Get Mystery Box with random crypto!

Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የሰርጥ አድራሻ: @housinginaddisababa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 68.66K
የሰርጥ መግለጫ

The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates.

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 117

2022-09-24 17:47:25 የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ከ44 ሺህ በላይ የሚሆኑ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ነባር ካርታዎችን ኦዲት አድርጎ ማስወገዱን አሳወቀ ።

በከተማ ደረጃ በወረደው አቅጣጫ መሠረት በመሬት አካባቢ የሚስተዋሉ ለሌብነትና ብልሹ አሠራሮች አንዱ መንስኤ ነበሩ ያላቸውን 44,395 (አርባ አራት ሺህ ሶሰት መቶ ዘጠና አምስት) ካርታዎች የለሚ ኩራ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት በዛሬው እለት እንዲወገዱ ማድረጉ ገለፀ።

በእለቱ የተወገዱ የካርታ አይነቶች ሠባት አይነት ሲሆኑ ለተለያየ አገልግሎቶችም ሲውሉ እንደነበር ተጠቅሷል።

እየተወገዱ ያሉት ካርታዎች በክፍለ ከተማው በመሬት ዙሪያ እየተሠሩ ካሉ የሪፎርም ስራዎች አንዱ ነው ያለው ጽ/ቤቱ ካርታዎች ከ2013 ዓ.ም እና ከዚያ በፊት እስከ አመቱ መጨረሻ ድረስ ተቋሙ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ካርታዎች ተወግደው በአዲስ መልክ ከተማ አስተዳደሩ ያተማቸውን ለመጠቀም ያለመ ስለመሆኑም ተገልጿል።

ካርታዎቹ እንዲወገዱ የተደረገበት ምክንያትም በዋናነት ከዚህ በፊት ታትመው ስራ ላይ እንዲውሉ የተደረጉ ካርታዎች በተለያየ መንገድ የተለያዩ ሰዎች እጅ ላይ ገብለው ለማይገባ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በመደረጉ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የእነዚህ ካርታዎች መወገድ በህብረተሰቡ ዘንድ እፎይታን የሚፈጥርና ለተቋሙ የለውጥ ማነቆ የሆኑ የሌብነትና ብልሹ አሠራር ምንጮች ለማክሰምና ለማድረቅ የሚያግዝ አንዱ የውሳኔ አካል ነው ተብሎለታል።

በሌላ በኩል በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ እነዚህ ካርታዎች ታትመው ሰው እጅ ላይ የገቡ ካሉ የትኛውንም አገልግሎት እንዳያገኙና ስራ ላይ እንዳይወሉ ለአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞችና ለሚመለከታቸው አካላት በደብዳቤ ማሳወቁን ጽ/ቤቱ ገልጿል።

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ገረመው ወርቁ በመልዕክታቸው እ ጽ/ቤቱ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ወደ ስራ ከገባ በኋላ ህብረተሠቡ በተለያዩ ጊዜአት ሲያነሳቸው የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት እያደረግ ነው ካለው ጥረት አንዱ ይህ የዛሬው ተግባር አንዱ አካል ነው ያሉት ኃላፊው የመንግስትና የህዝብ ሀብት የሆነውን መሬት ለመቀራመት የሚሞክሩ አካላትን ከጽ/ቤቱ ጋር ሆኖ ህብረተሠቡ እንዲታገልና እንዲያጋልጥ እንዲሁም አሁን የተጀመረወን ለውጥ ቀጣይነት እንዲኖረውና ማንኛውም ተገልጋይ ምቹና፣ፈጣን እንዲሁም ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እያደረግነው ያለውን ጥረት ህብረተሰቡ እንዲደግፍና ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

ለሚ ኩራ ኮሚኒኬሽን
መስከረም 14/2015ዓ.ም
8.5K views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 17:47:16
8.1K views14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 12:55:14
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪ በ20 ሺሕ ብር እየተሸጠ መሆኑ ተነገረ

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አንድ ዲግሪ በ20 ሺሕ ብር እየተሸጠ መሆኑን አዲስ ማለዳ ለኹለት ወር ገደማ ባደረገችው የማጣራት ሥራ አረጋግጣለች።

በዩኒቨርሲቲው ያሉ ሠራተኞች፤ ሰዎች በሚገዙት ዲግሪ ዙሪያ ሳይማሩ መደበኛ ተማሪ እንደሆኑ አስመስለው በ20 ሺሕ ብር ሐሰተኛ ዲግሪ እየሸጡ መሆኑን ማወቅ ተችሏል።

አዲስ ማለዳ ከኹለት ወር በፊት የዩኒቨርሲቲውን ዲግሪ የገዙ ሰዎች መረጃውን ሲለዋወጡ እንዲሁ ሰምታ የነበረ ሲሆን፤ ከዚያን ወቅት ጀምሮ በማጣራት ሂደት ላይ ቆይታለች። በመሆኑም፣ ዲግሪ ከገዙ ሰዎች በተደረገ ማጣራት የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች በምስጢራዊ አካሄድ ዲግሪ እየሸጡ መሆኑ ተደርሶበታል።

ለተጨማሪ ንባብ -> https://bit.ly/3LItJtY
3.5K views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 12:52:06 የከተማ አስተዳደሩ የመሬት ውክልና እግድ ውሳኔ ከባድ እንግልትና ግራ መጋባት ፈጥሯል!

.
የሞተር ብስክሌቶች ለተወሰነ ጊዜ በአዲስ አበባ እንዳይንቀሳቀሱ ታገዱ!
.
የሸኔ አባላት ከህውሀት ታጣቂዎች ጋር ተሰልፈው በግንባር ሲዋጉ ተማረኩ!



3.6K views09:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-24 06:44:57
8.4K views03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 22:53:34
ማንኛውም የመሬት አገልግሎት በውክልና እንዳይሰጥ ታግዷል
2.9K views19:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 22:51:27
ማንኛውም የመሬት አገልግሎት በውክልና እንዳይሰጥ ታገደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው በተለያየ መንገድ እየተፈፀመ ያለውን ህገወጥ የቤትና ተያያዥ ሽያጭ ለመቆጣጠርና : ስርአት : ለማስያዝ ከመስከረም 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ማንኛውም መሬትና መሬት ነክ አገልግሎቶች የይዞታው ባለቤት በአካል ሳይቀርብ በውክልና እንዳይሰጥ መታገዱን የከንቲባ ጽ/ቤት ለሁሉም ክፍለ ከተማዎች በላከው ደብዳቤ አስታውቋል

ግልባጭ
➢ ለፌዴራል ሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኣገልግሎት
➢ ለወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ጉዳዮች ኃላፊ
572 views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 10:35:06
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርድ በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። ካምፓኒው እስካሁን በይፋ አዲስ አበባ ዉስጥ አገልግሎት መስጠት ባይጀምርም ደንበኞች ከሌሎች አካባቢዎች የገዟቸውን ሲም ካርዶች በከተማዋ እየተጠቀሙት እንደሆነ ካፒታል ያገኘው መረጃ ያሳያል።
Capital
12.0K views07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 10:26:04 በኢትዮጵያ እና በኢንዶኔዢያ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ከደረሱ አደጋዎች በኋላ ለባለሃብቶች የአደጋውን መንስኤ በመደበቁ 200 ሚሊዮን ዶላር ተቀጣ። የቦይንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት ዴኒስ ሙሌንበርግ አደጋው በምን ምክንያት እንደተፈጠረ እያወቁ ሐቁን ባለመናገራቸው በግል 1 ሚሊዮን ዶላር ተቀጥተዋል።

https://bbc.in/3Uy1z8J
12.1K views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 10:18:51
በመንግሥት ተቋማት የሚገኙ ቁርጥራጭ ብረቶችና ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ለብረት አምራች ኢንዱስትሪዎች በሽያጭ እንዲተላለፉ መንግስት ወሰነ፡፡

እንደየብረት አይነቶችና የገበያው ሁኔታ የመሽጫ ዋጋ የተዘጋጀ ሲሆን ፥ ይህም የብረት አምራች ፋብሪካዎች ላይ ያለውን የግብዓት እጥረት በከፍተኛ መጠን የሚያቃልል ነው ተብሏል።

ስለሆነም ቁርጥራጭ ብረቶችና ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ፋብሪካዎቹ ያለ ጨረታ በመነሻ ዋጋ እንዲወስዱ በተወሰነው መሰረት የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ባገናዘበ መልኩ ድልድል እንደሚካሄድም ነው የተገለጸው።

በዚህም ከፌደራል መስሪያ ቤቶች ፣ ተጠሪ ተቋማት ፣ በፌዴራል ደረጃ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች እንዲሁም በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ቁርጥራጭ ብረቶችና ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ለብረት አምራች ኢንዱስትሪዎች በሽያጭ ይተላለፋሉ ተብሏል፡፡

በድልድሉ ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር የውይይት መድረክ መዘጋጀቱን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
FBC
11.4K views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ