውን ህዝብ ዝቅ ብለን ይቅርታ በመጠየቅ ለመካስ ዝግጁነታችንን አጠናቀናል ብለዋል፡፡

አቶ ገረመው ከነገ ጀምሮ ባሉ ቀናት በነባር ይዞታዎች ላይ ከስም ዝውውር እዳ እገዳ፣ከፍርድ ቤት ክርክር አገልግሎት፣ ከዋስትና ፣ከመንግስት ፕሮጀክቶች ልማት እና ከሊዝ ክፍያ ጋር የሚያያዙ አገልግሎቶችን መስጠት እንደሚጀመር ገልጸው ከመብት ፈጠራ እና ከዚህ ቀደም ተጣርተው መጡ ከተባሉ የአርሶ አደር ፋይሎች ጋር የሚገናኙ አገልግሎቶች ግን ሁኔታዎች በደንብ እስከሚጣሩ እና ህብረተሰቡ እና መንግሥት ወደ ሚፈልገው አገልግሎት በትክክል እስኪመጣ ለተወሰነ ጊዜ ምናልባትም እስከ አንድ ወር ድረስ እንደማይጀምሩ ተናግዋል፡፡

በነበረን ቃለ መጠይቅ ሀሳባቸውን የሰጡን የጽ/ቤቱ ባለሙያዎችም በተፈጠረው ነገር በጣም አዝነናል፣ተጸጽተናል፡ህብረተሰቡን ይቅርታ ጠይቀን በተሻለ አገልግሎት ለመካስም ቆርጠን ተነስተናል በማለት ያላቸውን ዝግጁነት አረጋግጠውልናል፡፡

ለሚ ኩራ ኮሚዩኒኬሽን
ጳጉሜ 02/2014 ዓ.ም
8.2K views23:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 02:32:27
7.8K views23:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 11:47:37
ሁዋዌይ በየትኛውም የዓለም ክፍል በሳተላይት የሚሰራ ሜት 50 ስማርት ስልክ ይፋ አደረገ

ስማርት ስልኩ ከጂ.ፒ.ኤስ ተመሳሳይነት ባለው በቻይናው ቤይ-ዶው ናቪጌሽን ሳተላይት ሲስትም (BDS) ኔትዎርክ አማኝነት በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚባይል ኔትዎርክ ባይኖርም መስራት ይችላል።

ይህም ባትሪው ሊዘጋ 1 ፐርሰት እየቀረው 3 ሰዓት እንደቆይ ማድረግ እንደሚያስችልም ኩባያው አስታውቋል።

ስማርት ስልኩ ከጀርባው 4 የካሜራ ሌንሶች የተገጠሙለት ሲሆን፤ ሌንሶቹም 50 ሜጋ ፒክስል፣ 13 ሜጋ ፒክሰል እና 12 ሚክስል ናቸው።

ከፊትለፊት አሊያም ሰለፊ ካሜራው ደግሞ 1 ሲሆን፤ የሌንሱ ምስል የማንሳት ጥራትም 13 ሜጋ ፒከስል ነው ተብሏል!!
4.9K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ